ሚያዚያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በረሃብ የተጠቁት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ቀድሞ ከተገለጠው 10 ሚሊዮን በእጥፍ ጨምሮ 20 ሚሊዮን ደርሶአል፡፡ ይህ አሃዝ በምግብ ለስራ የታቀፉትና የምግብ እርዳታ የሚሰፈርላቸውን 8 ሚሊዮን ዜጎች እንዲሁም፣ በከተሞች በምግብ እጥረት የተጠቁትን 10 ሚሊዮን ዜጎች አይጨምርም፡፡ በድርቅ ከተጎዱ 443 ወረዳዎች መካከል 219 ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ችግር አጋጥሞአቸዋል፡፡ ከፍተኛ የምግብ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከግማሽ በታች እንደሚያሽቆለቁል አይ.ኤም.ኤፍ. አስታወቀ
ሚያዚያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በምህጻረ ቃሉ አይ ኤም ኤፍ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት በያዝነው ዓመት ላይ የኤኮኖሚ እድገታቸው እንደ ሚያሽቆለቁል ገልጾአል፡፡ ድርጅቱ ድርቁን ተከትሎ ኤኮኖሚያቸው ክፉኛ ከሚጠቁ አገራት ተርታ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ተጎጂ አገር መሆኗንና ካለፈው ዓመት ካስመዘገበችው እድገት ከግማሽ በታች በመውረድ 4.5% ከመቶ እንደምታስመዘግብ ገልጾአል፡፡ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የነዳጅ ላኪ የአፍሪካ አገራት የዓለም ...
Read More »በኢትዮጵያ 84ሺህ ብቻ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን CNN ዘገበ
ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) በአፍሪካ ባሉት 97 ሚሊዮን ህዝብ ቁጥር በአህጉሪቱ ከናይጀሪያ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ 84ሺህ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዳሏት ተገለጠ። በጉዳዩ ዙሪያ ልዩ ዘገባን ያቀረበው ሲኤንኤን (CNN) የቴለቪዥን ጣቢያ ሃገሪቱ ከውጭ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ 35 በመቶ ታክስን እንደምታስከፍልም አመልክቷል። አብዛኞቹ ተሽከርካዎች ከውጭ ሃገር የገቡ መሆናቸውን ያወሳው የቴለቪዥን ጣቢያው በአሁኑ ወቅት 84ሺህ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ባቀረበው ሪፖርት ...
Read More »የማህበራዊ ድምጽና ምስል አገልግሎቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተቋረጡ
ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) መንግስት በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደረጉ የድምፅና የምስል አገልግሎቶች ላይ አዲስ መመሪያን እንደሚተገብር ማስታወቁን ተከትሎ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተቋረጠ። በተለይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል የትዊተርና የWhatsAPP አገልግሎቶች ከተቋረጡ አንድ ወር አካባቢ እንደሆናቸው ብሉምበርግ የዜና ወኪል የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ አገልግሎቶቹ በደቡብ ክልል ሃዋሳ ከተማና በተለያዩ ...
Read More »በኢትዮጵያ በአለም ደረጃ በጣም ውድ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደምታቀርብ ተገለጸ
ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) ኢትዮጵያ በአለማችን ካሉ ሃገራት መካከል የኢንተርኔት አገልግሎትን በጣም ውድ በሆነ ክፍያ በማቅረብ ግንባር ቀደም ሃገር ሆና መገኘቷን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ይፋ አድርጓል። ይኸው የ120 ሃገራትን ታሪፍ በንጽጽር ያቀረበው ኑሚቢዬ የተሰኘው አካል በኢትዮጵያ ዝቅተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያው የማይቀመስ መሆኑንም አመልክቷል። የኢትዮ-ቴለኮም ባለስልጣናት ይህንኑ አገልግሎት ጨምሮ በቫይበር የሚደረግ የስልክ ጥሪ ...
Read More »የመከላከያ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስብሰባ የሰራዊት መክዳት አብይ ርዕስ ነበር ተባለ
ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) የመከላከያ ሚኒስቴር የበታች ሹሞችና መኮንኖች ባዘጋጀው የ4 ቀናት ኮንፈረንስ የሰራዊቱ መክዳት አብይ ርዕስ ሆኖ መውጣቱን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሳምንት የተካሄደውና ከሰኞ እስከ ሃሙስ በቀጠለው ኮንፈረንስ ከተለያዩ የሰራዊቱ ክፍሎች የተውጣቱ የበታች ሹሞችና መኮንኖች በቪዲዮ ኮንፈረንሰ ከመከላከያ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። አዲስ አበባ ላይ ሆነው በቪዲዮ ኮንፈረንሰ ማብራሪያና መግለጫ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ሲሆኑ፣ ከፍተኛውን ...
Read More »አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር በወልቃይት ጉዳይ ጸብ ውስጥ ነኝ አሉ
ዜና (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) የወልቃይትን ማንነት በተመለከተ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት፣ ከትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ጋር ፀብ ውስጥ መሆናቸው ተገለጠ። ይህንን የተናገሩት ራሳቸው የአማራ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ፣ የአማራ ምሁራን ከሩቅ ሆነው ከሚቃወሙ እንደ ትግራይ ተወላጆች ሃብት እንዲሰበስቡም ጥሪ ማቅረባቸው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ በህክምና ላይ የሚገኙትን ባለቤታቸውን ለመጎብኘት በአሜሪካ የሚገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የወልቃይት ...
Read More »መንግስት በኮምፒዩተሮች ላይ እንደፈለገ ስለላ የሚያካሂድበትን ህግ አረቀቀ
ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት እንደፈለገ የግል የኮምፒውተር መረጃዎችን መጥለፍ፣ መበርበር፣ መሰለል፣ ኦን ላይን መፈለግ የሚያስችለውን ህግ አርቅቆ ለፓርላማ አቅርቦአል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ኮምፒውተር ወይንም የኮምፒወተር ስርዓት ምንነት ሲያብራራ በሶፍትዌር እና ማይክሮቺን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ የዳታ ፕሮሰሲንግ፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ስርጭት፣ ግንኙነት ወይንም ሌሎች ሂሳባዊ ወይንም አመክኖአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ ነው ይለዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የኮምፒውተር ወንጀል ...
Read More »በጅንካ የመከላከያ ሰራዊትና ልዩ ሃይል አባላት ከፍተኛ ቅኝት እያደረጉ ነው
ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በደቡብ ኦሞ በጅንካ ከተማና አካባቢዋ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከልዩ ሃይል አባላት ጋር በመሆን፣ በተለይ ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ በመኪኖች ላይ መትረጊስና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችን ደግነው ቅኝት በማድግ ላይ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የወጣቶች ነጻ እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን፣ ነዋሪዎችም ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ክትትሉ የተጀመረው በአካባቢው ከፍተኛ እውቅና ያላቸው የኦሞ ህዝቦች ...
Read More »አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በ1.1 ብር ሚሊዮን ብር የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው
ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪልስቴት መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ዋስትና የቀረበባቸውን ክስ ውጪ ሆነው መከራከር እንደሚችሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብያኔወስኗል። ባለሃብቱን በደረቅ ቼክና በሌሎች የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው አቃቤ ሕግ የዋስትና መብቱን እንዲነሳ ቢቃወምም ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በመቀበል ውጪ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ሲል ብያኔውን ሰጥቷል። አቶ ኤርሚያስ ...
Read More »