የሶማሊ ክልል ለመከላከያ አዛዦች አዛዦች የመክበሪያ ቦታ መሆኗን ምንጮች አስታወቁ

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ ከፍተኛ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የህወሀት  ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች ወደ ሶማሊ ክልል ሲመዱ  ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ሀብት አጋብሰው እንደሚመለሱ ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ተቀማጭነታቸው ጅጅጋ የሆኑት እና በክልሉ ቁጥር አንድ ሀብታም የሚባሉት /ወ/ት ሀዋ የሌተናንት ጄኔራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ሁለተኛ ሚስትና የልጅ እናት ሲሆኑ፣ ግለሰቧ ከተራ ጫት ነጋዴነት በአንድ ጊዜ ...

Read More »

የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች የዋስትና መብት ተከለከሉ

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በከፍተኛው ፍርድ ቤት ታስረው ከተለቀቁ በሁዋላ ተመልሰው እንዲታሰሩ የተደረጉት የቁጫ ወረዳ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ተመልሰው በአርባምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ መደረጉን ከሽማግሌዎች አንዱ ገልጸዋል። ችግሩን ለፌደራል መንግስት አቤት ለማለት እስከዛሬ ሲመላለሱ የቆዩት የአገር ሽማግሌዎች አንድም ባለስልጣን ሳያገኙ በመቅረት ነገ ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው ፍርድ ቤት እንደሚቆሙና እንደ ጓደኞቻቸው የዋስትና መብታቸው ተገፎ እስር ቤት እንደሚገቡ ...

Read More »

የቦንጋ አስተዳዳሪ ከመምህራን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ

ህዳር ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው የአንድ ወር ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የቦንጋ መምህራን፣ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ካስታወቁ በሁዋላ፣ ዋና አስተዳዳሪው ማከስኞ ከመምህራን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቛል። ከመምህራን ተወካዮች ጋር የተነጋገሩት ባለስልጣኑ፣ ስምምነት ለመድረስ ባለመቻላቸው ከመላው መምህራን ጋር ለመነጋገር ወስነዋል። መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ መልሶ የማይሰጣቸው ከሆነ በአድማው ለመቀጠል እየተናገሩ ነው።

Read More »

በማንዴላ ሞት አለም ሀዘኑን እየገለጸ ነው

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደቡብ አፍሪካውያን ለነፃነት አባታቸውና ለቀድሞ መሪያቸው ለኔልሰን ማንዴላ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ወደ ጁሀንስበርግበና ሶዌቶ እየተሰበሰቡ ሲሆን፤ ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችም በማንዴላ ሞት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በስዌቶ በሚገኘው በቀድሞው የኔልሰን ማንዴላ መኖሪያ ቤት በመሰባሰብ በባህላዊ ስርአታቸው መሰረት በልዩ ልዩ የብሔረሰቦች የሀዘን ጭፈራ  ለመሪያቸው ያላቸውን አክብሮች እየገለፁ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። የተለያዩ የዓለማችን ...

Read More »

የቁጫ ነዋሪዎች መኖር አልቻልንም ሲሉ ምሬታቸውን ገለጹ

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እያደረሱባቸውን ያለውን ስቃይ ለማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢገኙም የሚያነጋግራቸው አጥተው ተመልሰዋል። አገር ሽማግሌዎቹ ጉዳያቸውን ለጠ/ሚንስተሩ ለማምልከት በተደጋጋሚ ወደ ...

Read More »

በቦንጋ መምህራን አድማ ሊጠሩ ነው

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል ደሞዛቸው ተቆርጦ ተሰጥቷቸዋል። በሁኔታው የተበሳጩት መምህራን ወደ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያመሩ መስተዳድሩ ያዘዘው በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። ...

Read More »

በ2006 ዓ.ም ከስድስት ሚልየን በላይ ህፃናት ትምህርት አቋረጡ

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው መማር ከሚገባቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሀፃናት ውስጥ 23 በመቶዎቹ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው ሰነድ ያስረዳል። ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የሚያሳያየው ሰነዱ፣ከ5ኛ አስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ገብተው መማር የነበረባቸው ተማሪዎች   ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም  ያመለክታል ፡፡ በዚህ ዓመት መድረስ ...

Read More »

ከሳውድ አረቢያ ከሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የመንግስት እንቅስቃሴ እየተተቸ ነው

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም ወገኖች ለመመለስ መመዝገባቸውን በመግለጽ ለተመላሾቹ ...

Read More »

ጅጅጋ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ናት

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ  አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ ሜትሮች ቁጥጥር እያደረጉ ነው። የጸጥታ ጥበቃው በሄሊኮፕተር ላይ በሚደረግ ቅኝት የታጀበ ሲሆን፣ በየ አቅጣጫውም በዙ 23 እና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጥበቃ እየተደረገ ...

Read More »

የመርካቶ ነጋዴዎች በእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ ክስ ሊመሰርቱ ነው

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀትር በኃላ የደረሰውን የእሳት አደጋ በወቅቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ጉቦ ለማግኘት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በድርድር ጊዜ በማጥፋታቸው ንብረታችንን እንድናጣ አድርጎናል ያሉ ነጋዴዎች የአዲስአበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲን ለመክሰስ መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡ ከተጎጂ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገሩት እሳት አደጋው በግምት ከቀኑ ...

Read More »