ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሸበት በ30 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ ኤጀንሲው ትላንት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚጠቁመው ከ12 ወራቱ አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሸበት ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሸበት 36 ነጥብ 5 በመቶ፣ምግብ ነክ ያልሆኑ 20 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ ከምግብ ውስጥ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ ውስጥ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊው ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ የግንቦት7 አመራሮች ተናገሩ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ከፍተኛ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ እና ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ ንቅናቄው በስልጣን ላይ ያለውን ሀይል አስገድዶ ከተቻለ ወደ ድርድር ካልተቻለም ለማስወገድ፣ ፈጣን የሆነ ውጤታማ ስራ የሚሰራበትን ዝግጅት እያደረገ ነው። ገዢው ፓርቲ ህልውናውንም አገሪቱንም ከጥፋት ለመከላከል በአፋጣኝ የፖለቲካ ለውጥ በማድረግ ሁሉም በእኩል የሚሳተፉበት የሽግግር ጊዜ አስተዳደር እንዲመሰረት ...
Read More »ኢህአዴግ የዩኒቨርስቲ መምህራንን ለስብሰባ ጠራ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምንጮቻችን እንደገለጡት መምህራኑ ከመስከርም ሶስት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆይ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው አጀንዳ ባይታወቅም የአገዛዙ ተተኪ አመራሮች ልክ አቶ መለስ ወደ ስልጣን ሲመጡ እንዳደረጉት ሁሉ ራሳቸውን ከምሁራን ጋር በማስተዋወቅ፣ ተቀባይነት ለማግኘት ነው የሚል መላምት አለ። በተለያዩ አገራት የሚገኙ የዩኒቨርስቲ መምህራን በሚሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ ምሁራኑ በአገራቸው መጻኢ እድል ላይ ገንቢ አስተያየቶችን ...
Read More »“ወደ ሥልጣን የመጣው አመራር ባለፈው መንገድ ሊቀጥል አይችልም” ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አስጠነቀቁ
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በቀጣይ በኢትዮጵያ የተሸለ ነገር የሚመጣው፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ተገናኝተው፣ በክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ተመካክረው መፍትሔ ማምጣት የሚችሉበት ዕድል ሲፈጠር ብቻ ነው።” ሲሉ አቶ ቡልቻ ወደ ሥልጣን እየመጣ ላለው አዲስ አመራር ቡድን መልዕክት አስተላለፈዋል። የቀድሞው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር ይህን ያሉት፤ዛሬ ለንባብ ከበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። “ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ...
Read More »ኢትዮጵያዊው አርሶአደር የእንግሊዝን መንግስት ሊከስ ነው
ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ ድርጅት የሰብአዊ መብቴን ጥሶብኛል ሲሉ ነው ክስ ለማቅረብ የተነሳሱት ። ሚስተር ኦ የተባሉት ሰው ለእንግሊዝ ጠበቆች እንደተናገሩት በመንደር ምሰረታ መርሀ ግብር የተነሳ ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገርፈዋል እንዲሁም አስገድዶ መድፈሮች ሲፈጸሙ ተመልክተዋል። የአርሶአደር ኦ ጠበቆች እንዳሉት የመንደር መስረታው መርሀ ግብር ከእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል። የልማት ...
Read More »በአቶ በረከት ስምኦንና በህወሀት መካከል ያለው ፍጥጫ ተካሯል
ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ሳምንት በፊት አቶ በረከት ስምኦን ፣ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት እንደተፈጸመ ፣ የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ስልጣን ፓርላማው በአስቸኳይ ተጠርቶ ያጸድቀዋል የሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ የመንግስቱ የመገናኛ ብዙሀን አቶ ሀይለማርያምን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ እስከመጥራት ደረሱ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረትም አቶ ሀይለማርያም እስከ 2007 ዓም የጠቅላይ ሚኒሰትርነቱን ቦታ ...
Read More »በአማራ ክልል የመንግስት ስራተኛዉ የወር ደሞዙን እንዲለግስ ተጠየቀ
ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰራተኛው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀዱትን ልማት ለማስቀጠል በሚል ሰበብ የወር ደሞዙን በግድ እንዲለግስ እየተገደደ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። የመንግስት ሰራተኛዉ በኑሮ ዉድነት እየተንገላታ ባለበት ባሁኑ ወቅት እንዲህ አይነቱን ውሳኔ ማስተላለፍ እጅግ የሚዘገንን ነው በማለት አንድ የመንግስት ሰራተኛ ምሬታቸውን ለኢሳት ገልጠዋል። ከዚህ ቀደም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የከፈሉት ገንዘብ አራቁቷቸው መሄዱን የገለጡት ...
Read More »ኢሳት በአውስትራሊያ የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ
ነሀሴ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን መርጃ እንዲውል በአውስትራሊያ ከተሞች ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከ 115 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ። የሜልቦርን ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ቡድን ባደረገለት ግብዣ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ባለፈው ኦገስት 12 ቀን አውስትራሊያ የገባው ተወዳጁ አርቲስት፤ በአምስት የአውስትራሊያ ከተሞች ማለትም በሜልቦርን፣ በሲድኒ፣ በአድላይድ፣ በብሪዝበንና በፐርዝ እንዲሁም በኒውዝላንድ-ኦክላንድ ባካሄዳቸው ደማቅ ዝግጅቶች ...
Read More »የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ዘመቻ መጠቀሙ እንዳሳፈራቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ
ነሀሴ ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ፌደራሊስ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የበላይ ጠባቂና የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ዲክታተር ነበሩ ብለዋል:: የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ኢስነምግባራዊ እና የሚዘገንን ነው በማለት መላውን የኢህአዴግ አመራሮች ወቅሰዋል :: ኢህአዴግ ህዝቡን አልቅሱ ብሎ አለማስገደዱን ይልቁንም በራሱ ፈቃድ ፈንቅሎ እንደወጣ ይናገራል ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ ታፈነዋል አለ
ነሀሴ ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ በሀገሪቱ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የሰብዓዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ መታፈናቸውን ቀጥለዋል ሲል አንድነት ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ። አንድነት ፓርቲ ፦”የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ መታገድ፤አምባገነናዊው ስርዓት አፈናውን አጠናክሮና አባብሶ መቀጠሉን የሚያሳይ ድርጊት ነው” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤የ አቶ መለስን ሞት ተከትሎ በሀገሪቱ ሊስተካከሉ የሚገባቸው የሰብዓዊ፣የዲሞክራሲያዊና ሀሳብን ...
Read More »