ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየአመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል አምና በጅጅጋ ሲከበር ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ሲያስወጣ ዘንድሮ ደግሞ በአሶሳ በሚከበረው እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያስወጣል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት የብሄር ብሄረሰቦችንም ሆኑ የባንዲራ፣ የመከላከያና ሌሎች አገር አቀፍ በአላትን በብቸኝነት ለማዘጋጀት የተፈቀደለት ወዛም ኮሚኒኬሽን የተባለው ድርጅት ለህወሃት ባለስልጣናት ገቢ ማስተላለፊያ ድርጅት ሆኖ በማገልገል ...
Read More »በበለሳ የጸጥታ ሰራተኞች እርስ በርስ ተታኩሰው ተጋደሉ
ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ የጸጥታ አስተዳደር ሰራተኞች እርስ በርስ ሲገማገሙ ከቆዩ በሁዋላ ፖሊሶቹ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውንና አቶ ባዩ ማሩንና ሌላ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውን በጥይት ደብድበው ገለዋል። አቶ አባይ ማሩ በጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዳር 3 ቀን ተቀብረዋል። በተራ ፖሊስ አባላት የተወሰደው እርምጃ አመራሩን ድንጋጤ ውስጥ ከቷል። ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን በእስር ላይ ለሚገኙት ለሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች የመከላከያ ምስክርነት ሰጠ
ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህዳር 25/2007 ዓም የመከላከያ ምስክርነቱን የሰጠ ሲሆን ጥር 11/2004 በታላቁ አወሊያ መስጂድ ቅጥር ጊቢ ተገኝቶ የሙስሊም መሪዎች በነጻ ምርጫ መመረጣቸውን ተናግሯል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሃምሌ 9/2004 የህግ አዋቂውን ኡስታዝ ካሚል ሸምሱን፣ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን፣ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋን፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ማናገሩን ገልጿል። የመንግስት ባለስልጣን የሆኑት አ/ቶ ሪድዋን ሁሴን በሰንደቅ ...
Read More »በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ውስጥ የሚገኘው መንግስት ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል ከፍተኛ ብድር ይፈልጋል ተባለ
ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ የተባለው አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከአለማቀፍ የግል ባንኮች ለመበደር የወሰነው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለግል አበዳሪ ተቋማት ባላሃብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። ፋይናንሻል ታይምስ 1 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ጫፍ ላይ የደረሰው መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ያልተለመደ ወይም እስከዛሬ ያልታየ ነው ብሎታል። አገሪቱ በኢኮኖሚ እየገሰገሰች መሆኑዋን፣ በምግብ ...
Read More »የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለንግዱ ማህበረሰብ ጥሪ አቀረበ
ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብበሩ የንግዱ ማህበረሰብ ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም በሚደረገው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከመሳተፍ ጀምሮ በገንዘብና በሌሎችም መንገዶች ድጋፉን እንዲገልጽ ጠይቋል። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት ጊዜ ጀምሮ ነጻ ገበያን እንደሚከተል በመግለጹ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻ ገበያ መርህ ተወዳድሮ ራሱንም አገሩንም ይጠቅማል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም ይህ ተስፋ እውን ሳይሆን መቅረቱን የገለጸው ትብብሩ፣ ይልቁንም ገዥው ...
Read More »አሶሳ በከፍተኛ የመከላከያ ጥበቃ ስር መውደቁዋ ተሰማ፡፡
ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-9ነኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የሚያስተናግደው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዝግጅት ማጠናቀቁን ቢገልጽም፣ በአካባቢው መንግስትን የሚቃወሙ ኃይሎች በተለያየ ጊዜያት በደፈጣ ውጊያ ጥቃት ማድረሳቸው ያሰጋው መንግስት በአካባቢው ከፍተና ወታደራዊ ሃይል አሰማርቷል። ህዳር 29 ከሚካሄደውን በዓል ጋር ተያይዞ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ብዙዎች የሚሰጉ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉ አመራሮች፣ ባለሃብቶችና ታዋቂ ሰዎች በተለያዪ ሰበቦች የጉዞ እቅዳቸውን የሰረዙ ...
Read More »በበርሊን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጀርመንን ለመጎብኘት መገኘታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያኑ መንግስትን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ጠ/ሚንስተሩ ከጀርመን መሪ አንግላ መርከል ጋር ተገናኝተዋል። ታዋቂው የጀርመን ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት በድር ለመስጠት ከተዘጋጁት ባንኮች መካከል ቀዳሚው ነው። ጉብኝቱም ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።
Read More »በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ ታወቀ
ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው። አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ ጽ/ቤትና ሌሎች ቁሳቁሶች ሰጥቷቸው ከመንግስት ...
Read More »የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዝቡ ድጋፉን እንዲሰጠጥ ጠየቀ
ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ህዳር 27 እና 28 በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የአንድ ቀንና ሌሊት የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ የተጀመረውን የሰው በሰው ቅስቀሳ እንዲደግፍ፣ የገንዘብ የሞራልና ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዲያደርግ እንዲሁም ለትግሉ ይጠቅማል ያሉትን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል። ህዝቡ በዝግጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በመስቀል አደባባይ በሚኖረው ቆይታ የሚያስልጉት ቁሳቁሶች በተለይም ደረቅ ምግብና ውሃ ከአሁኑ እንዲያዘጋጅ ትብብሩ አስታውሷል። ትብብሩ ...
Read More »በአማራ ክልል ባለፉት 5 አመታት ከ6ሺ በላይ ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጡ
ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በተከሰተ አደጋ በክልሉ 18ሺ 994 የመኪና አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡ በትራፊክ ሳምንት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በአጠቃላይ በአምስት አመታት በተከሰተው አደጋ 6ሺ 668 ሰዎች ህይዋታቸውን አጠዋል፡፡ 6ሺህ 581 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤ 11 ሺ 781 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው 994 ሚልዮን 626 ሺህ 866 ብርየሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ በ2007 ዓ.ም ...
Read More »