የቦንጋ አስተዳዳሪ ከመምህራን ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ

ህዳር (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው የአንድ ወር ደሞዛቸው የተቆረጠባቸው የቦንጋ መምህራን፣ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ካስታወቁ በሁዋላ፣ ዋና አስተዳዳሪው ማከስኞ ከመምህራን ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ታውቛል።

ከመምህራን ተወካዮች ጋር የተነጋገሩት ባለስልጣኑ፣ ስምምነት ለመድረስ ባለመቻላቸው ከመላው መምህራን ጋር ለመነጋገር ወስነዋል። መምህራን የተቆረጠባቸው ደሞዝ መልሶ የማይሰጣቸው ከሆነ በአድማው ለመቀጠል እየተናገሩ ነው።