ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ2015ትን የአለም የሰብአዊ መብት አያያዝን የሚተነትነው ሪፖርት በኢትዮጵያ የሚታየው አፈናና ዜጎችን በእስር ቤት ማሰቃየት መቀጠሉን ይተነትናል፡፡ የአሜሪካ መንግስት በያመቱ በሚያወጣው የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ተቃዋዎችን ፣ ደጋፊዎቻውንና ጋዜጠኞችን እንደሚያሳድዱ፣ እንደሚያስሩ፣ በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድደባ እንደሚፈጽሙ፣ እንዲሁም በህግ ስም ፖለቲካዊ ክስ እንደሚመሰር ዘርዝሮአል፡፡ ያለ ህግ እንደፈለጉ መግደል፣ ማሰር፣ ለፍርድ ...
Read More »እነ አቶ ዓለማዬሁ መኮንን በድጋሜ ተቀጠሩ
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከመጋቢት 20፣ 2008 ዓም ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ አንድነት የዞኑ ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ፖሊስ የጠየቀባቸውን የ14 ...
Read More »85 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር ባልተማረበት ሁኔታ የመንግስትን የልማት እቅድ ማሳካት አይቻልም ተባለ
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ከያዛቸው እቅዶች መካከል የተጠናከረ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም አንዱ ቢሆንም፣ ባለሙያዎች ግን በእቅዱ አተገባበር ላይ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ሰሞኑን በክልል ደረጃ በተደረገው የባለሙያዎች ውይይት እንደተነገረው የ2008 ዓም የጎልማሶች ትምህርት እየተቀዛቀዘ ሄዶአል፡፡ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም የልማቱ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብሎ የሚያምን አመራር አለመገኘቱን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሸን ...
Read More »በባህርዳር ታዋቂው ዳቦ ቤት ለልማት በሚል ስም ሊፈርስ ነው
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳሬዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት አለው፤ በታሪካዊነቱ ብቻ ሳይሆን ፣ በጣፋጭነቱም ይታወቃል፡፡ በ1962 ዓም የተቁዋቁዋመው እና ለ50 አመታት ተወዳጅነቱን ጠብቆ የዘለቀው የመጀመሪያው ዳቦ ቤት የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል፡ ዳቦ ቤቱን የመሰረቱት ሃጅ አድጎይ መሃመድ ወይም በከተማው ህዝብ አጣራር አባ አድጎይ ዛሬ በህይወት የሉም፡፡ ቤተሰቦቻቸው ግን ድርጅቱን ይዘው በመዝለቅ እስካሁን ድረስ የከተማውን ህዝብ ዳቦ እየጋገሩ ...
Read More »የፍርሃት ስሜት፣ ሁከት፣ አመጽ እንዲፈጠር የሚያነሳሳ ጽሁፍና የተንቀሳቃሽ ምስልን አሰራጭቶ የተገኘ ሰው በህግ የሚያስቀጣ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በአገልግሎት ላይ ያሉ የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችን ለመመዝገብ በዝግጅት ላይ የሚገኘው መንግስት አመጽ የሚያነሳሳ ወይም ጹሁፍን ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች ድርጊቶችን በህግ የሚያስቀጣ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ። ይኸው በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ረቂቅ አዋጅ ማንኛውም ሰው በህበረተሰቡ መካከል የፍርሃት ስሜት፣ ሁከት፣ አመጽ እንዲፈጠር የሚያነሳሳ ጽሁፍና የተንቀሳቃሽ ምስልን አሰራጭቶ ከተገኘ በህግ እንደሚቀጣ አመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም ሰው ...
Read More »ከ20 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ ጠባቂ መሆናቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እየባሰና እየተስፋፋ በመቀጠል ከህዝቡ 1/5ኛው ወይንም 20 ሚሊዮን ያህሉ የምግብ እርዳታ ጠባቂ ማድረጉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። በታህሳስ ወር ላይ በድርቅ ተጠቂ የነበሩት 429 ወረዳዎች ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት የድርቅ ሰለባ የሆኑ ወረዳዎች ቁጥር በ 14 ጨርሞ 443 መድረሱንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመጥቀስ ብሉምበርግ ዘግቧል። በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ የተጠቁ ወረዳዎች ቁጥር በ18 በመቶ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ሃይሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አለም-አቀፍ ትኩረት አለማግኘቱን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይሎች ቢገደሉም፣ አለም አቀፍ ማህበረሰቡ ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘነው የሰብዓዊ መብቶች ጠባቂ ድርጅት (Human Rights Watch) ትናንት ባወጣው መግለጫ ገለጸ። በኦሮሚያ ክልል የታየው ተቃውሞ ከምርጫ 97 በኋላ ከተቀሰቀሱት የፖለቲካ ቀውሶች ትልቁ እንደሆነ የገለጸው የሰብዓዊ መብቶች ጠባቂ ድርጅት (Human Rights Watch)፣ ይህ ተቃውሞ ግን በአለም አቀፍ መድረክ ያገኘው ...
Read More »የድርቅ መከሰትን ተከትሎ ከ600 ሺ በላይ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ ከ600ሺ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። ድርቁ እያደረሰ ያለው ጉዳት እልባት ባለማግኘቱ ምክንያትም ህይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ መኖሪያ ቀያቸውን እየለቀቁ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችልም ተሰግቷል። በድርቁ ሳቢያ ከተፈናቀሉት ወደ 640ሺ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በአፋር፣ ሶማሊ እና አማራ ክልል የሚገኙ ሲሆን ከእነዚሁ መካከልም ...
Read More »የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ወደ 4.5 በመቶ እንደሚያሽቆለቁል ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 5 ፥ 2008) በ11 በመቶ እድገትን ያስመዘግባል ተብሎ የተጠበቀው የዘንድሮው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ወደ 4.5 በመቶ እንደሚያሽቆለቁል የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ረቡዕ ይፋ አደረገ። የመንግስት ባለስልጣናት ለተከታታይ አመታት እድገትን አሳይቷል ያሉት የኢኮኖሚ እድገት በተያዘው አመት በሁለት አህዝ እድገትን ያስመዘግባል ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንና በአለም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዙሪያ አዲስ ሪፖርትን ያወጣው የገንዘብ ተቋሙ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ...
Read More »በደሴ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተበተኑ
ሚያዚያ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወጣቶች ትናንት ምሽት በተለያዩ የደሴ ከተማ አካባቢዎች የበተኑት ወረቀት የከተማው ህዝብ ትኩረት መሳቡን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡ የትግል ጥሪ ወረቀቶች፣ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ፣ በወልቃይት ጥያቄ ዙሪያ የደሴ ህዝብ ጥያቄውን ከሚያቀርቡ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ጋር በጋራ እንዲቆም የሚያሳስቡ ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ህዝብ በብዛት ይገኝባቸዋል በተባሉ ቦታዎች፣ በአራዳ፣ መናፈሻ፣ መላ፣ መናሃሪያ ...
Read More »