የአቶ መለስ እና የአቡነ ጳውሎስ ህልፈት ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሌላ መከራ ይዞ መምጣቱን መነኮሳቱ ተናገሩ::

ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ኢሳት ያነጋገራቸው የዋልድባ ገዳም መነኮሳት እንደተናገሩት አቶ መለስ ዜናዊ እና አቡነጰ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ ጀምሮ በመኖካሳቱ ላይ የሚደርሰው እንግልት ጨምሯል።

 

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደሮችን ልከው መነኮሳቱን እያሳደዱ መገኘታቸው፣ ከ13 በላይ መነኮሳት ከገዳሙ ወጥተው እንዲሸሸጉ ግድ ማለቱን ኢሳት ያነጋገራቸው አባት ገልጠዋል

 

የታጣቂዎችን እንግልት በመሸሽ ከተሰደዱት መካከል አባ ወልደ ጊዮርጊስ ገብረማርያም፣ አባ ገብረማርያም ገብረዮሀንስ፣ አባ ገብረህይወት ተክለማርያም፣ አባ ገብረስላሴ ዋለለኝ፣ አባ ገብረማርያም ወልደ ሳሙኤል፣ አባ ሀይለ እየሱስ አሸኔ፣ አባ ሀይለእየሱስ ወልደ ሳሙኤል፣ መናኝ ሀይለማርያም ወልደ ሳሙኤል፣ መናኝ ገብረጊዮርጊስ ወልደ ሳሙኤል፣ አባ ገብረስላሴ ዋለልኝ፣ መናኝ ታዲዮስ እና ሌሎች እናቶችም ይገኙበታል።

 

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide