ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008) ከ200ሺ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሚገኙበት የጋምቤላ ክልል የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት በአዲስ መልክ መቀጣጠሉ ተገለጸ። ይኸው ግጭት በርካታ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን አስጠልሎ በሚገኝበት የጃዊ መጠለያ ጣቢያ መቀጠሉንና በድርጊቱ ተጨማሪ ሰዎች ይሞታሉ የሚል ስጋት መኖሩን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ከ10 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ግድያ ተጠያቂ ናቸው ...
Read More »የኢንተርኔት አጠቃቀም ረቂቅ ህግ እንዲወጣ የተደረገው ተቃዋሚዎችንና ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር ነው ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008) በቅርቡ በኢትዮጵያ ረቅቆ ለምክር ቤት የቀረበው የኢንተርኔት አጠቃቀም ህግ በአገሪቱ ያሉትን የመንግስት ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የድረ-ገጽ ተጠቃሚዎችን ድምፅ ለማፈን ሆን ተብሎ የታቀደ ህግ እንደሆነ በኬንያ የሚታተመው ኦኬ አፍሪካ የተባለው ጋዜጣ ዘገበ። በኢትዮጵያ የቀረበው አዲስ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ተብሎ የሚጠራው ረቂቅ ህግ በብዛት የሚሰራጩ የጹሁፍ መልዕክቶችን ተቀብሎ ማሰራጨት በወንጀል እንደሚያቀጣ ያትታል። በኬንያ የሚታተመውና ኦኬ አፍሪካ የተባለው ...
Read More »በትንሳኤ በአል ዋዜማ የሚታየው የዋጋ ንረት ሸማቾችን አስደንግጧል
ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከሚከበረውን የፋሲካ በአል ጋር ተያይዞ የቅቤ እና የዶሮ ዋጋ የተጋነነ ጭማሪ ሲያሳዩ፣ በብዙ የክልል ከተሞች ደግሞ ዘይት እስከናካቴው ጠፍቷል። በአማራ ክልለ በሚገኙ ከተሞች ደግሞ፣ ከዘይት በላይ ውሃ ማግኘትም እየቸገረ ነው። ዛሬ በአዲስአበባ ሳሪስ እና ሾላ ገበያዎችን የቃኘው ዘጋቢያችን እንደገለጸው፣ የምግብ ቅቤ የችርቻሮ ዋጋ በኪሎግራም ከ250 እስከ 300 ብር በመሸጥ ...
Read More »እነ አቶ መላኩ ፈንታ ተከላከሉ ተባሉ
ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የፀረ ሙስና ኮሚሽን በቀድሞ የጉምሩክ ኃላፊ በነበሩት አንደኛ ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታውና ግብረ አበሮቻቸው ላይ ከተከሰሱባቸው አስራ ሰባት ክሶች በተወሰኑት የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፎባቸዋል። 1ኛ ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር፣ 2ኛው ተከሳሽ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ የባለስልጣኑ የህግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ 3ኛው ተከሳሽ አቶ ...
Read More »ዱባይ 6ቱን የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ክስ አነሳች
ሚያዚያ ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው የካቲት ወር በዱባይ የተደረገውን የምግብ ኤግዚቢሽን ለመካፈል ያቀኑ 6 የኢትዮጵያ ነጋዴዎች፣ የተበላሸ ስጋ አቅርበዋል በሚል ለሁለት ወራት ያክል ከአገር እንዳይወጡ ታግተውና ሁለቱ ነጋዴዎች ደግሞ በተደጋጋሚ ሲታሰሩ መቆየታቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ጭንቅት ውስጥ መግባታቸውን በተደጋጋሚ ከገለጹ በሁዋላ፣በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና በኢህአዴግ መንግስት መካከል በተደረገ ስምምነት፣ ክሳቸው መነሳቱ ወደ አገራቸው መሄድ እንደሚችሉ እንደተፈቀደላቸው ታውቋል። ነጋዴዎቹ ...
Read More »የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ተብለው በመንግስት ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ኩባንያዎች ውጤታማ አይደሉም ተባሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008) የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኙ ታስበው በመንግስት ልዩ የማበረታቻ ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ከ30 በላይ ኩባንያዎች በየወሩ ስድስት ሚሊዮን ዶላር እንዲያስገኙ ቢጠበቅባቸውም ከ90 ሺ ዶላር በታች ማስመዝገባቸው ተገለጠ። በጉዳዩ ቅሬታ የተሰማቸው የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ድርጅቶቹ ሲደረግላቸው የቆየ ልዩ ልዩ ድጋፍ ተቋርጦ በኩባንያዎቹ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ አሳስበዋል። እነዚሁ በብረታ-ብረትና በኤሌክትሮኒክስ ማምረት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ድርጅቶች ለምርት ግብዓት የሚሆናቸውን ...
Read More »በአፍሪካ ሃገራት የመገናኛ ብዙህን ነጻነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008) ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት የመገናኛ ብዙህን ነጻነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያደረገ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ረቡዕ ይፋ አደረገ። መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገውና የ2015 ሪፖርቱን ለህዝብ ይፋ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ (Freedom House) እኤአ አቆጣጠር በ2015 የአለም የመገናኛ ብዙሃን ባለፉት 12 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሽቆልቁሎ መገኘቱን አስታውቋል። ከአፍሪካ ቡሩንዲ፣ በመገናኛ ብዙሃን ላይ ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲሱ ትውልድ የኢትዮጵያን አንድነት እንዲጠብቅና የታሪክ ህፀፆችን እንዲያርም ጥሪ አቀረበ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008) የኢትዮጵያ አንድነት የመጠበቅና የታሪክ ህፀፆችን ማረም ከአዲሱ ዘመንት ዲሞራቶች ይጠበቃል ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ። ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ የዘንድሮ ግንቦት 20” በሚል ርዕስ ሰሞኑን ከወህኒ ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ፅሁፍ ኢህአዴግ ወደስልጣን የመጣበትን 25ኛ አመት በማስመልከት ያለፉትን 50 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። በኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ውስጥ የነበረው ...
Read More »አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች እስከ ዘጠኝ አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008) የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ ሰባት ተከሳሾች በተመሰረተባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ከሰባት እስከ ዘጠኝ አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ። ተከሳሾች የቀረበባቸውን ወንጀል እንዳልፈጸሙ በመግለጽ የመከላከያ ማስረጃን በማቅረብ ሲከራከሩ ቢቆዩም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች ያቀረቡት ማስረጃ የሚያስተባብል አይደለም ሲሉ ውድቅ ማድረጉም ታውቋል። የተከሳሾች ጉዳይ ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ ...
Read More »ተመድና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ለምግብ እርዳታ ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀመሩ
ኢሳት (ሚያዚያ 19 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ አለመገኘቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችና መንግስት በለጋሽ ሃገራት በመዘዋወር ገቢ የማሰባሰብ ዘመቻ ጀመሩ። ይኸው ማክሰኞ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ ከተማ የተጀመረው ድጋፍን የማሰባሰብ ዘመቻው በስዊዘርላንድ ጄኔቫና በዚህ በአሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መቀመጫ በሆነችው የኒውዮርክ ከተማ እንደሚካሄድም ታውቋል። ከ10 ሚሊዮን ለሚበልጡ ተረጂዎች ወደ 1.4 ...
Read More »