Author Archives: Central

የመድረኩ ሊቀመንበር ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ምንም አይነት ምስክርነት እንዳልሰጡ ገለጡ::

ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋዜጠኞች የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የሰጠሁትን የሐዘን መግለጫ ወደ ጎን ጥለው የራሳቸውን የፈጠራ ድርሰት አዘጋጅተው አስተላልፈዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንዳሻው ቅሬታቸውን አቅርበዋል። አቶ ጥላሁን የሀዘን መግለጫውን ባስተላለፉበት ወቅት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋዜጠኞች ስለ ጠቅላይሚኒስትሩ የስራ ሁኔታ አስተያየት ለመቀበል ጥያቄ አቅርበው ...

Read More »

መኢአድ ህዝብ የሥልጣን ባለቤት የሚሆንበት ኮንፈረንስ እንዲጠራ ጠየቀ::

ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ህዝብ በኢህአዴግ አገዛዝ እየተፈፀመበት ካለው አፈናና ረገጣ ተላቆ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ሁሉን አቀፍ ኮንፈረንስ እንዲጠራ ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥያቄ አቀረበ። ፓርቲው ሰሞኑን ባቀረበው ጥሪ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተቋቋሙ ፓርቲዎች በሙሉ እንዲሁም ሲቪክ ማኅበራት፣ ...

Read More »

የአዲስ አበባ አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለዕድለኞችን ዝርዝር “አገሪቱ ሐዘን ላይ ናት” በሚል ለሕዝብ እንዳይሰራጭ አገደ፡፡

ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዲስ አበባ አስተዳደር የጠ/ሚኒስትር መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በዕጣ የለያቸውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለዕድለኞችን ዝርዝር “አዲስ ልሳን” የያዘውን ጋዜጣ “አገሪቱ ሐዘን ላይ ናት” በሚል ለሕዝብ እንዳይሰራጭ አገደ፡፡ ነሃሴ 13 ቀን 2004 ዓ.ም በሕዝብ ፊት በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት ለ7 ሺ 300 የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ዕጣ የወጣ ሲሆን ዕድለኞች የዕጣውን ውጤት ከአዲስአበባ አስተዳደር ድረገጽ መመልከት ...

Read More »

እየታየ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሕልፈት የሐዘን አገላለጽ አቅጣጫውን የሳተ እንዳይሆን፣ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መጠየቁን ሪፖርተር ዘገበ፡፡

ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት በኋላ እየታየ ያለው የሐዘን አገላለጽ ዓላማውንና አቅጣጫውን የሳተ እንዳይሆን፣ ሕዝቡም ሆነ የመንግሥት አካላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መጠየቁን ሪፖርተር ዘገበ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕይወታቸው ማለፉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ከተነገረ  ካለፈው ነሐሴ 15  ቀን  ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው፣ በሁሉም ክልሎች እና ወረዳዎች  ሕዝቡ ሐዘኑን እየገለጸ መሆኑን የተናገሩ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች፣ ዜጐች ...

Read More »

ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን በቤተመንግስት ተገኝተው ሀዘናቸውን ገለጡ::

ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት መንጮች እንደገለጡት በአቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአትና የአቶ መለስን አስከሬን በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው ለመቀበል አለመቻላቸው ታመዋል ከሚለው ጀምሮ ሞተዋል የሚል ዜና እንዲሰራጭ ግድ ብሎአል። ሼክ አላሙዲን ከአቡነ ጳውሎስና ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ያላቸው ልዩ ቀረቤታ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ባለሀብቱ በጳጳሱ ቀብር ላይ ሳይገኙ፣ በአቶ መለስ የሽኝት ዝግጅት ላይ ዘግይተው ተገኝተዋል። ሼክ ...

Read More »

አባይን የደፈረ መሪ የሚል ፎቶ ግራፍ እያዞሩ የሚሸጡ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች በፖሊስ እየተዋከቡ ነው::

ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቶ መለስ ዜናዊን ከዚህ አለም በሞት መለየት ተከትሎ፣ መንግስት በይፋ በየከተማው ሙሾ እአስወረደ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የአዲስ አበባ ፖሊሶች  “አባይን የደፈረው መሪ” የሚል ጽሁፍ ያለበትን የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ በፒያሳ ጎዳናዎች ላይ ፣ በ5 ብር ሲሸጡ የተገኙ የጎዳና ላይ አዟሪዎች በፖሊስ ተይዘው የሚሸጡዋቸውን ፎቶዎች እንዲቀሙ ተደርጓል።   አንድ የአዲስ አበባ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በልዩ ትእዛዝ ተፈታ::

ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ልዩ ትዕዛዝ በፌዴራል ዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ተቋርጦ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲፈታ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተፈትቷል።   ምንጮቻችን እንደገለጹልን በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ተኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ...

Read More »

የአቶ መለስ እና የአቡነ ጳውሎስ ህልፈት ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሌላ መከራ ይዞ መምጣቱን መነኮሳቱ ተናገሩ::

ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢሳት ያነጋገራቸው የዋልድባ ገዳም መነኮሳት እንደተናገሩት አቶ መለስ ዜናዊ እና አቡነጰ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ ጀምሮ በመኖካሳቱ ላይ የሚደርሰው እንግልት ጨምሯል።   የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደሮችን ልከው መነኮሳቱን እያሳደዱ መገኘታቸው፣ ከ13 በላይ መነኮሳት ከገዳሙ ወጥተው እንዲሸሸጉ ግድ ማለቱን ኢሳት ያነጋገራቸው አባት ገልጠዋል   የታጣቂዎችን እንግልት በመሸሽ ከተሰደዱት መካከል አባ ወልደ ...

Read More »