ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በድንበር ዘለል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጥቃት ኢትዮጵያ ግዛት ገብተው ሰዎች ሲገድሉም ሆነ ታፍነው ሲወስዱ ይህ የመጀመሪያቸው አለመሆኑን የጋምቤላ ክልል ፕሬዚደንት ገለጹ። ከሰሞኑ ጥቃት በፊት ባሉት 20 ቀናት ብቻ ታጣቂዎቹ 21 ኢትዮጵያውያን ገድለው፣ 17 ህጻናትን አፍነው መውሰዳቸውን ለመንግታዊና ለፓርቲ ሚዲያዎች በሰጡት ቃለምልልስ አመልክተዋል። የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ እንደተናገሩት አርብ ሚያዚያ 8 ፥ 2008 ከተገደሉት ...
Read More »ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በቃሊቲና በሌሎች የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች የደረሰባቸውን ሰቆቃ ገለጹ
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) የህወሃት ኢህአዴግን መንግስት በመሸሽ በኬንያ ተሰደው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቃሊቲና በሌሎች የኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች የደረሰባቸውን ሰቆቃ ኦኬ አፍሪካ ለተባለ ጋዜጣ በዝርዝር ገለጹ። በኢትዮጵያ ወህኔ ቤቶች ምን አይነት ሰቆቃ በእስረኞቹ ላይ ሲደርስ እንደበር በዝርዝር ያሰፈረው ጋዜጣው፣ በኬንያ ያሉት ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው በነበሩበት ጊዜ፣ በማዕከላዊና በሌሎች ተመሳሳይ እስር ቤቶች የሚገኙ መርማሪዎች፣ እስረኞቹን በኤለክትሪክ ወንበር እንደሚያቃጥሉ፣ እስኪቆስሉ ከገረፉ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ሊያጠናቀቅ ባለመቻሉ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያሰበው እንዳልተሳካ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በተያዘው አመት ስኳርን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዞ የነበረው መንግስት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ እቅዱ ለሁለተኛ ጊዜ መስተጓጎሉን የስኳር ኮርፖሬሽን ገለጠ። መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብን በመመደብ አራት የስኳር ፋብሪካዎችን ስራ ለማስጀመር ጥረት ቢያደርግም ፋብሪካዎቹ መጠናቀቅ እንዳልቻሉ ታውቋል። በሃገሪቱ በመባባስ ላይ ያለው የድርቅ አደጋ በነባር የስኳር ፋብሪካዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንና ስኳርን ከውጭ ሃገር ለማስገባት ...
Read More »የአጣዳፊ ተቅማት ወረርሽን ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሰው ህይወት አጠፋ
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በድርቅ በተጎዱ ሶስት ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በተቀሰቀሰ የአጣዳፊ ተቅማጥ ወረርሽን በትንሹ 14 ሰዎች ሞተው ከ1ሺ የሚበልጡ ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ይኸው በኦሮሚያ፣ የደቡብ እንዲሁም የሶማሊ ክልሎች የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ በ15 ወረዳዎች ውስጥ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን በሽታው ወደ አጎራባች ክልሎች ይዛመታል ተብሎም ተሰግቷል። እስከሳምንቱ መገባደጃ በደረሰው የበሽታው ወረርሽኝ በትንሹ 14 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና ...
Read More »በኬንያ በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ወከባ እየደረሰባቸው ነው
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) ከኢህአዴግ መንግስት ሸሽተው በኬንያ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የኢትዮጵያ መንግስት ባሰማራቸው የደህንነት ሰዎች እንደሚዋከቡ ተገለጸ። በኬንያ የሚታተመው ኦኬ አፍሪካ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው በኬንያ የሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውና ንብረታቸውን በኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ከመዘረፋቸው በላይ፣ የማስፈራራት ድርጊትም ይፈጸምባቸዋል በማለት አትቷል። ታሪኩ ደበላ የሚባል አንድ በኬንያ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ጋዜጣው፣ በናይሮቢ ከተማ ኢስትሌይ በሚባል አካባቢ ...
Read More »በጋምቤላ የተጨፈጨፉት ዜጎች ጉዳይ ኢትዮጵያውያንን ማነጋገሩን ቀጥሎአል
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የአለምን ትኩረት በሳበት በዚህ ወቅት፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት ምንም አይነት መግለጫ አለማውጣቱ ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለጥቃቱ አፋጣኝ መልስ አለመስጠቱ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከባድ የሆነውን አገራዊ ጉዳይ ትተው ወሳኝ ላልሆነ ስብሰባ ስዊድን መገኘታቸው ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረ ነው። ...
Read More »በሃረር ለሚደረገው የብሄረሰቦች በአል 500 ሚሊዮን ብር በጀት ተያዘ
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምንጮች እንደገለጹት ህዳር 29 ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ግማሽ ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን፣ ገንዘቡም ከሃረረ ስታዲየም እስከ አመሬሳ የሚደረሰውን 3.3 ኪሜ ባለሁለት መስመር መገድ ለማሰራት እንዲሁም፣ ከውጭ ለሚመጡ ዲያስፖራ እንግዶች ማረፊያ 600 ባለ አንድ ፎቅ ቤቶችን ለመገንባት እና ከተማዋን ለማጽዳት ይውላል ተብሎአል። ለመንገድና ለቤቶች መስሪያ በሚል በሃኪም ወረዳ የሚገኙ 250 ነዋሪዎችና ...
Read More »በሸዋሮቢት ከተማ ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ደረሰ
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው ባሉ አጎራባች ቀበሌዎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ። ጎርፉ መጠነሰፊ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳትቶችን አስከትሏል። እስካሁን የደረሰውን የንብረት ውድመት በውል ለይቶ አሃዙን ማስቀመጥ ባይቻልም በሸዋሮቢት ከተማ ብቻ ባሉ አራት ቀበሌዎች ውስጥ ከአራት መቶ በላይ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ አደጋ ወድመዋል። ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት ቤት ...
Read More »በአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ሆነው ለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሜልበርን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የበላይ አስተዳዳሪ እና እንዲሁም የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሆነውለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በድንገት በተወለዱ በ71አመታቸው አፕሪል 18/ 2016 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተ/ክ ድጓ ጾመ ድጓንና አቋቋም በታወቁ የጎንደር ጉባዕዎች፣ ቅኔን በጎጃም እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርትም በሩሲያ የተማሩ ...
Read More »በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ በጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ ትናንት ሰኞ ከባድ ዝናብ ጥሎ ከ400 ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ፣ አገልግሎት ድርጅቶች መውደማቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። በከተማው 03 ፥ 02 እና 05 ቀበሌ በደረሰው በዚሁ የጎርፍ አደጋ፣ በርካታ የንግድ ሱቁችና ሆቴሎችና የህክምና ተቋም በጎርፉ ተወስደዋል። በደረሰው ጎርፍ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም፣ የንግድ ሱቆችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በጎርፍ ፈራርሰው ...
Read More »