የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፈቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ላይ ተደብድበው መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጌትነት የሰማያዊን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አረካ ላይ ተደብድበው ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን ተቀምተዋል። የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያዝም ፖሊስ እርሳቸውን አስሮ ወንጀሉን የፈፀመውን ሰው ለቆታል። አቶ ጌትነት ድርጊቱ በመንግስት ...

Read More »

በቁጫ ሰዎች ታሰሩ

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነትና ከአስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ለአመታት የዘለቀው የቁጫ ህዝብ ጥያቄ፣ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ አሁንም የሚታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከ140 በላይ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ካለፉት ሁለት አመታ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችም መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል። በአካባቢው የሚታየው አፈና ከአቅም ...

Read More »

አራት ንፁሃን ሶማሊያዊያን በኢትዮጵያ ሰራዊት ተገደሉ

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር የዘመተው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት በመሃከላዊ ሶማሊያ በገልጋዱ ግዛት ውስጥ አራት ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎችን በግፍ መግደሉንና ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል። ”በአካባቢያችን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች እንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ እርምጃዎች እየተወሰዱብን እኛ ከዚህ በላይ ልንታገስ አይገባንም።ይቅርታ ልናደርግላቸውም አይገባንም።ካለርህራሄ አራት ንፁሃን ሰላማዊ ዜጎቻችንን ገለውብናል።” በማለት ...

Read More »

ቤኒሻንጉል ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ግድያ ተፈጸመባቸው

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 25, 2015) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ ጥቃት መሰንዘሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ተፈጸመ በተባለው በዚሁ ጥቃት፣ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ አማሮች ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ከሶስት ወራት በፊት በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 84 ሰዎች መገደላቸውን ...

Read More »

የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳን ባለሀብቶች መተማ ዮሃንስ ከተማ ውስጥ “ትራክተር መንዳት የሚችል 11 ሰዎችን እንፈልጋለን” የሚል ማስታወቂያ መለጠፋቸውን ተከትሎ፣ ውድድሩን ካለፉት መካካል 8ቱ በሱዳን ታጣቂዎች ታርደው ተገድለዋል። ባለሀብቶቹ በርካታ አመልካቾችን ቢያገኙም፣ አስራ አንዱን ብቻ ይዘው ወደ ሱዳን መሄዳቸውን ፣ ይሁን እንጅ ሱዳን ውስጥ ሲገቡ፣ ወታደሮቹ መንገድ ላይ ጠብቀው ከመኪና ላይ በመውጣት ሰዎችን ማረድ ሲጀምሩ፣ ...

Read More »

በቡሌሆራ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎቸ ተጎዱ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 19 ቀን በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ ከተማ፣ በ1949 የተገነባውን የገበያ ማእከል በማፍረስ የመኪና መናሃሪያ ለማድረግ፣ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት ህዝቡ ያሰማውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ከ150 በላይ ሰዎች በድብደባ ሲቆስሉ፣ ወገኖ ወንዳቸው የተባለ ወጣት በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ገብቶ እየታከመ ነው። የከተማው ባለስልጣናት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ሳይስማሙና ለነጋዴዎቹ አስፈላጊውን ካሳ ሳይከፍሉ የማፍረሻ ...

Read More »

በርካታ የትግራይ ህዝብ ለርሃብ ተጋርጦ ባለበት ሰአት ህወሃት 2 ሺ እንግዶችን በውስኪና በቁርጥ ስጋ አንበሸበሸ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ባለፈው ቅዳሜ ህወሃት ለኢህአዴግ ጉባኤተኞች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ፣ ከ2 ሺ ያላነሰ ሰው ተገኝቷል። ለእንግዶቹ የተለያዩ ምግቦች፣ ቁርጥ ስጋ እና ውስኪ እንደ ልብ ቀርቦላቸዋል። ግብዣው የተደረገው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚላስና የሚቀመስ እንደሌለው ሪፖርት በተደረገበት ወቅት ነው። በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱን ሪፖርቶች ያስረዳሉ። ኢህአዴግ ለተለያዩ በአላት ...

Read More »

ኣርበኞች ግንቦት ፯ ሌላ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ በኮሎራዶ ዴንቨር ማድረጉን አስታወቀ

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትላንትናው እለት በርካታ የኮሎራዶ ነዋሪዎች በተሳተፉበት ስብሰባ ላይ የከተማው ኣርበኞች ግንቦት ፯ ክፍል ለጫራታ ያዘጋጀው መኪና በ47 ሺ 200 ዶላር ተሽጧል። በዚህ ሀገርን የማዳን ጥሪ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ የምክርቤት አባል ኣቶ ቸኮል ጌታነህ በአካል ተገኝተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጋዜጠኛ አበበ ገላው የትግልን አስፈላጊነት በተመለከተ ንግግር አድርጓል።

Read More »

ኢህአደግ ጥራት ያለው አባል ማግኘት አልቻልኩም አለ

ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ሰማእታት አዳራሽ ዛሬ ሲጀምር በጽሁፍ ባሰራጨው ሪፖርቱ የአባላት ጥራት ችግር እንደገጠመው ይፋ አደርጓል። ሪፖርቱ እንደሚለው አባላት ስለድርጅቱ ታሪክ ፣ፕሮግራም፣እሴቶችና ህገደንብ ዝርዝር ግንዛቤ ሳይዙ የሚመለመሉበት ሁኔታ አለ። “በእኛና በተቃዋሚዎች መካከል ስላለው መሰረታዊ ልዩነት ፣ስለመድረኩ ባህሪና ፈተናዎቹ በቂ መነሻ እውቀት ይዘው የእጩነት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደሙሉ አባልነት እንዲሸጋገሩ ...

Read More »

ለምርጫ ተብለው የተቀየሩ ትራንስፎርመሮች ተቃጥለው በርካታ ሰዎች ተጎዶ

ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ የተቀየሩ በርካታ ትራንስፎርመሮች በአንድ ቀንና ሰአት በመቃጠላቸው ሰዎች ተጎድተዋል። በነ ጸማይ ወረዳ ቃቆ ቀበሌ ትራንስፎርመሩ ሲቃጠል አንድ ነርስ ወዲያውኑ ህይወቱን ሲያጣ፣ 11 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። በዚሁ ወረዳ ቀይ አፈር ከተማ ላይ ተጨማሪ 3 ትራንስፎርመሮች ሲፈነዱ፣ በሀመር ወረዳ በዲመካ ከተማ አንድ ትራንስፎርም፣ በጂንካ ከተማም ...

Read More »