የአዲስ አበባ ሕዝብ የመራጭነት ካርድ እየወሰደ አይደለም

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሚያዝያ ወር ለሚያካሂደው የአካባቢና የአዲስአበባ ምርጫ ከታህሳስ 22 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ ቢጀምርም በተለይ በአዲስአበባ ምዝገባው የተቀዛቀዘ መሆኑ ታወቀ፡፡ የምርጫ ጽ/ቤቶች ለመራጮች ምዝገባ  ከታህሳስ 22 ቀን እስከ ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም  ክፍት የተደረጉ ቢሆኑም ባለፈው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የነበረው የሕዝቡ ምላሽ ለገዥው ፓርቲም አስደንጋጭ እንደሆነ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ ተጠንስሶ በከሸፈው የግድያ ሙከራ ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ለመግደል ተጠንስሶ የነበረውና በ ኤፍ.ቢ.አይ መርማሪዎች የከሸፈው  የግድያ ሙከራ ዜና በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያስቆጣ ነው። በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ የታቀዳውን የግድያ ሙከራ የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ማክሸፉን ተከትሎ በቦስተን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አክቲቪስቶች ሌሎች የህውሀት ጉዳይ አስፈጻሚ ያሎቸውን ሰዎችና ስም ዝርዝራቸውን ለኢሳት አድርሰዋል:: እነዚህ ግለሰቦች በተለይ በሀገር ቤት ንብረት ያፈሩ ኢትዮጵያዊያን በየትኛውም ህዝባዊ ...

Read More »

የ 104 አመት ኢትዮጵያዊ በዴንቨር ይኖራሉ

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ 104 አመት የዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያዊ ላለፉት 12 አመታት ያላማቆረጥ በዴንቨር በሚገኝ አንድ ሞል ለ 2 ሰአታት የእግር ጉዞ ያደርጋሉ:: ጡረተኛው የፋርማሲ ባለሙያ የ 104 አመቱ ኢትዮጵያዊ አቶ ሚካኤል የጥሻ ወርቅ ለረዥም ዕድሜና ለሙሉ ጤንነት ሚስጥሩ መራመድ መንቀሳቀስና መጎዝ ነው ይላሉ:: በዴንቨር ቼግሪ ቻጊ የገበያ አዳራሽ ላለፉት 12 አመታት በትንሹ ለ 2 ሰአት ...

Read More »

በሐገር ቤት የሚገኙ የቤ/ክ አባቶች መልካም የሆነውን ነገር በመፈጸም ለቤ/ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲሰሩ አቡነ መርቆርዮስ አሳሰቡ

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እርሳቸውና ከርሳቸው ጋር የሚገኙ ጳጳሳትም ይህንኑ ኃላፊነታቸውንለመወጣት እየሰሩ መሆናቸውን አመለከቱ:: ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት የ2005 ዓ.ም.የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በማስመልከት በጽሁፍ ባሰራጩት መልዕክትነው:: አቡነ መርቆርዮስ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ካከበሩበት ከካናዳ ቶሮንቶባስተላለፉት መልዕክት መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚያግድ ምንምዓይነት ችግር እንደሌለባቸው አመልክተዋል::  ስልጣንና ክብርን እንደማይሹያብራሩት ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ ሆኖም የልዩነቱ ምዕራፍ ተዘግቶ አንድ እረኛያላት አንዲት ቤ/ክ ለትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም አስገንዝበዋል::ሲቀጥሉም “አሁን በኛ በኩል ሕገ-ቤ/ክርስቲያን የሚያስከብርና ቤ/ክርስቲያንንበሰላምና በአንድነት የሚያጸና ሰላም እንዲመጣ ለቤ/ክ ሰላም እና አንድነትቅድሚያ ሰጥተን እየሰራን ነው” ሲሉ አመልክተዋል:: ሰላም የሚመጣው ሁሉም ለሰላም የበኩሉን አስተዋዕጾ ሲያደርግ ነው ያሉትብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ በአገር ላሉት አባቶች ጥሪ አቅርበው በነርሱ በኩልለሰላም ያለውን ዝግጅት አስፍረዋል:: “በኢትዮጵያ ያሉት ወገኖቻችን ሊቃነ ጳጳሳትም ቢያስቡበትና መልካምየሆነውን ነገር ለማድረግ ቢስማሙ ለቤ/ክርስቲያናችን አንድነት ጠቃሚ ነው”በማለት ያስገነዘቡት ፓትሪያርክ መርቆርዮስ “ያ ካልሆነ እግዚአብሔር ባኖረንእየኖርን በአለም የተበተነውን ሕዝባችንን እያጽናናንና እየባረክንየእግዚአብሔርን ቀንና ጊዜ እንጠብቃለን::በኛ በኩል መቼም ቢሆን ከቤ/ክሰላምና አንድነት የምናስቀድመው አንዲት ነገር የለም” በማለት መልዕክታቸውንአስተላልፈዋል::

Read More »

የሕወሃት መሪዎች የመሰረቱት ኩባንያ የሆነውሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተባለ

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) መሪዎች የመሰረቱት ኩባንያ የሆነውሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል በታክስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ተባለ::     ሆኖም ሥራአስኪያጁ ከ13 ቀናት እሥራት ብኃላ ተለቀዋል:: የኢትዮጵያ ገቢዎችጉምሩክ ባለሥልጣን ታክስ ባለመክፈል በሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል እና በስራአስኪያጁ በአቶ ዕቁባይ በርሔ ላይ በመሰረተው ክስ ሥራ አስኪያጁ የሦስትመቶ ሺህ ብር ዋስትና ጠርተው በውጪ ሆነው ሲከራከሩ ቆይተዋል:: የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደት ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት በሕወሐትመሪዎች የተቋቋመው ሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ታክስ ማጭበርበሩ ተረጋግጧልብሎ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማሳለፉ አቶ ዕቁባይ በርሔ ፍርድ  እስኪሰጥ በእስርላይ እንዲቆዮ ተደረገዋል:: ፍ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ጥር 1 ቀን 2005 በ አቶ ዕቁባይ በርሔ ላይ የአራትዓመት ከአምስት ወራት ጽኑ ዕእስራት እንዲሁም በሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ላይየ125 ሺህ ብር ቅጣት ወሥኗል:: ሆኖም ውሳኔው በሁለት ዓመት ገደብ በመታለፉ አቶ ዕቁባይ በርሔ ከእስር ቤትእንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተሰቷል:: በዚህ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት ሜጋ ኪነጥበብ ማዕከልም የ125 ሺህ ብርቅጣቱን አይከፍልም: አቶ ዕቁባይ በርሔም የአራት ዓመት ከ5 ወራት እሥራቱተፈጻሚ አይሆንባችውም:: ቅጣቱ ተፈጻሚ የሚሆነው በሚቀጥሉት ሁለትዓመታት ሌላ ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ ብቻ መሆኑን ከሕግ ባለሙያዎችማብራሪያ

Read More »

ሰበር ዜና:-በትግራይ ክልል በአላማጣ ወረዳ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው

ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል በአላማጣ ወረዳ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው:: ህዝቡ የመኪና መንገዶችን በመዝጋቱ መኪኖች ከጧት ጀምረው እንደቆሙ ናቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት ከህዝቡ ጋር ተፋጠዋል ተማሪዎች ትምህርት አቁመው የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው:: በምሽቱ የዜና ሰዓት ዝርዝር ዜና ይኖረናል::

Read More »

የFBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ – በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን አንድ የአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (FBI) ግበረሃል ባለፈው ወር መባቻ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ወደ ቦስተን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተጓዘበት ወቅት የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በመዶለትና በማስተባበር ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረና ለህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሰልል የሚጠረጠር ግለሰብ እና በግብረአበሮቹ ላይ ከፍተኛ ምርመራ መክፈቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጡ። በአሜሪካ ሀገር የፖለቲካ ጥገኝነት ...

Read More »

በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ብዙ ተማሪዎች መደብደባቸውና መታሰራቸው ታውቀ

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታህሳስ 29 ቀን 2005 ዓም  በእራት ሰአት ላይ በድሬዳዊ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተን ረብሻ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥራቸው የበዛ ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎችን ደግሞ ይዘው አስረዋል። እስከ ምሽት የዘለቀውን ይህንኑ የፖሊሶች  ድብደባ መቋቋም ያቃታቸው ተማሪዎች በምሽት  ግቢያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን  ያመለከተው ዘጋቢያችን፤   የሚያድሩበት ቦታ  በማጣታቸው በቤተክርስቲያኖች እና ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ወደ መስጊድ ሄደው ...

Read More »

‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ብቻ ነኝ››ሲል የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አንዷለም አራጌ ገለጸ

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንዷለም ይህን ያለው፤የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲጠይቁት የተፈቀደላቸው የ አንድነት አመራሮች በቃሊቲ ተገኝተው በጎበኙት ጊዜ ነው።   ወጣቱ ፖለቲከኛ በዚሁ ጊዜ ቃሊቲ ለተገኙት  የአንድነት አመራሮች ፦”በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”በማለት ህያው ራዕዩንና ውስጣዊ ምኞቱን ገልጾላቸዋል።   ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ተመስጌን ዘውዴ፣ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፣ ...

Read More »

የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

ታህሳስ  ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ርእዮት ዛሬ ሰበር ሰሚ ችሎት ባትቀርብም ጠበቃዋ፣ አባቷ እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቿና ጓደኞቿ በችሎቱ ተገኝተው ውሳኔውን ሰምተዋል። ሰበር ሰሚ ችሎቱ በርእዮት የቀረበው አቤቱታ የህግ ክፍተት የለበትም ሲል ውሳኔ አሳልፎአል። ጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት ጥር 17 ቀን 2004 ዓም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት የ14 አመት ጽኑ እስራትና የ33 ሺ ብር ቅጣት እንደተወሰነባት ይታወሳል። ...

Read More »