በመጪዎቹ 100 ዓመታት ውስጥ ይፈጸማሉ ስለተባሉት ነገሮች ምን ሰምተዋል? ይላል ቢቢሲ

ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-ባለፈው ሳምንት  ፕርሰን እና ቱከር የተባሉ ተምባዮች  በመጪዎች መቶ አመታት ውስጥ ምን ምን አይነት ለውጦችን ትጠብቃላችሁ ብለው ላቀረቡት ጥያቄ፣ አስተያየት ሰጪዎች የሚከተሉትን ብለዋል።

ውቅያኖሶች ለአሳ ምርት ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ሀይል ምርትን ለመጨመር እንዲሁም እያደገ የመጣውን ህዝብ ለመመገብ ይታረሳሉ።

በድምጽ ወይም በድርጊት ሳይገልጡ ሀሳብን በማወቅ ብቻ ለመግባባት የሚያስችሉ መሳሪያዎች ይፈጠራሉ። ሳይንቲስቶች ለዘላለሙ የማይሞቱ እና እጅግ ጎበዝ እጅግ አዋቂ የሆኑ ሰዎችን ይፈጥራሉ።

የአየር ጸባይን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ይቻላል። አንታርቲካ ለንግድ ስራ ክፍት ይሆናል። በአለም ላይ አንድ የመገበያያዘ ገንዘብ ይኖራል።

አእምሮአችን በፍጥነት እንዲሰራ ለማድረግ ኮምፒዩተር እናስገጥማለን። 80 በመቶ የሚሆነው የአለም ህዝብ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ጋብቻ ይፈጽማል።

የካሊፎርንያ ግዛት ከአሜሪካ ተገንጥሎ የራሱን መንግስት ይመሰርታል። በህዋ ላይ የሚገጠመው ሊፍት ሰዎችን በቀላሉ ከምድር ወደ ህዋ እንዲበሩ ያስችላቸዋል

ሴቶች በባህላዊ መንገድ ከሚጸንሱ በዘመናዊ ቴክሎጂ መጸነስን ይመርጣሉ በረሀማ ቦታዎች አረንጓዴ ይለብሳሉ ጋብቻ ለአንድ አመት፣ ለ10 አመት እየተባለ  ስምምነት ይወሰናል፤

አሁን ያሉት አገሮች ጠፍተው በአለም ላይ አንድ መንግስት ብቻ ይኖራል። ምእራባዊያን ጦርነትን በሪሞት ኮንትሮል ብቻ ያካሂዳሉ። በእንግሊዝ አብዮት ይካሄዳል።

እርስዎስ የዛሬ 100 አመት ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች ብለው ያስባሉ? በኢሳት አድራሻ አስተያየትዎን ይጻፉልን።