አቶ አየለ ጫሚሶ በሕገወጥ ዶላር ምንዛሪ ለመጠቀም ሞክረው ባለመሳካቱ ግብረአበሮቻቸውን በወንጀል ከሰሱ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሕጋዊ ወራሸ እኔ ነኝ የሚሉት አቶ አየለ ጫሚሶ ፎርጅድ ገንዘብ በማዘዋወር ወንጀል ውስጥ ተሳትፈው በተፈጠረ አለመግባባት ጉዳዩን ወደፖሊስ ወስደው ራሳቸው ነጻ የሆኑበት የሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር የወንጀል ድርጊትን አንዳንድ የፖሊስ አባላት ተቃወሙት ፡፡ አቶ አየለ ጫሚሶ ኦልበሞ መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ  ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ...

Read More »

ኢትዮጵያ ባለፈው የበጀት አመት ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ በእርዳታና በብድር መልክ ማግኘቷ ታወቀ

ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፈው የበጀት አመት አገሪቱ በእርዳታና በብድር መልክ 47 ቢሊዮን ብር ወይም ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝታለች። ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊዮን ብር በእርዳታ መልክ ቀሪው ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው። ባለፈው አመትም አገሪቱ ካለባት እዳ ውሰጥ  324 ሚሊዮን ብር እንደተሰረዘላት ታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት አገሪቱ ያለባትን እዳ በትክክት ለህዝብ ግልጽ ...

Read More »

በምእራብ ጎጃም ዞን አንድ የፌደራል ፖሊስ ጓደኛውን ጨምሮ 4 ሰዎችን ገድሎ 2ቱን አቆሰለ

መስከረም ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደተናገሩት ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ክልል፣ በምእራብ ጎጃም ዞን፣ በሽንዲ ከተማ እሁድ መስከረም 28፣ 2004ዓም ነው። የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጡት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች  ትንሳኤ በሚባለው ሆቴል ውስጥ የባሪሴሎና እና የሪያል ማድሪድን ኳስ ጨዋታ በቴሌቪዥን እየተከታተሉ በነበረበት ወቅት፣  አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ህዝቡን በማስተናገድ ላይ የነበረችን  ወጣት ለመውሰድ ለሆቴሉ ባለቤት ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ...

Read More »

የኢሕአዴግ ታጋዮች ጡረታ ትግሉን ከተቀላቀሉበት ጊዜ ጀምሮ ሊሰላ ነው

መስከረም ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞውን ወታደራዊ አገዛዝ የመገርሰስ ትግል ውስጥ የተሳተፉና በአሁኑ ወቅት በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ የቀድሞ ታጋዮች ጡረታ (ማኅበራዊ ዋስትና) ትግሉን ከተቀላቀሉበት ጊዜ አንስቶ እንዲሰላ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ  ማሳሰቡን ሪፖርትር ዘገበ ለመንግሥት ተቋማት የተሰራጨው ደብዳቤ ከሰኔ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ የጋዜጣው ዘገባ ያመለክታል፡፡  ከአምስት ወራት ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደረሳቸው

መስከረም ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወይዘሮ  አዜብ ቤተመንግስቱን ለተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያስረክቡ ማስጠንቀቂያ  እንደደረሳቸው ሰንደቅ ዘገበ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ከተሾሙ 19ኛ ቀናቸውን የያዙት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቤተሰባቸውን ይዘው ወደቤተመንግስት እስካሁን መግባት አልቻሉም።   በመሆኑም፤ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር  ባለቤትና የህወሓት ሥራአስፈጻሚ አባል የሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን ለተተኪው ጠ/ሚኒስትር ማስረከብ ባለባቸው ጊዜ ውስጥ ማስረከብ ባለመቻላቸው፤ የማስጠንቀቂያ የጊዜ ገደብ እንደተሰጣቸው ...

Read More »

ኅብረተሰቡ ወዳላስፈላጊ እንቅስቃሴ ከመግባቱ በፊት መንግሥት ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲሰጥ ኢፍዴሀግ ጠየቀ

መስከረም ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በአንድ ጥላ ሥር ያሰባሰበው ኢፍዴኃግ፤ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ እንዲመልስ በአፅንኦት ያስገነዘበው፤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰኞ ዕለት በጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። የግንባሩ አመራሮች  በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ፤በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የአገሪቱን ሁለንተናዊ ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥሉ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች  ማንዣበባቸውን አመልክተዋል። ‹‹ እጅግ ውስብስብና ዘርፈ ብዙ የሆኑ ...

Read More »

በለገጣፎ ለገዳዲ አካባቢ ለእስር ተዳርገው የነበሩ ወጣቶች ፣ ችግሩ እስካልተፈታ ድረስ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ

መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ልዩ ዞን በለገጣፎ ለገዳዲ አካባቢ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጸመውን ሙስና በመቃወማቸው ለእስር ተዳርገው የነበሩ 7 ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ ህዝቡ ባሳየው ተቃውሞ በ21 ሺ ብር የዋስትና ገንዘብ እንዲፈቱ መደረጉ ታውቋል። ወጣቶቹ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆን፣ አቃቢ ህግ ስትጠሩ ትመጣላችሁ በማለት አሰናብቷቸዋል። ታስረው ከተፈቱት ወጣቶች መካከል መኮንን ተስፋየ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የአክራሪነትና የሽብርተኝነት አደጋ መገታት አለበት ሲሉ ሚኒስትር ደብረጺዮን ተናገሩ

መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ም/ል ሊቀመንበር በመሆን በቅርቡ የተመረጡት የየኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ይህንን የተናገሩት ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ሚኒስትሩ  በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የአክራሪነትና የሽብርተኝነት አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ አገሪቱን ሊበታትናት መቃረቡን ገልጠዋል። ” በሀይማኖት ሽፋን ኢትዮጵያን ለመበታተን ና ለማተራመስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ዝም ብለን መመልከት የለብንም፤ አሁን ...

Read More »

ህገወጥ ቤቶችን ሰርታችሁዋል ተብለው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መፍትሄ አለማግኘታቸውን ተናገሩ

መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየካ እና በንፋስ ስልክ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ቤታቸው የፈረሰባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች አሁንም መጠጊያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው። በየካ አካባቢ የሚኖሩ አንድ ግለሰብ ለኢሳት እንደገለጡት ህጻናት፣ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች አሁንም መጠለያ አጥተው ቢቸገሩም መንግስት ግን ለችግራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። መሀንዲሶች ህጋዊ ነው ብለው በማጽደቃቸው ገንዘባቸውን አፍስሰው መሰረተ ልማቶችን መስራታቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊው የታክሲ ሾፌር ሩብ ሚሊዮን ዶላር ረስቶ ለወረደው ተሳፋሪ ገንዘቡን መለሰ

መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በላስ ቬጋስ የታክሲ ሾፈር የሆነው አዳም ወልደማርያም፣ አንድ በቁማር 250 ሺ ዶላር አሸንፎ ገንዘቡን ታክሲው ውስጥ ረስቶ ለወረደ ሰው ነው ገንዘቡን የመለሰው። አዳም ወልደማርያም  በላፕቶፕ መያዢያ ውስጥ ታጭቆ ያገኘውን ገንዘብ እንዳተመለከተ ወዲያውኑ ለተቆጣጠሪው ማስረከቡን የደይሊ ሜል ሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል። ተሳፋሪው ገንዘቡን መልሶ በማግኘቱ መደሰቱንና ለወልደማርያምም 2 ሺ ዶላር እንደሰጠው ታውቋል። አዳም ገንዘቡን ...

Read More »