ኢትዮጵያዊው አርሶአደር የእንግሊዝን መንግስት ሊከስ ነው

ጳጉሜን ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ ድርጅት የሰብአዊ መብቴን ጥሶብኛል ሲሉ ነው ክስ ለማቅረብ የተነሳሱት ።

ሚስተር ኦ የተባሉት ሰው ለእንግሊዝ ጠበቆች እንደተናገሩት በመንደር ምሰረታ መርሀ ግብር የተነሳ ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገርፈዋል እንዲሁም አስገድዶ መድፈሮች ሲፈጸሙ ተመልክተዋል።

የአርሶአደር ኦ ጠበቆች እንዳሉት የመንደር መስረታው መርሀ ግብር ከእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል።

የልማት ትብብሩ መስሪያቤት በበኩሉ ለሰፈራ መርሀግብሩ ገንዘብ አለመስጠቱን አስታውቋል።

በስደት ኬንያ ውስጥ የሚኖሩት በጋንቤላ የተወለዱት  አርሶአደር ኦ  የስድስት ልጆች አባት ናቸው። አርሶአደሩ ብዙ ሰዎች መደብደባቸውን፣ሴቶች መደፈራቸውንና ተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን  ለጠበቆች ተናግረዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide