ሚያዝያ ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 12 ፣ 2007ዓም ኡራኤል አካባቢ አንድ ኢትዮጵያዊ ቤንዚን በራሱ ላይ አርከፍክፎ የተወሰነ የሰውነት ክፍሉ ከተቃጠለ በሁዋላ በህዝብና በፖሊስ እርዳታ ሊተርፍ ችሎአል። የአይን እማኞች ግለሰቡ ሙሉ ልብስ የለበሰ እና ጥሩ የሰውነት ቁመና ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ፖሊሶችም ግለሰቡን ወደ ስድሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል ዘግይቶ በመጣው መረጃ ደግሞ ግለሰቡ የመንግስት ሰራተኛና ከስራ ከወጣ ...
Read More »ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያን ምርጫ ሂደት በማበረታታት ስህተት መሥራቷን ፍሪደም ሀውስ ገለጸ።
ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፍሪደም ሀውስ ይህን ያለው-በዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ወንዲ ሸርማን ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ አስመልክተው ለተናገሩት ንግግር በሰጠው ምላሽ ነው። ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደኾነች የጠቀሱት ወንዲ ሸርማን ሀገሪቱ በመጪው ግንቦት የምታደርገው ምርጫ ነጻ፣ፍተሀዊና ተዓማኒ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ተናግረዋል። “ወንዲ ሸርማን የተናገሩት ነገር መሉ በሙሉ በመረጃ ላይ ያልተመሰረተና መጥፎ ውጤት የሚያስከትል ...
Read More »የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በ አስቸኳይ እንዲቆም አሣሰቡ።
ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዶክተርን ኮሳዛና ድላሚኒ የተፈጸመው ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። “ምንም ዓይነት ችግር ቢጋረጥብንም፣ ሟቾቹ የሀገሬው ሰው ይሁኑ አልያም የውጪ ሀገር ዜጋ፤ በህዝብ ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በምንም ዓይነት ምክንያት ማስተባበል አይቻልም” ብለዋል- ሊቀመንበሯ። የደቡብ አፍሪካ መንግስትና የኩዋ ዙሉ አካባቢ አገልግሎት ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ...
Read More »“ኢትዮጵያውያን የሀገራችንና የራሳችን ክብር እና ደህንነት ማስጠበቅ ካለብን መጀመሪያ ሀገራችን ላይ የሚገኘውን ስርዓት በፅኑ መታገል የግድ ይለናል”ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ።
ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ፦«ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም!»በሚል ርእስ በየመንና በደቡብ አፍሪካ በሚገኚ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ፣የኢትዮጵያውያን የውርደት ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰሞኑን ከተከሰተው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ አድርሶናል ብሏል። “የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ተጎጂ የሆኑትን የውጭ ዜጎች መንግስታቶቻቸው ቀድመው ሲያስወጡ ለኢትዮጵያውያን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም”ያለው ሰማያዊ ...
Read More »የኢህአዴግ አባል የሆኑ መምህራን ተሸለሙ
ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዛሬ ሚያዝያ 9/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀን በሚከበረው ‹‹የመምህራን ቀን›› የኢህአዴግ አባል የሆኑ መምህራን ብቻ መሸለማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ በዝግጅቱላይ የነበሩ መምህራንን ዋቢ አድርጎ ዘገበ፡፡ በተማሪዎች ዘንድ ብቃት የላቸውም ተብለው ቅሬታ የሚነሳባቸው መምህራን የገዥው ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ‹‹ምርጥ መምህራን›› ተብለው እንደተሸለሙ የገለጹት መምህራኑ ‹‹ከመቶው 90፣ 80…. አግኝተዋል ተብለው ከመሸለማቸውውጭ መስፈርቱም ግልጽነት የጎደለውና ወገንተኛ እንደሆነ በግልጽ ተገንዝበናል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በታህሳስ ወር 2007 ዓ.ም በፈጠራ ውጤታማ የሆኑትን መምህራን ሸልመው እንደነበር ያስታወሱት መምህራን ‹‹በአገር ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈጠራ ሙያቸው የተሸለሙት መምህራን አሁን በከተማደረጃ ለተደረገው ሽልማት እንደማይበቁ ተደርጎ ከሽልማቱ መገለላቸው መምህራኑን አነጋግሯል›› ብለዋል፡፡ ዛሬ በተከበረው በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙት እንዳይካተቱ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት የኢህአዴግ አባል ባለመሆናቸው እንደሆነ፣ በሌላ በኩል የኢህአዴግ አባል የሆኑትና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም የተሸለሙትአሁንም መሸለማቸው የድርጅቱ አባል ያልሆኑትን መምህራን ሆን ተብሎ ለማግለል ያለመ ነው ብለዋል፡
Read More »ደቡብ አፍሪካውያን ጥላችን በመቃወም ታላቅሰልፍ አደረጉ
ሚያዝያ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የውጪ ሀገር ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ያስቆጣቸው በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ደርጊቱን ለማውገዝ በደርባን ታላቅ ሰልፍ ማድረጋቸውን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን እና የውጭ አገር ዜጎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። “የውጪ ሀገር ዜጎችን ማጥቃትና ማሳድድ ይቁም!” የሚል መፈክር ያነገቡት የደርባን ነዋሪዎች፤ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ተቃውሟቸውንና ቁጣቸውን ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ ትናንት ...
Read More »በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊየን በላይ ሰዎች በምግብ እርዳታ ይኖራሉ ተባለ
ሚያዝያ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው በአሁኑ ወቅት በገጠር ያሉ 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ቤተሰቦች ያለባቸውን የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ በሴፍቲኔት እንዲታቀፉ የተደረገ ሲሆን ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ነጥበ 9 ቢሊየን ብር ለክልሎች ተላልፎ፣ ከዚህ ውስጥ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ለተጠቃሚዎች መከፈሉን መረጃው ያሳያል፡፡ በተጠቀሰው ወራት ወደወረዳዎቹ ከ32 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ...
Read More »የኢትዮጵያ አርሶደሮች ከሱዳን ፖሊሶች ጋር ተጋጩ
ሚያዝያ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መረጃዎች እንደሚያመለክትቱት ከዚህ ቀደም በኢህአዴግ መንግስት ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ላይ ሲያርሱ የነበሩ አርሶአደሮች በሱዳን ታጣቂዎች ተኩስ የተከፈተባቸው ሲሆን፣ አርሶደሮችም ራሳቸውን በማደራጀት የአጸፋ እርምጃ መውሰዳቸው ታውቋል። በሁለቱ ሃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ግጭቱ የረገበ ቢመስልም ውጥረቱ ግን እንዳለ ነው ይላሉ። ኢትዮጵያውያኑ ለሱዳን የተሰጠው መሬት የኢትዮጵያ መሬት ነው በማለት ተቃውሞ ...
Read More »በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ
ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች ያስተላለፉትን ድንገተኛ ትእዛዝ ተከትሎ በፌደራል ፖሊስ አባላት የእጅ ስልኮችና የኢሜል አካውንቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ የተቃዋሚ መሪ ፎቶዎችን፣ አገራዊ ሙዚቃዎችንና ማንኛውም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ከኢንተርኔት አውርደው በስልካቸው ላይ ያስቀመጡ ፖሊሶች ተይዘው የተወሰኑት ማእከላዊ ሲገቡ፣ የተወሰኑት ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸውን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። በድንገት የተደረገውን ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ ነው
ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ አፍሪካዋ የቱሪስት ከተማ የደርባን ተወላጆች_የውጭ አገር ዜጎች ከአገራቸው እንዲወጡ ለማስገደድ በወሰዱት ጥቃት 3 ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አጇንስፍራንስፕሬስዘግቧል። ኢትዮጵያዊያኑ ሱቆቻቸው ውስጥ እንዳለ በጋስ በተሞላ ቦንብ መቃጠላቸውን አንዳንዶች ተደብድበው መሞታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በደርባንና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጭንቅ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ደግሞ አንድ ኢትዮጵያዊ አገራችን ችግር ...
Read More »