ታላቁ የስፓርት አባት ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ የሩጫ ታሪክ ሲነሳ ስማቸው በጉልህ ከሚጠሩት የመስኩ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ በተወለዱ በስድሳ ስድስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ዶክተር ወልደመሰቅል ኮስትሬ በሸዋ ክፍለሃገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ሳሊት እንግዳ ዋሻ በተባለ ቦታ በ1942 ዓ.ም.ተወለዱ። ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በመምጣት በደጃዝማች ወንድይራድ ትምህርት ቤት በኮተቤ የመምህራን ኮሌጅ ወደ ባሕር ማዶ በማቅናትም ...

Read More »

በዛምቢያ 41 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሶስት ወር እስራት ተቀጡ

ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ዛምቢያ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ 41 ሰደተኞች ኢትዮጵያዊያን በሶስት ወር እስራት ተቀጡ። የሉአንግዋ ግዛት ፍርድ ቤት በስደተኞቹ ላይ የእስር ቅጣቱን ባስተላልፈ ጊዜ በየጊዜው ወደ ማላዊ የሚገቡ ኢትዮጵይዊያን ስደተኖች ቁጥር ለሀገሪቱ ስጋት እየሆነ መምጣቱን እንደገለጸም ሉሳካ ታይምስ ጋዜጣ አርብ ዘግቧል። የእስር ቅጣት የተላለፈባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያዊያኑ እድሜያቸው ከ 30 አመት በታች ...

Read More »

ስራ ላልጀመሩት የስኳር ኮርፖሬሽን ሰራተኞች 160 ሚሊዮን ብር  በላይ ደሞዝ ወጪ ሆኖ እየተከፈለ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቦላቸው በስድስት አመት ጊዜ ውስጥ ወደስራ መግባት ያልቻሉ የስኳር ፋብሪካዎች በየወሩ ከ160 ሚሊዮን ብር በላይ ለደሞዝ ክፍያ ወጪን እያደረጉ እንደሆነ ተገለጠ። በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የስኳር ኮርፖሬሽን የፋብሪካዎች ግንባታ ሳይጠናቀቅ የሰራተኛ ቅጥርን እንዳይፈጽም አሳስቧል። መንግስት ከተለያዩ አካላት ብድርን በማሰባሰብ የስኳር ፋብሪካዎቹን ለማቋቋም ጥረትን ቢያደርግም፣ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በጎርፍ ከ 100 ሰዎች በላይ መሞታቸውን አስታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ፣ ከ100 በላይ ዜጎች በመሬት መደርመስና መሞታቸውንና በደራሽ ጎርፍ መወሰዳቸውን መንግስት አስታወቀ። በወቅታዊ ጎዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በተከሰተው በዚሁ ጎርፍ አያሌ ዜጎች ተጎድተዋል በማለት ተናግረዋል።  አቶ ጌታቸው ማክሰኞ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር አለመግባባት ላይ ናቸው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) በቅርቡ ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን ለማስለቀቅ በሚል ወደጎረቤት ደቡብ ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከነዋሪዎች ጋር አለመግባባት ውስት መሆናቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። ከጋምቤላ ክልል በቅርቡ ርቀት ላይ ከሚገኘው የፓቻላ ግዛት የሚኖሩት ነዋሪዎች ወታደሮች በእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው የጸጥታ ስጋትን አሳድረውባቸው እንደሚገኝም አስታውቀዋል። በፓቻላ አስተደደር አካባቢ ወሰጥ ሶስት ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ...

Read More »

በአዋሽ ወንዝ ሙላት ከሶስት ሺ ነዋሪዎች በላይ ተፈናቀሉ

ኢሳት (ግንቦት 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ለአዋሽ ወንዝ መሙላት ምክንያት ሆኖ 300ሺ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። በክልሉ አሚባራ ወረዳ የደረሰው ይኸው የጎርፍ አደጋ በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይም ከባድ ጉዳት ማድረሱን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች የነፍስ አድን ሰራተኞችም ነዋርዎችን ለከፋ አደጋ ለመታደግ ርብርብን እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን የወንዙ ሙላት በቀጣዮቹ ቀናቶችም እየጨመረ ...

Read More »

በዲላ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መንገድ ዘግተው ፈተሻ ሲያደርጉ ዋሉ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት፣ የመከላከያ ስራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዶችን ዘግተው ፍተሻ ሲያደርጉ እንዲሁም በመኪና ላይ ሆነው ቅኝት በማድረግና የሚጠርጥሩዋቸውን ወጣቶችም ይዘው ሲጠይቁ መዋላቸውን ተናግረዋል። ወታደራዊ ፍተሻውና ቅኝቱ፣ በመንግስት ታጣቂዎችና በአርበኞች ግንቦት 7 መካከል በአርባምንጭ አካባቢ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ የተካሄድ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፍተሻውን እና ጥበቃውን በተመለከተ በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናትን ...

Read More »

በዶ/ር ቴዎድሮስ ሲመራ የነበረው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከግሎባል ፈንድ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጪ መጠቀሙና ማጉደሉ ተገለጠ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጤና ጠበቃ ሚኒስቴርን መርተው ለውጤት እንዳበቁት በመግለጥ ፣ የአለም የጤና ድርጅት መሪ ለመሆን የቅስቅሳ ስራ የጀመሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋት በሚል ከግሎባል ፈንድ ለህዝብ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀማቸውን የሚያመለክት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦባችዋል። ግሎባል ፈንድ በአውሮፓውያን አቆጣጥር በ2010 ፣ 1 ቢሊዮን 3 ...

Read More »

በካራሚሌ 4 ሴቶች በወታደሮች ተደፍረው ሆስፒታል ገቡ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ ሰሞኑን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከምስራቅ እዝ የተላኩት ወታደሮች 5 ውጣት ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውንና ጉዳተኞችም ሆስፒታል መተኛታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ የ 7ኛ ክፍል ተማሪ በ4 ወታደሮች በቡድን በመደፈሩዋ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በከተማው ያለው ወጥረትም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ ስዎች ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ...

Read More »

በደንቢያ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን አድማ አደረጉ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ያደርጉ ሲሆን፣ መንግስትን የሚያውግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። አድማውን ትከትሎ ትምህርት በመቁዋርጡ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጎአል። ባድማው የተሳትፉ መምህራንን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም፣ ከሰአት በሁዋላ ወደ ስብሰባ በመግባታቸው ሳይሳካልን ቀርቶአል። መምህራኑ መብታችን ሳይከብር ስራ አንጀምርም ማለታቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

Read More »