መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ከፍተኛ ችግር፤ እስራትና እንግልት እየደረሰባቸዉ መሆናቸዉን የዘገበዉ የመን ታይምስ ጋዜጣ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛ ከፍተኛ ኮሚሽነርን በመጥቀስ እንደገለፀዉ እኤአ በ20110 የመን የገቡት ስደተኞች ቁጥር 34ሺህ 422 ሲሆን በ2011 ይኸዉ ቁጥር ወደ 65ሺህ ከፍ ማለቱን አመልክቷል። በ2010 ከገቡት መካከል 616 ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቅ ተገልጿል። የየመን መንግስት ወታደሮች ህገወጥ ናቸዉ ...
Read More »Author Archives: Central
የመለስ መንግስት በመሬት ሽያጭ ፖሊሲው ተደጋጋሚ ነቀፌታ ቢደርስበትም ፖሊሲውን ለመቀየር ፍላጎት አላሳያም ተባለ
መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሰት በአገር ዉስጥና በዉጭ የሰላ ተቃዉሞ ቢሰነዘርበትም በኢትዮጵያ አነስተኛ ድሃ ገበሬዎችን ከአያት ቅድመ አያት ይዞታቸዉ ያለፈቃዳቸዉ እያፈናቀለ መሬታቸዉን ለዉጭ ከበርቴዎች የሚያከራየዉ እጅግ አነስተኛ በሆነ አመታዊ የኪራይ ዋጋ ክፍያ እንደሆነ ሮይተርስ ገለፀ። ሮይተርስ የዜና ወኪል ይህንን ያስታወቀዉ አነስተኛ ክፍያዉን ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ለመዘርጋት እቅድ እንዳለዉ በግብርና ሚኒስቴር ...
Read More »አቶ መለስ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች ቃሊቲ እየተመላለሱ ነው
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ የላኩዋቸው ሽማግሌዎች ቃሊቲ እየተመላለሱ ነው የአቶ መለስ መንግሥት የወከላቸው ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት በመሄድ የፖለቲካ እሥረኛ የሆኑ ፍርደኛ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን ይቅርታ ለማስጠየቅ የማግባባት ሙከራ ማድረግ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የፍትህ ሚኒስቴር ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተወከሉ ሽማግሌዎች ወደ ማረሚያ ቤት እየተመላለሱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሊቀመንበርን ...
Read More »የፌዴራል አቃቤ ህግ በፍትህ ጋዜጣ ላይ አቤቱታ አቀረበ
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ፍትህ ጋዜጣ የተከሳሾችን ቃል ብቻ በጋዜጣ በማስተናገድና ዐቃቤ ሕግ ከመንግሥት ፖለቲካዊ ጫና ነፃ ሆኖ እንደማይሰራ በማተት በህዝብ ላይ እምነት እንድናጣ አድርጎናል ሲል”የፌዴራል አቃቤ ህግ አቤቱታ አቀረበ። አቃቤ ህግ ይህን ክስ ያቀረበው፤ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ከሰዓት በኋላ በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በማረሚያ ቤት ሆነው ከሚከራከሩ ስምንት ተከሳሾች ...
Read More »ኢትዮጵያውያን ለዘመዶቻቸው የላኩት ገንዘብ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ወደ ውጭ በመላክ ካስገኙት ገንዘብ በለጠ
መጋቢት ፳፯ (ሃይ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት 7 አመታት 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት እንዳገኘ በተደጋጋሚ መናገሩ ይታወቃል። የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋም ወይም አይኤም ኤፍ የኢትየጵያ እድገት የተጋነነ ነው በማለት እድገቱ ከ6 እስከ 7 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል በመግለጥ የመንግስትን መከራከሪያ ውድቅ ሲያድርግ ቆይቷል። ገዢው ፓርቲ የኢኮኖሚ እድገቱ የመጣው መንግስት የውጭ ንግድን ማእከል ያደረገ ፖሊሲ ቀርጾ በመንቀሳቀሱ መሆኑን ይገልጣል። ...
Read More »የኢሳትን ህልውና የማረጋገጥ ጥሪ
መጋቢት 27 ቀን 2004 ዓ/ም የኢሳት – ማኔጅመንት ኢሳት ከተቋቋመ ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ ህዝባችን የሞራል የገንዘብ እና የተለያዩ እርዳታዎች በማድረጉ ይህ የህዝብ አይንና ጆሮ የሆነ የሚድያ ተቋም ዛሬ የሚገኝበት ደረጃል ለመድረስ በቅቷል። ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀላሉ የማይዳፈን የተስፋ ብርሃን መፈንጠቅ አስችሏል። ላለፉት ሶስት ወራት የኢሳትን ወርሃዊ ወጪ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሸፈንና የድርጅቱን ህልውና ለመታደግ ይሆናል ብለን ያቀረብነውን የመፍትሄ ...
Read More »የአማራ ተወላጆችን በግዳጅ ወደ መጡበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት ተወገዘ
መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ይኖረ የነበሩ ከ20 እስከ 80 ሺ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች ለአካባቢው ህዝብ አደጋ ናቸው ተብለው እየተፈናቀሉ መሆናቸውን በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ጋዜጦች ሰፊ ትኩረት ሰጥተው በመዘገብ ላይ ናቸው። በዛሬው እለት ለንባብ የበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ ተፈናቃዮች በግዳጅ ወደ መጡበት እየተመለሱ መሆኑን ፣ የአማራ ...
Read More »ኢትዮጵያ ውስጥ በሁለት እስር ቤቶች ውስጥ ብቻ 401 የፖለቲካ እስረኞች እንደሚገኙ ተገለጸ
መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ አንድም ሰው የለም ቢልም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁለት እስር ቤቶች ውስጥ ብቻ 401 የፖለቲካ እስረኞች እንደሚገኙ ተገለጸ። የተጠቀሰው የፖለቲካ እስረኞች አሀዝ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት የታሠሩትን ብቻ እንጂ፤ከዚያ በፊት ያለውን እንደማያካትትም ተመልክቷል። ምንጮቹን በመጥቀስ ፍኖተ ነፃነት እንደዘገበው፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ የሀሰት ክስ የተመሰረተባቸው 401 እስረኞች የሚገኙት፤በቃሊቱና ...
Read More »የሱማሌ ክልል ሦስቱ ርዕሳነ- መስተዳድሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ
መጋቢት ፳፮ (ሃይ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሱማሌ ክልል ሦስቱ ርዕሳነ- መስተዳድሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ። የሁለቱ ያለመከሰስ መብት ተነስቷል። በጅጅጋ ከተማ ከትናትንት በስቲያ በተጀመረው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ ጉባዔ ፤ሦስቱም የክልሉ ምክትል ርዕሳነ- መስተዳደሮች ከሥልጣናቸው ተሻሩ፡፡ ቀደም ሲልም ለአንድ ክልል ሦስት ሰዎች ከተሰጣቸው የቢሮ ሃላፊነት ባሻገር በምክትል ፕሬዚዳንትነት ጭምር እንዲሾሙ መደረጋቸው ብዙዎችን ማስገረሙ ይታወሳል። የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ...
Read More »ሚድሮክ ወርቅ በጉጂና በቦረና ዞኖች ነዋሪዎችን ለማፈናቀል ማቀዱ ተቃውሞ አስነሳ
መጋቢት ፳፭ (ሃይ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሻኪሶ ወረዳ በሬጂ ቀበሌ፣ በሰባ ቦሩ ወረዳ በ ቡሪ ኢጄርሳ ቀበሌ እንዲሁም በቦረና ዞን በመልካ ሶዳ ወረዳ ሀሎ መጣዳ ቀበሌ ስር የሚገኙ ኤቢቻ፣ ሎቶሪ፣ ኦኮቴ፣ ኦዳ ሀንቃሪ ፣ ደዳቡቱ እና አዩ ቦዳ ቀበሌዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የካሳ ክፍያ እና የመስፈሪያ ቦታ ሳይሰጣቸው አካባቢውን ለሚድሮክ ኢትዮጵያ አስረክበው እንዲወጡ በመታዘዛቸው የአካባቢው ነዋሪዎች “አካባቢውን ለቀን አንወጣም ...
Read More »