በካራሚሌ 4 ሴቶች በወታደሮች ተደፍረው ሆስፒታል ገቡ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ ሰሞኑን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከምስራቅ እዝ የተላኩት ወታደሮች 5 ውጣት ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውንና ጉዳተኞችም ሆስፒታል መተኛታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ የ 7ኛ ክፍል ተማሪ በ4 ወታደሮች በቡድን በመደፈሩዋ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በከተማው ያለው ወጥረትም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ ስዎች ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 3 የመንግስት ደጋፊዎች መገደላቸው ይታወቃል።