የአማራ ክልል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸል ብለው የሚጠረጥሩትን ሁሉ እንዲይዙ ታዘዙ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ወር በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህርዳር የተካሄደውን የብአዴን እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዞን እና የወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊዎች ኢህአዴግ አሸባሪ እያለ ከሚጠራቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ በሚጠረጠሩት ወጣቶች ላይ  የቁጥጥር ዘመቻ እንዲካሄዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል። ጥር 8፣ 2006 ዓም በሁሉም የአማራ ...

Read More »

በደቡብ ክልል 60 አቃቢ ህጎች ከስራ መባረራቸው ተሰማ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቃቢ ህጎቹ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ መባረራቸው ተግልጿል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እንደገለጹት ከ100 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ የተለያዩ የዲሲፒሊን እርምጃዎችን ወስደዋል። ከ40 በላይ በሚሆኑ የእስር ቤቶች ሃላፊዎች ላይም እንዲሁ የዲሲፒሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን 10 ከስራ ተባረዋል። ጉቦ መቀበል፣ ወገናዊነት፣ ፍትህ ማዛባት እንዲሁም እስረኞችን እየፈቱ መልቀቅ ከዋና ዋና ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። የኢሳት የደቡብ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት አላሳየም

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት እና በአማጽያን መካከል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ድርድር እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሁለቱም ሀይሎች በሚያቀርቡዋቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስካሁን ውጤት አለመገኘቱ ታወቀ። አማጽያኑ የታሰሩት ባልደረቦቻቸው እንዲፈቱ፣ የዩጋንዳ ጦር አገሪቱን ለቆ እንዲወጣና የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያበቃ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል ደግሞ በአማጽያኑ የቀረቡትን በተለይም እስረኞችን መፍታት የሚለውን ቅድመ ሁኔታ አልተቀበለውም። ነገሮች እየባሱ ሄደው ...

Read More »

በሶማሊያ ክልል 47 ሰዎች መገደላቸውን የአገር ሽማግሌዎች ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በላኩት ደብዳቤ ገለጹ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ የየረር ባሬ ጎሳ  የአገር ሽማግሌዎች ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያስገቡትና መረጃው ለኢሳት እንዲደርስ በሚል በላኩት መረጃ ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር እና ጄኔራል አብርሀም በቅጽል ስማቸው ኳታር የሚመራው ልዩ ሚሊሺያ እየተባለ የሚጠራው ሀይል ታህሳስ 1 እና 2 በከፈተው ተኩስ በትምህርት ላይ የነበሩ ህጻናትንና ወጣቶችን ጨምሮ 47 ሰዎችን ...

Read More »

የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ጸደቀ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተሞች ሥር የሰደደውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል የተባለ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ፡፡ አዋጁ በተበታተነና በልማዊ መንገድ ሲካሄድ የነበረውን የመሬት ባለቤትነት ይዞታ አሰራርን በዘመናዊ መልኩ እንዲካሄድ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የህዝቦችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ተብሎአል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት ይፋዊ ምዝገባ ከመነሻው መሰረቱ የከተማ ቁራሽ መሬት ...

Read More »

በ3 ዓመታት ውስጥ ወደ አረብ አገራት የሚደረገው ስደት በእጅጉ መጨመሩ ተነገረ

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወደዓረብ አገራት ዜጎች የሚያደርጉት ጉዞ ከ2003 ዓ.ም በኋላ በአስደንጋጭ መልኩ ከ4ሺህ ወደ 198 ሺህ ማደጉን ዶ/ር ዘሪሁን ከበደ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ይፋ አደረጉ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ለንባብ በበቃው “ዘመን” ከተባለው መንግስታዊ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ በ2002 ዓ.ም ሚኒስቴር መ/ቤቱ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት አጥንቶ ተግባራዊ ሲደርግ ከ3-5 ሺህ ሰዎች በዓመት ሊጓዙ ...

Read More »

ከኢሳት ጋር በተያያዘ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተወዛገቡ ነው

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ ሆነው የሚቦረቡሩ ሃይሎች አሉ በማለት እርስበርስ መወዛገባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ በረከት ለሚኒስትሮችና ለኢህአዴግ  ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ንግግር በኢሳት ከተለቀቀ በሁዋላ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። የኢህአዴግ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ውስጣችን ማጥራት አለብን በሚል ትናንትና ዛሬ ለአመራሮች ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ውለዋል። ኢሳት ...

Read More »

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በባህር ዳር ሊካሄድ ነው

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥር 16-18 ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮች ስብሰባ  የአማራ ክልል ም/ቤት በቻይና ድጋፍ ባሰራው አዲስ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡ ህብረቱ አፍሪካ በ2063 ስለምትከተለው አቅጣጫ ይነጋገራል ተብሎአል። የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ስብሰባ ሲያዘጋጅ  የመጀመሪያው ይሆናል።

Read More »

አርሶ አደሩን እንደፈለገ ብናደርገው በኢህአዴግ ላይ አይነሳም ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ ይሸከመዋል” ብለዋል። 30 በመቶ የሚሆነውን ...

Read More »

ኢትዮጵያ በአለም የምግብ እጥረትና ባልተመጣጠነ ምግብ የመጨረሻውን ደረጃ ያዘች

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦክስፋምን ጥናት መነሻ በማድረግ ረዩተርስ እንደዘገበው በምግብ አቅርቦት፣ በምግብ ጥራትና በምግብ ዋጋ ኢትዮጵያ ከ125 አገራት ከቻድ በመቀጠል የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። በአለም ላይ የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ፣ በምግብ ዋጋና በጥራት ሆላንድ አንደኛ ሆና ስትመረጥ ፈረንሳይና ስዊዝርላንድ ይከተላሉ። አሜሪካ 21ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአንድ እስከ 10 ያሉትን ደረጃዎች የአውሮፓ አገራት ይዘውታል። የኦክስፋም ጥናት ላለፉት 23 አመታት ኢትዮጵያን ...

Read More »