እንደ ቢቢሲ ዘገባ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው አይሁዳውያን እንደሆኑ የሚያምኑ በትንሹ 9ሺህ ያህል ኢትዮጵያውያን ወደ እስራኤል ለመጓዝ ለዓመታት እየጠበቁ ይገኛሉ። ናትኒያሁ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር በሰጡት መግለጫ የአይሁድ ኢትዮጵያኑ ጉዞ በቅርቡ እንደሚከናወን ገልጸዋል። ይሁንና መቼ እንደሚሆን ትክክለኛውን የጊዜ ሰሌዳ አልተጠቀሱም። “አይሁድ ኢትዮጵያውያንን ወደ እስራኤል የመመለሱን ጉዳይ እየሰራንበት ነው፤ያን ለማድረግ ቁርጠኝነቱ አለን። በቤተሰብ መቀላቀል ሂደቱ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ እያሟላን ነው። ይህ የሚሆነው ለወደፊት አይደለም።በወቅቱ ...
Read More »የተመድ የምግብና የእርሻ ክፍል በጎርፍ ለተጎዱት ዜጎች ተጨማሪ ገንዘብ ጠየቀ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ክፍል በቅርቡ በተከሰተው ረሃብ የተጎዱ ዜጎች ሳያገግሙ በድጋሜ በጎርፍ በመጠቃታቸው ለመስከረም ወር ተጨማሪ የ3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል። ድርጅቱ የኢትዮጵያን የጎርፍ አደጋ መከላከል ግብረሃይልን ጠቅሶ እንደዘገበው በጎርፉ ምክንያት 690 ሺ ተፈናቅለዋል። 55 ሺ ሄክታር መሬትም በጎርፍ መጥለቅለቁን ድርጅቱ አስታውቋል። በድርቁ የተጎዱ ዜጎች ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ በትንሹ ሁለት አመት ያስፈልጋቸዋል። ድርጅቱ የውሃ አቅርቦትን ለመጨመር ...
Read More »የኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አሊ ኢስላም ተፈታ።
ፍራንስ 24 የተሰኘው ሚዲያ እንደዘገበው በሊቢያ ሳይፍ አሊ ኢስላምን ያሰሩት ኃይሎች እንደለቀቁት ጠበቃው ለዓለም አቀፉ ይወንጀለኞች ፍርድ ቤት በምህጻረ ቃሉ አይ ሲሲ አሳውቋል። ሳይፍ አሊ ኢስላም አባቱን ጋዳፊን ባስወገደው አብዮት ወቅት ፈጽሞታል በተባለው ወንጀል የሞት እስራት ተፈርዶበት እንደነበር ይታወሳል። የጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ የሆነው ሳይፍ አሊ ኢስላም ነጻነቱን ያገኘው ባለፈው ሚያዚያ ወር እንደኾነ ጠበቃው ካሪም ካን ትናንት ተናግረዋል። ሳይፍ የተፈታውም በዓለማቀፍ ...
Read More »በአምቦ ዩኒቨርስቲ አንድ የጸጥታ አባል ሁለት የፌዴራል ፖሊሶችን ገደለ
ኢሳት (ሰኔ 29, 2008) በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ዕርቀት ላይ በሚገኘው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ተመድቦ በማገልገል ላይ የነበረ አንድ የጸጥታ አባል ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ገድሎ ማምለጡን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ። አዋሮ ተብሎ በሚጠራው የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሰኞ በጸጥታ ባልደርባው በተፈጸመው ጥቃት ሶስት ተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በጥይት ጉዳይ እንደደረሰባቸው ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአምቦ ከተማ ነዋሪ ከዜና ክፍላችን ጋር ...
Read More »የኢድ አል ፈጥር በአል በመላው አለም እየተከበረ ነው
ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አለም የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች 1 ሺህ 437ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እያከበሩ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም በአሉን በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች አደባባዮች በመሰባሰብ በጋራ ያከበሩ ሲሆን፣ በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ እና በአርሲ ሙስሊሜ ከበአሉ በሁዋላ በመንግስት ላይ ያለውን ተቃውሞ አሰምቷል። ሰሞኑን በኢራቅ፣ ሳውድ አረቢያና ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር ዜጎችን የማፈናቀሉን እርምጃ እንዲያቆም የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ጠየቀ
ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብዛሃኞቹ ዜጎች ካርታ ባይኖራቸውም ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸውንና የመብራትና ውሃን የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ሲያገኙ እንደነበር ሰመጉ ገልጿል። “እነዚህ ዜጎች አስቀድሞ ሕጋዊነትን በያዘ መልኩ መኖሪያዎችን እንዲሰሩ መደረግ ነበረበት። ይህ ከሆነ በኋላሕገወጥ ናችሁ በማለት አፍራሽ ግብረኃይል አሰማርቶ በክረምት ነዋሪዎች ላይ ቤት ማፍረስ ኢሰብዓዊ ነው” ሲል ሰመጉ ድርጊቱን በጽኑ ኮንኗል። በ አፍራሽ ግብረኃይሉ ...
Read More »የኢህአዴግ ታማኝ አባላት ናቸው የተባሉ መምህራን ተመርጠው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንዲሰጡ ሊደረግ ነው
ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአንድ ወር በፊት ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃው ብሄራዊ ፈተና መሰረቁን ተከትሎ፣ የድጋሜ ፈተና ያዘጋጀው ትምህርት ሚኒስቴር፣ ፈተናውን ለስርዓቱ ይታመናሉ በተባሉ መምህራን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ነው። ከመላው አገሪቱ በጥንቃቄ የተመረጡ መምህራን ሰኔ 28 ቀን 2008 ዓም አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን ፣ በዳግምዊ ሚኒሊክ መሰናዶ ት/ቤት ቅጥር ግቢ በጊዜያዊነት በተዘጋጀው ጣቢያ ...
Read More »የኢህአዴግ ፍ/ቤት በህመም የሚሰቃየው ሃብታሙ አያሌው ውጭ አገር እንዲታከም ዕግድ አላነሳም
ኢሳት (ሰኔ 28 ፥ 2008) ለሳምንታት ከፍተኛ የህመም ስቃይ ላይ የሚገኘው ሃብታሙ አያሌው የውጭ ሃገር ህክምና እንደሚያስፈልገው በሃኪሞች ማረጋገጫ ቢሰጠውም ፍርድ ቤቱ ዕግድን እስካሁን አላነሳም። የሃኪም ማስረጃውን አይቶ ዕግድን ለማንሳት የተሰየመው ችሎት አልተሟላም በሚል ያለቀጠሮ መነሳቱንም ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያስረዳል። የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበረውና ከሃብታሙ ጋር በወህኒ ቤት እስር ላይ ቆይቶ የተለቀቀው ዳንዔል ሺበሺ ለኢሳት እንደተናገረው የውጭ ሃገር ህክምና ...
Read More »የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ለሁለት የኢሳት ባልደርቦች በቤተሰቦቻቸው በኩል ማስጠንቀቂያ ላከ
ኢሳት (ሰኔ 28 ፥ 2008) በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ለሁለት የኢሳት ባልደርቦች በቤተሰቦቻቸው በኩል ማስጠንቀቂያ ላከ። የደህንነት አባላቱ ኢትዮጵያ በሚገኙት የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች ቤት በመሄድና በመጥራት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓም በተመሳሳይ ቀን በሃገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በኩል ማሳሰቢያው የደረሳቸው የኢሳት ባልደርቦች ታማኝ በየነና ሲሳይ አጌና በጋራ በጻፉት ደብዳቤ መልዕክቱ እንደደረሳቸው ገልጸው፣ ማናቸውም ...
Read More »አንድ የአረና ፓርቲ አባል ባለፈው ሳምንት ተገደለ
ኢሳት (ሰኔ 28 ፥ 2008) የአረና ፓርቲ አባል በሳምንቱ መጨረሻ ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ተገለጸ። የአረና ፓርቲ በማህበራዊ መድረኩ እንዳስታወቀው ወጣት ዝናቡ ሃይሉ ባልታወቁ ሰዎች የተገደው በሳምንቱ መጨረሻ ሲሆን፣ ኩርመዓጋ በተባለ የአፋር ክልል ውስጥ ሞቶ መገኘቱም ተመልክቷል። በቅፅል ስሙ ሴንቸሪ በሚል የተጠቀሰው ዝናቡ ሃይሉ አርብ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓም ከጓደኞቹ ጋር ምሳ ከበላ ከሰዓታት በኋላ ሞቶ መገኘቱን ከዘገባው መረዳት ተችሏል። ...
Read More »