ኢህአዴግ የዩኒቨርስቲ መምህራንን ለስብሰባ ጠራ

ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ምንጮቻችን እንደገለጡት መምህራኑ  ከመስከርም ሶስት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆይ ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው አጀንዳ ባይታወቅም የአገዛዙ ተተኪ አመራሮች ልክ አቶ መለስ ወደ ስልጣን ሲመጡ እንዳደረጉት ሁሉ ራሳቸውን ከምሁራን ጋር በማስተዋወቅ፣ ተቀባይነት ለማግኘት ነው የሚል መላምት አለ።

በተለያዩ አገራት የሚገኙ የዩኒቨርስቲ መምህራን በሚሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ ምሁራኑ በአገራቸው መጻኢ እድል ላይ ገንቢ አስተያየቶችን ይሰጣሉ ተብሎ ይታመናል።

ኢህአዴግ ከምሁራኑ ጋር የሚያደርገውን ስብሰባ ሲጨርስ ወደ ሌሎች ተቋማትም ሰረተኞችም እንደሚያወርድ ታውቋል። ከምሁራን ጋር የሚደረገውን ውይይት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide