ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሚስጥር የደረሰን በአዲስ አበባ የኢህአዴግ ድርጅት ጽህፈት ቤት ያዘጋጀው ሚስጢራዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የኢህአዴግ አባላት ከመለስ ሌጋሲ እና ከልማት ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ተመልክቷል። የኢህአዴግ አባላት ካነሱዋቸው ሀሳቦች መካከል ” መስመሩን ያላወቁ አባላት ባለበት እንዴት ሌጋሲውን ማስቀጠል ይቻላል? አባሎች ራሳቸው ጀርባቸው መጠናት አለበት፣ ንፋስ ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ ቁጥራቸው እየበዛ ነው፣ የመለስ ሌጋሲ ሊኖር ...
Read More »በ አዲስ አበባ የወላይታ ተወላጆች እየታፈሱ ነው
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በተለያዩ ጥቃቅን የንግድ ሥራዎች ተሰማርተው የሚገኙ የወላይታ ተወላጆች”ወደ አካባቢያችሁ ትመለሳላችሁ”ተብለው ታፍሰው መታሰራቸውን ፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሯቸውን ለማሸነፍ ሲሉ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሊስትሮነትና በሌሎች ጥቃቅን ንግዶች ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የወላይታ ተወላጆች “የጸጥታ ስጋት ናቸው”ተብለው በፌዴራል ፖሊስ ታፍሰው ታስረዋል። እንደ ወኪላችን መረጃ በትናንትናው ዕለት ብቻ 130 የወላይታ ተወላጆች አራት ኪሎ ...
Read More »የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ጉባኤ ተደናቀፈ
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሊያካሂዱት የነበረው አመታዊ ጉባኤ ገዢው ፓርቲ አስርጎ ባስገባቸው ወጣቶች መደናቀፉን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎች ለማህበሩ አዳራሽ ለማከራየት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶቹ ጉባኤያቸውን በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ለማካሄድ ተገደው ነበር። ይሁን እንጅ ዛሬ ጧት ስብሰባው በሚካሄድበት ወቅት የተወሰኑ ወጣቶች ስብሰባውን ማደናቀፋቸውንና ይህንኑ ተከትሎ የፌደራል ...
Read More »ሱሪዎች ዛሬ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር ሲዋጉ መዋላቸው ታወቀ
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከስፍራው የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሱሪዎችን የቤት እንስሶቻቸውን በመውሰድ የአካባቢውን ህዝብ በግድ ወደ ሰፈራ ጣቢያ ለማንቀሳቀስ ባደረጉት ሙከራ ነው ዲማ በሚባለው አካባቢ የተኩስ ልውውጥ የተደረገው። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ለማወቅ አልተቻለም። ኢሳት ባለፈው ሳምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ150 በላይ ሱሪዎች መገደላቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
Read More »አዲስ አበባ በህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች እየተናጠች ነው
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ አዲስ አድማስ ዘገባ፤ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ፖሊሶችና ነጋዴዎች የአነቃቂ እፆች ተጠቃሚ ናቸው ተባለ በአዲስ አበባ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ቤቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ መምጣታቸውንና ከተማዋ አደጋ ላይ እንደሆነች ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ጥናት “መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ላይ እያስከተሉት ...
Read More »ኢትዮቴልኮም በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እየገባ መሆኑ ታወቀ
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባወጣው ጥናት እንዳመለከተው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ኢትዮ ቴልኮምን ከነጻ ኩባንያነት አውጥቶ የአንድ ብሄር መሰባሰቢያና የስለላ ተቋም አድርጎታል። በድርጅቱ ውስጥ ኤን አንድና ኤን ሁለት የሚባሉ ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች መኖራቸውን ያስታወሰው ጥናቱ ፣ በኤን አንድና ሁለት የተመ =ደቡትን በማኔጅመንት ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ፈረንሳዮችን የሚያጠቃልል ነው። በኤን አንድና በኤን ...
Read More »4 አመት የተፈረደባቸው የሜጋው ባለስልጣን በሳምንቱ ከእስር ተፈቱ
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በሜጋ ኪነጥበባት ኀ/የተ/ግ/ማ እና በቀድሞ ስራአስኪያጁ አቶ ዕቁባይ በርሄ ላይ በመሰረተው ክስ መሰረት አቶ ዕቁባይ አራት ዓመት ከአምስት ወራት ቅጣት ከተላለፈባቸው በኋላ ቅጣቱ በገደብ ተደርጎላቸው ተለቀዋል። የባለስልጣኑ መለቀቅ የፍትህ ሥርዓቱ አድሎአዊነት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለጸዋል፡፡ የባለስልጣኑ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ መሰረት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አስረኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመለከት ...
Read More »በአለማጣ ከታሰሩት መካከል የተወሰኑት ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከ 20 ያላነሱ ሰዎች ታስረው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አብዛኞቹ ወጣቶች ወደ ማይጨው እስር ቤት ተወስደው መታሰራቸው ታውቋል። ከታሰሩት መካከል አቶ አባተ ያለው እስከ ልጃቸው፣ አቶ አሰፋ ዳርጎ ከሴት ልጃቸው ጋር ፣ ሽበሺ አለሙ፣ አሰፋ አሰግድ ፣ ውዱ ቸኮል፣ አቶ ዝናቡ ቸኮል ከሴት ልጃቸው ጋር እንዲሁም አቶ ...
Read More »ቴዲ አፍሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ለመስጠት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያመራ ነው
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሙዚቃው ለማነቃቃትና ለመደገፍ በመጪው ቅዳሜ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ ቢቢሲ ዘገበ። ከአርቲስቱ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረገው ቢቢሲ ፊከስ ኦን አፍሪካ፤ ቴዲ አፍሮን፦ “የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ልጅ የሆነ ድንቅ የፖፕ ስታር ሙዚቀኛ” ብሎታል። ቀደም ሲል ባለለፈው የእስር ጊዜ እና በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ...
Read More »በኦስትሪያ ዜጋ ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው ከተረጠሩት መካከል ሁለቱ መያዛቸውን መንግስት አስታወቀ
ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው ተጠርጣሪዎቹ በአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። ወንጀሉ ተራ የዘረፋ ሙከራ መሆኑን መንግስት ይናገራል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ድርጊቱን መፈጸማቸውን ይናገራሉ። የሟቹ አስከሬን ከትናንት በስቲያ ወደ ሀገሩ መላኩ ታውቋል።
Read More »