የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በሚካሄደው ድርድር በቅርቡ ከእስር የተፈቱት 7ቱ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳታፊዎች ሆነዋል። ይሁን እንጅ ባለስልጣኖቹ ከሁለቱም ወገኖች ሳይሆኑ በገለልተኛነት በድርደሩ ላይ መገኘታቸውን ተናግረዋል። ገለልተኝነትን የመረጡበትም ምክንያት ሲናገሩ ደግሞ የጦር መሳሪያ የለንም የሚል ነው። የሳልቫኪር መንግስት ባለስልጣኖችን ያሰረው ከተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ነበር። በሌላ በኩል ዩጋንዳ ጦሩዋን ከደቡብ ...
Read More »በርካታ የየረር ጎሳ አባላት የአገር ሽማግሌዎች ታሰሩ
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በቀላፎ አካባቢ የሚኖሩ 19 የየረር ባሬ ጎሳ የአገር ሽማግሌዎች በክልሉ ውስጥ የተፈጸመውን ከፍተኛ እልቂት ለጠ/ሚንስትሩ አቤት ለማለት ወደ አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት አካባቢውን በሚጠብቁ ልዩ ሃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከእስር ያመለጡ አንዳንድ ሽማግሌዎች በትናንትናው እለት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከዚህ ቀደም በልዩ ሚሊሺው በቀጥታ የተገደሉትን የ47 ሰዎች ...
Read More »በሀገረ-ማርያም የተፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮሚያ ክልል በቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በሀገረማርያም ከተማ ከአርሴማ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በሁዋላ ህዝቡ ባሰማው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገር ሽማግሌዎቹ በዛሬው እለት የተፈቱ ሲሆን፣ ህዝቡ በድል አድራጊነት ስሜት በሆታ አጅቦ ወደ ቤተክርስቲያን ወስዷቸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ ትናንት ረቡእ እንዲፈቱ ...
Read More »በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር በሌላ ጊዜ ...
Read More »የአዲስ አበባ እድሮች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በድጋሜ መዋጮ እንዲያዋጡ ታዘዙ
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቲት 2፣ 2006 ዓም ከእድር ተጠሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እያንዳንዱ እድር በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ እንዲከፍል ታዟል። ትእዛዙ የተጣለው የካቲት 2 ቀም 2006 ሲሆን፣ 650 እድሮች በነፍስ ወከፍ 8 ሺ ብር ይከፋላሉ። በዚሁ ከላይ በወረደው መመሪያ መንግስት ከእድሮች በአንድ ጊዜ 5 ሚሊዮን 200 ሺ ብር ...
Read More »በኢሳት ጋዜጠኞች ኮምፒዩተሮች ላይ የሚካሄደው ስለላ እንደቀጠለ ነው
የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና የኢሳት የኮምፒዩተር ባለሙያ በሆነው ተቀማጭነቱ ቤልጂየም በሆነው የኢሳት ባልደረባ ላይ የተገኙ ባእድ የመሰላያ ሶፍትዌሮች ከጣሊያኑ ሃኪንግ ቲም የተላኩ መሆናቸውን ሲትዝን ላብን በመጥቀስ ታዋቂው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ጋዜጣው ባወጣው ሰፊ ዘገባ መረጃዎችን ከኮምፒዩተሮች ላይ ለመውሰድ የሚያስፈልገው ባእድ ሶፍትዌር የተላከው ከጣሊያን ኩባንያ ጋር ቢሆንም፣ ኩባንያው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነት ...
Read More »በሀገረ-ማርያም ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች ታሰሩ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአርሴማ ቤተክርስቲያን የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረዋል። በህዝቡ የተመረጡት 15ቱ ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍታት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የቀጠናው ሃላፊ የሆኑት አቡነ ገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባላቱ እንዲበተኑና ችግሩን ለመፍታት እንደሚሞክሩ መግለጻቸው ህዝቡን አስቆጥቷል። ጳጳሱ ለፌደራል ፖሊሶች በማመልከት የአገር ሽማግሌዎች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ዛሬ ጳጳሱ ወደ አካባቢው በመሄድ ...
Read More »የብአዴን ዋና ጸሃፊ ቤት በፖሊሶች እየተጠበቀ ነው
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ተወላጆች ላይ በጅምላ ፀያፍ ስድብ የሰነዘሩት የብአዴኑ አመራር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የ አቶ ኣለምነው መኮነን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን፣ ዜናውን ተከትሎ ኢሳት ባደረገው ማጣራት የባለስልጣኑ መኖሪያ ቤት በ11 ፖሊሶች ሌትና ቀን እየተጠበቀ ነው። አቶ አለምነው የአማራው ህዝብ የትምክህት ለሃጩን በማራገፍ ከሌላው ህዝብ ጋር ለመኖር ...
Read More »የጋዜጠኛው ጥያቄ ጠ/ሚኒስትሩን አስቆጣ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡ አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጋዜጠኛውን ሂድና ...
Read More »በኦሮምያ ማንኛውም የፍርድ ቤት ጉዳይ በኮምፒዩተር ተጽፎ እንዲቀርብ ታዘዘ
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የፍትህ ቢሮ በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ ማንኛውም ባለጉዳይ አቤቱታዎችን በኮምፒዩተር ካላስጻፈ ጉዳዩ እንዳይታይለት ወስኗል። በክልሉ የሚገኙ ዳኞች በበኩላቸው ውሳኔው የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የእድገት ደረጃ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ይላል። ዳኞች እንደሚሉት አብዛኛው ህዝብ አቤቱታዎችን አስጽፎ የሚያቀርበው በወረቀትና በእስክር ቢቶ ሆኖ ሳለ፣ የድሆችን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ ሳያስገቡ፣ ...
Read More »