የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰዊስ አቃቢ ህግ ቃል አቀባይ ሚስ ያኔት ባልመር በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙሪያ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ የምርመራ ሂደቱ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ገልጸው፣ የሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በኩል ለተነሳው ጥያቄ ግን ስዊዘርላንድ የሰብአዊ መብቶችን በጠበቅ በኩል ታዋቂ አገር መሆኑዋን በመግለጽ የሃይለመድህንን የሰብአዊ መብቶች እንደሚያከብሩ ገልጸዋል። ሃይለመድህን ጠበቃ ተቀጥሮለት ጉዳዩን ...
Read More »ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ በአባይ ግድብ ግንባታ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ሪፖርተር ዘገበ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጣው በእሁድ እትሙ እንደገለጸው ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ ” በህዳሴው ግድብ ላይ 60 ከመቶውን የትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክና አፈር የማንሳት ሥራዎችን ከሳሊኒ በተቋራጭነት በመውሰድ እየሠራ እንደሚገኝም ባለፈው አመት ኩባንያው በቀድሞው ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ መመስረቱን ፣ በግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ...
Read More »በአርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ አባላት ከስራ ተባረሩ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው አባላት በመንግስት ስራ ውስጥ ድርሻ አይኖራችሁም ተብለው መባረራቸውን የተባረሩ የፓርቲው አባላት ለኢሳት ገልጸዋል። አብዛኞቹ ለሱዳን እየተሰጠ ያለውን መሬት በተመለከተ ተቃውሞ በማሰማታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል። የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ አንጋው ተገኝ፣ በድንበር ጉዳይ ጥያቄ በማንሳታቸው መባረራቸውን ገልጸዋል ከተባረሩት የፓርቲው አባላት መካከል አወቀ ብርሃኑ፣ አባይ ዘውዱ ፣ አንጋው ተገኝ፣ አብርሃም ...
Read More »መንግስት ኢማሞችን በመሾም በኩል ጣልቃ መግባቱን የሚያሳይ መረጃ ይፋ ተደረገ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማህበራዊ ድረገጾች የተለቀቀው ይህ መረጃ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ አበባ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበ ነው። ወንጀል ዝርዝር በሚለው ክፍል ውስጥ ” 2ኛ ተከሳሽ መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም፣ ሳይፈቀድለት የነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊ ሙስሊም እንዳይሰገድ በማድረግና መስኪዱ በመታወቁ በወና ወንጀል አድራጊነት ተከሷል” ይላል ምንም እንኳ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ...
Read More »“የባህርዳር ህዝብ አንግቦ የተነሳው በአገሪቱ እየጨመረ የመጣውን የለውጥ ጥያቄ ነው” ሲሉ ነዋሪዎች ገለጹ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ28 አመቱ ሙላት የመሸንቲ ነዋሪ ነው፤ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘሁት በአገዛዙ ተማርሬ ነው ይላል። ለምን ተማረርክ በማለት ዘጋቢያችን ላቀረበችለት ጥያቄ፣ “ምን የማያስመርር ነገር አለ፣ ሁሉም ነገር እየተበላሸ እንጅ እየተሻሻለ ሲሄድ አታይም፣ ይህም አልበቃ ብሎ ይዘልፉናል” በማለት በሰልፉ ላይ የተገኘበትን ምክንያት ገልጿል። የባህርዳር ነዋሪዎች አንድነትና መኢአድ በጋራ በጠሩት ሰልፍ ላይ በነቂስ ወጥተዋል። ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል ከስልጣን የለቀቁትን ፕሬዚዳንቱን ለማሳከም ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱ ታወቀ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፉትን ሶስት የሥልጣን አመታት በህክምና ያሳለፉትና ከሳምንት በፊት በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው የተሰናበቱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለማሳከም ክልሉ ከአንድ ሚሊየን አሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉ ተሰማ፡፡ በጰጉሜ ወር 2002 ዓ.ም ኦህዴድ ባካሄደው ጉባዔ ባልተጠበቀ መንገድ አቶ አባዱላ ገመዳን ተክተው ወደስልጣን የመጡት አቶ አለማየሁ በስራ ገበታቸው ላይ ብዙም ሳይሰነበቱ በመታመማቸው ...
Read More »አቶ ካሃሰ ወ/ማርያም የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም በከንቲባ ድሪባ ኩማ ፊርማ ተጽፎ በወጣው ደብዳቤ አቶ ካሓሰ ወ/ማርያም ከየካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር በቢሮና በኃላፊ ደረጃ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል። “የተለያየ መ/ቤት ስያሜ እያወጡ እና ለህዝቡ ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተቋማትን ...
Read More »በኒውዚላንድ የኢሳትን የኔነው ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈዉ ቅዳሜ የካቲት 15፣ 2006 ዓም በ ኒዉዚላንድ አገር በኦክላንድ ከተማ ተዘጋጅቶ የነበረዉ የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በሂደቱ በርካታ ችግሮች ተጋርጠውበት የነበረ ቢሆንም፣ ለአገራቸዉ ነፃ መዉጣትና ኢሳትን አሁን ካለበት እጥፍ አድጎ ማየት በሚፈልጉ ቀናኢ ኢትዮጵያዉያን ጥረት የገንዘብ ማሰባሰቡ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስተባባሪዎች ገልጸዋል። በርካታ ኢትዮጵያን የነበረዉን መሰናክል ...
Read More »መኢአድና አንድነት በጋራ የጠሩት የባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄ ነው ሲሉ አስተባባሪዎች ገለጹ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የመኢአድ ሰሜን ቀጠና አደራጅና የተቃውሞ ሰልፉ ግብረሃይል ለኢሳት እንደገለጹት የተቃውሞ ሰልፉን ለመከልከል መንግስት የተለያዩ መንገዶችን ቢጠቀምም፣ አስፈላጊውን መስዋትነት በመክፍል ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ነው። የክልሉ መስተዳደር ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ፈቃድ መስጠቱንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለማስተባበል የሞከሩት ህዝቡን ይበልጥ ማስቆጣቱንም ...
Read More »የአዲስአበባ አስተዳደር ጋዜጠኞች ለአባይ ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀሩ
የካቲት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ጋዜጠኞችና ሠራተኞች ለአባይ ግድብ ቦንድ ግዥ በድጋሚ እንዲያዋጡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ የአስተዳደሩ ሹማምንትና ካድሬዎች ከሁለት ዓመት በፊት ሠራተኛውን ካወያዩ በኃላ በራሳቸው ውሳኔ ሠራተኛው የአንድ ወር ደመወዙን በአንድ ዓመት ከፍሎ ለማጠናቀቅ እንደፈቀደ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ሰፊውን ሠራተኛ በማስቆጣቱ ወዲያውኑ ስብሰባ እንዲጠራለት በመጠየቅ ተቃውሞውን ...
Read More »