ሚያዚያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ኤፕሪል 27 ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው በክልሉ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት ወደ አደገኛ ሁኔታ እየተሸጋገረ ነው ብሎአል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ኤፕሪል 17 በዱብቲ ከተማ በህዝቡ ላይ በፈጸሙት ድብደባ 8 ሴቶችና 12 ወንዶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፋጡማ ሙሳ የተባለች ሴት ቤቷን የሚያፈርሱባትን ሰራተኞች በመቃወሙዋ በጡቷ ላይ በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ አሁንም ድረስ በህመም ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ሕይወታቸዉን የሚያጡ እናቶች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ የተመድ የዜና አገልግሎት ገለፀ
ሚያዚያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የጤና ድርጅትን ዋቤ ያደረገዉ መረጃ እንደሚገልፀዉ በኢትዮጵያ ከ100ሺህ እናቶች መካከል 676 የሚሆኑት በወሊድ ወቅት ህይወታቸዉን የሚያጡ ሲሆን በታዳጊ አገራት ካለዉ አማካይ ከ100 ሺህ እናቶች የ290 እናቶችን ሞት በእጥፍ የሚበልጥ ነዉ። በበለፀጉት አገራት ከ100ሺህ እናቶች በወሊድ ምክንያት ሕይወታቸዉን ሊያጡ የሚችሉት 14 ብቻ ናቸዉ። በኢትዮጵያ 10 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ...
Read More »በአፋር አንድ ወጣት ተገደለ ሶስት ቆሰሉ
ሚያዚያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፋር ክልል በዱብቲ ከተማ በህዝቡ እና በመንግስት ማካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ደም መፋሰስ እያመራ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ በዛሬው እለት የፌደራል ፖሊስ አባላት የ17 አመቱን የ7ኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን አሊ ኡመር ሙሀመድን በሶስት ጥይት ገድለው በጓደኞቹ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ድ ብደባ ፈጽመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቀበሌ አመራሮች ሳይቀሩ የልዩ ...
Read More »ክንፈሚካኤል ደበበ ለተመስገን ደሳለኝ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ አለ
ሚያዚያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ 5ተኛ ተከሳሽ የሆነው ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) የፌዴራል ዐቃቤ-ህግ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ላቀረበው አቤቱታ ምላሽ የሚሰጥ የምሥክርነት ቃሉን ዛሬ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት አሰምቷል፡፡ የመኢዴፓ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ክንፈሚካኤል ደበበ ” በፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 6 ቁጥር 183 ዓርብ ፣ ሚያዚያ 5 ቀን ...
Read More »የተመድ ሰራተኞች መታሰር የድርጅቱን ድክመት ያሳያል ተባለ
ሚያዚያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ያለ አግባብ በኢትዮጵያ ዉስጥ መታሰር የድርጅቱን ድክመት ያሳያል ሲል ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር የመረጃ ምንጭ ገለፀ የኢትዮጵያ መንግስት ከአንድ አመት በላይ ክስ ሳይመሰረትበት አንድ የድርጅቱን ሰራተኛ እስር ቤት እንደጣለዉና አንድ ሌላ ሰራተኛ ደግሞ በፀረ ሽብር ህግ ተከሶ በእስር ላይ መገኘቱን በማመልከት በአፍሪቃ ቀንድ በምእራባዊያን የሚደገፈዉ አናሳ የመለስ ዜናዊ ...
Read More »ለዶክተር ካትሪን ሐምሊን የክብር ዜግነት ተሰጠ
ሚያዚያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌስቱላ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት ለሆኑት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የክብር ዜግነት ተሰጠ:: ዶክተር ካትሪን በኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታሎችን በመመሰረት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የሕክምና እንዲሁም የሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት በመቶሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እናቶችን ሕይወት ታድገዋል። የክብር ዜግነቱን የሰጡት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ የተወለዱ ናቸው። በአዲስ አበባ በቀድሞው ...
Read More »በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ
ሚያዚያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ 22 ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘገበ። እንደ ፍኖተ-ነጻነት ዘገባ በሁለቱ ክልሎች የድንበር ነዋሪዎች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ የቦታ ይገባኛል ጥያቄ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ “በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ልዩ ሥፍራው “ጊዳ ኪራሞ” እና “ጊዳ አያና” በተባሉ ወረዳዎች ለተነሳው ግጭት መንስዔው፤ አቤንቱ፣ ቄሎ ...
Read More »የብርሃን እና ሠላም እና የጋዜጣ አሳታሚዎች ተፋጠዋል
ሚያዚያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ለአሳታሚዎች የላከው አወዛጋቢው የሕትመት ስምምነት ውል በመቃወም አሳታሚዎች አንድ አቋም በሚይዙበት ሁኔታ ላይ ዛሬ በአዲስአበባ መከሩ፡፡ አብዛኛውን የጋዜጦች ሕትመት ገበያ አማራጭ ባለመኖሩ ምክንያት በብቸኝነት የያዘው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት በቅርቡ ጋዜጦችና መጽሔቶች በሕግ የሚያስጠይቅ ይዘት ያለው ሥራ ማሳተም እንደማይችሉ፣ድርጅቱ የሕግ ተጠያቂነትን ያስከትላል ብሎ ካመነ ለማተም እንደማይገደድ፣ከነአካቴውም ውል ...
Read More »ሃዋላ ከኤክስፖርት ገቢ በለጠ
ሚያዚያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2004 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ሰባት ወራት አገሪቱ የተለመደውን ቡና፣ቆዳና ሌጦ፣ጥራጥሬ፣ጫት እና የመሣሰሉትን ለዓለም አቀፉ ገበያ በማቅረብ ከተገኘው ገቢ ይልቅ በሃዋላ የሚገኘው የውጪ ምንዛሪ የተሻለ ደረጃ አገኘ፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በተጠቀሰው ግዜ ከወጪ ንግድ 1.6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን በውጪ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል በህወሀት ሞግዚትነት እየተመራ ነው
ሚያዚያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ክልሉ በአሁኑ ጊዜ እየተመራ ያለው በርዕሰ መስተዳድሩ በአቶ አለማየሁ አቶምሳ ሳይሆን፤ በህወሀቱ አቶ ገብረተንሳይ ወልደተንሳይ ነው። በሕዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በህወሀት ሞግዚትነት እየተመራ ያለው፤ የኦህዴድ ባለሥልጣናት ሀላፊነታቸውን መወጣት ስላልቻሉ ነው ተብሏል። ክልሉ በህገ መንግሥትና በህዝብ ተወካዮች ህግ መሰረት ክልላዊ የመንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር እንዳለው ይታወቃል። ይሁንና ...
Read More »