በሱዳን ጎረምሶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በአንድ ወር ተቀጣች።

የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድንጋይ ተወግራ ልትገደል ትችላለች በማለት የእንግሊዙ ዘ ጋርድያንና ኢንዲፕንደት የተባሉት ጋዜጦች ቢዘግቡም፣ የሱዳን ፍርድ ቤት ወጣቱዋን በአንድ ወር ብቻ ቀጥቷታል። ይሁን እንጅ ነፍሰጡር በመሆኗ ከእስር ነጻ ሆና ወደ አገሩዋ እንድትመለስ እና 4 ሺ የሱዳን ፓውንድ እንድትከፍል መወሰኑዋን ቢቢሲ ዘገበ። ከልጅቷ ጋር ጾታዊ ግንኙነት የፈጸሙት 3ቱ ወጣቶች 100 ጊዜ እንዲገረፉ፣ ፊልሙን በመቅረጽ ...

Read More »

አልሸባብ በሱማሌው ፕሬዚዳንት ግቢ ውስጥ ጥቃት ፈጸመ

የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቱ የሶማሊ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች ሲገደሉ ፕሬዚዳንቱና ጠ/ሚንስትሩ መትረፋቸው ታውቋል። አልሸባብ በፕሬዚዳንቱ ግቢ ውስጥ ወታደሮቹ እንደሚገኙ ቢገልጽም የሶማሊያ መንግስት ግን ሁሉም የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገድለዋል ብሎአል። አልሸባብ ከሞቃዲሾ ለቆ ቢወጣም በከተማዋ ውስት የሚፈጽመውን ጥቃት አላቆመም።

Read More »

የብአዴን ድንጋጤና የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ  የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው። የካቲት 16  አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማ ባሉ ዘጠኝ ክፍለ ...

Read More »

ረዳት ፓይለት ሃይለ-መድህን አበራ ብቃት ያለው አብራሪ ነው ተባለ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አውሮፕላን  በመጥለፍ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ፣ ከጸባዩ በተጨማሪ ብቃት ያለው አብራሪ መሆኑን ግለሰቡን የሚያውቁ ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል። ከስልጠና ጀምሮ የሚያውቁት ጓደኞቹ እንደተናገሩት ሃይለመድህን ለሰዎች ህይወት የሚጨነቅና ጥንቃቄ የሚያደርግ፣ አውሮፕላኑን ከጠለፈ በሁዋላ ተሳፋሪዎች ሳይቸገሩ እንዲያርፍ ማድረጉ የፓይለቱን ብቃት ያሳያል ብለዋል። ምንም እንኳ በረዳት አብራሪነት ደረጃ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ አባላት በአያያዛቸው ላይ ቅሬታቸውን አሰሙ።

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባላቱ ቅሬታቸውን የሰነዘሩት በ2ኛው የመከላከያ ሰራዊት በአል ላይ ነው። በቀን አንድ ዳቦ እና ሁለት ጭልፋ ወጥ ለእራትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሚቀርብላቸው የመከላከያ ስራዊት አባላት፣  የቀን የምግብ ፍጆታ በጀታቸው ከህግ ታራሚዎች ያነሰ ነው። ወታደሮቹ  በቀን ስምንት ብር ከሃምሳ ሳንቲም በሆነ የምግብ በጅትየሚተዳደሩ ሲሆን፣ የሚቀርብላቸውን ዳቦ እንኳን  ለመብላት እንደሚቼገሩ እና ለምግብ እየተባለ በየወሩ ከደሞዛቸው ...

Read More »

በሱዳን በጎረምሶች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት በድንጋይ ተወግራ ልትገደል ትችላለች ተባለ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋርድያን እንደዘገበው የ18 አመቷ ወጣትና ነፍሰጡሩዋ ኢትዮጵያዊት በዝሙት ተግባር በመከሰሷ በድንጋይ ተወግራ ልትገደል እንደምትችል የምስራቅ አፍሪካ የሴቶች ስትራቴጂክ ኔትወርክ ወይም ሲሃ የተባለውን ድርጅት በመጥቀስ ዘግቧል። የ9 ወር ነፍሰ ጡሩዋ ወጣት በእስር ቤት ውስጥ ያለምንም ምንጣፍ በባዶ ኮንክሪት ላይ እንደምትተኛ ጋዜጣው ዘግቧል። ኢሳት ከወር በፊት ዜናውን ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ያለው አለመረጋጋት እንደ ቀጠለ ነው።

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማጺው መሪ ሪክ ማቻር እና በ ፕሬዚዳንት ሳል ቫኬር ያለው ልዮነት እየስፋ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ:: ከትላንት በስትያ በነዳጅ የበለጸገችው የአፐር ናይል ስቴት ዋና ከተማ ማላካል  ከባድ ጦርነት ተካሂዷል። ወደ ማላካል የሚደረጉ  የአየር በረራዎችች መሰረዛቸውንና አካባቢው በከባድ ጦርነት ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎል:: ማላካል የተባለው ቦታ ጠንካራ ስትራቴጅክ ቦታ ሲሆን ይህን ...

Read More »

በጠለፋው ዙሪያ ልዩ ጥንቅር

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካፒቴን ሃይለመድህን አበራ የጠለፋ ምክንያት  በአየር መንገዱ ውስጥ የሚታየውን የአስተዳደር መበላሸት ለአለም ለማሳየት ነው  ይችላል የሚለው ምክንያት አሳማኝ ነው ሲሉ አንድ የቀድሞው የድርጅቱ ሰራተኛ ገለጹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ  በበረራ ደህንነት ስራ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገለውና በክትትልና ደህንነት ስጋት ከአመት በፊት ድርጅቱን ለቆ በስዊዘርላንድ ጥገኝነት የጠየቀው ሚካኤል መላኩ ከኢሳት ጋር ባደረገው  ሰፊ ...

Read More »

77ኛው የኢትዮጵያ ሰማእታት ቀን ተከብሮ ዋለ

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወራሪ ሃይል በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተዘከረ ነው። በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰምአታት ሃውልት ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት በአሉ ተከብሯል። የካቲት 12፣ 1929 ዓም አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ኢትዮጵያውያን ግራዚያኒን ለመግደል የጣሉትን ቦንብ ተከትሎ፣ የጣሊያን ወራሪ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ  ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውን መገደላቸው ...

Read More »

ከአርብ ሃገራት የተመለሱ ኢትዩጵያውያን ለዘርፈ ብዙ ችግር መጋለጣቸው ተገለፀ፡፡

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዕምሮ ቸግር ፤ ዘገምተኝነት ፤ ሱስ ፤ ራስን መጣል ፤ የስነ ልቦና ችግር ፤ድብርት ፤ ከሰው መገለል፤ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን ማጥፋት ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች፤ አሰገድዶ መደፈር ችግር የጣላባቸው ጠባሳ በህይወታቸው ላይ ከባድ ተጽኖ ሁኖ ይሰተዋልባቸዋል ሲል የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስጠናው ጥናት አመልክቷል፡፡ ከአርባ ሃገራት ሰደተኛቸ ተመላሺ ኢትዩጵያውያን የኢትዩጵያን ...

Read More »