በእስራዔል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ወጡ

ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በእስራዔል እየሩሳሌም ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን  መንግስት በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ሃሙስ በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ። ለአመታት የቆየው የማንነት ጥያቄ አፈና ሲካሄድበት መቆየቱን የተናገሩት ሰልፈኞች ወልቃይትና አማራ የማይነጣጠሉ መሆናቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል።  የተለያዩ መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበሩት ሰልፈኞች በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማውገዝ እየተካሄደ ላለው ህዝባዊ ንቅናቄ አጋርነታቸውን እንዳሳዩ ...

Read More »

በታንዛኒያ የሚገኙ 500 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ አለም አቀፍ ድጋፍ ተጠየቀ

ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) የታንዛኒያ መንግስት በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ 500 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ አለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍን ጠየቀ። የሃገሪቱ የስደተኛና ኢሚግሬሽን መምሪያ በየጊዜው ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ በመጨመር ላይ መሆኑ እንደገለጸ ዘሲትዝን የተሰኘ የታንዛኒያ ጋዚኤጣ ሃሙስ ዘግቧል።  በተለያዩ ጊዜያት ወደ ታንዛኒያ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር ...

Read More »

ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ በግብፅ ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ከተረጋገጠ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አለች

ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የለም ሲል የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ከተረጋገጠ የማስተካከያ እርምጃን እንደሚወስድ ለግብፅ መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ።  የውሃ ሃብት ሚንስትሩ አቶ ሞቱማ መካሳ ሃገራቸው ግድቡ በተለይ በግብፅና ሱዳን ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ መኖሩ በባለሙያዎች ከተረጋገጠ ተፅዕኖውን ለመቀነስ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለግብጹ አክባር አልዩም ጋዜጣ በሰጡት ቃለምልልስ ...

Read More »

የተመድ ሰራተኞች  ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በሚደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቀ

ኢሳት (ሃምሌ 28 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች በሚቀጥሉት ቀናት በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰልፍ በሚካሄድባቸው ቦታዎች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታና ደህንነት ክፍል ባለስልጣን ገለጹ።  ማርኮ ስሞልነር የተባሉ የተባበሩት መንግስታት የደህንነትና የጸጥታ ክፍል ባለስልጣን ባሰራጩት የኢሜይል መልዕክት፣ በሚቀጥለው ቅዳሜና እሁድ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የዞንና የወረዳ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ሊደረጉ ስለሚችሉ፣ የተመድ ሰራተኞች የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ...

Read More »

አዲስ አበባን ጨምሮ በኦሮምያ፣ ባህርዳርና ደብረታቦር የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የተሳካ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው

ሐምሌ  ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊታችን ቅዳሜ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ኦሮምያ፣ በባህርዳር ከተማ እና በደብረታቦር ከተማ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀነቅኑ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ። በእነዚህ ሰልፎች ላይ የህወሃት አገዛዝ እንዲያበቃ ጥሪ ይቀርባል። ሰልፉ በኦሮምያ የደረሰውን ጭፍጨፋ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ምንነት የኮሚቴ አባላት መታሰራቸውን ያወግዛል። በኦሮምያና በባህርዳር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰልፉን ቀን በጉጉት እየጠበቁት ...

Read More »

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱ ከባድ የህልውና አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል አሉ ሌሎች ወገኖች ግን አደጋው ለኢህአዴግ ህልውና  እንጅ ለኢትዮጵያ አይደለም ይላሉ

ሐምሌ  ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ሲካሄድ በሰነበተው የዲያስፖራ በአል ላይ የተገኙት ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ኢትዮጵያ ከባድ የህልውና አደጋ እንደተደቀነባት ተናግረዋል። የጠባብነትና የትምክህትነት አደጋ ከፊታችን እንዳለ ዛሬ ሳይሆን አስቀድመን አውቀናል ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ ይህ ደግሞ አገራችንን ወደ ማትመለስበት የብሄር ግጭት አደጋና የእርስ በርስ ጦርነት ይከታታል ሲሉ ገልጸዋል። ሁላችንም ይህን ጠባብነትና ትምክት ተረባርበን ካላስቆምነው እስከዛሬ የተጓዝንበትን ሁሉ ...

Read More »

በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ድጋፋቸውን ገለጹ የሚፈጸመውን  ግድያም አወገዙ

ሐምሌ  ፳፰ ( ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ቤተ እስረኤላውያን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄን ደግፈው፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሁሉ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። በኦሮምያ የሚፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል። የታሰሩት ሁሉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ኪዳነምረት ቤተክርስቲያን በማምራት ገዢው ፓርቲ የሚጠቀምበትን ሰንደቅ አላማ በማውረድ ኮከብ የሌለውን ሰንደቃላማ ሰቅለዋል። ድርጊቱን በተመለከተ ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው አቶ ማስተዋል ጥላሁን ድርጊቱን ...

Read More »

በወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ዙሪያ የአመራር ክፍፍል መኖሩን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ

ሐምሌ  ፳፯ ( ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የዲያስፖራ ውይይት ላይ ፣  የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጥያቄ ህዝባዊነት የሌለውና በ አመራሮች የሃሳብ ልዩነት የመጣ መሆኑን በመግለጽ መፍትሄውም አመራሩን ማስተካከል ነው ብለዋል። ጠ/ሚኒስትሩ የትኛው አመራር ምን አይነት አቋም እያራመደ እንደሆነ ከመገልጽ ቢቆጠቡም፣ ከዚህ በፊት በተወሰኑ ከፍተኛ የብአዴን አመራሮችና በህወሃት አመራሮች መካከል ልዩነት መፈጠሩ ሲነገር ...

Read More »

በአወዳይ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ አጋጥሟል ተባለ

ሐምሌ  ፳፯ ( ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ባለፈው እሁድ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ11 ሰዎች በላይ ከተገደሉ በሁዋላ፣ አካባቢውን የተቆጣጠሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊሶች ማንኛውም ሰው ከቤቱ እንዳይወጣ እገዳ በመጣላቸው፣ ህጻናትና እናቶችን ጨምሮ ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መግባቱ ታውቋል። ወኪላችን እንደገለጸው አብዛኛው ህዝብ ከቤት አትወጣም በመባሉ የሚበላው አጥቶ ...

Read More »

በኦሮሚያ በዴሳ ከተማ ሁለት ሰዎች በመንግስት ጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ኢሳት (ሃምሌ 26 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሃረርጌ ዞን ስር በምትገኘው የበዴሳ ከተማ ማክሰኞ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ።  በከተማዋ ሰኞ የተገደሉት ሁለት ሰዎችን ማክሰኞ ለመቅበር በተካሄደ ስነ-ስርዓት ላይ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች እንዲሞቱ ማድረጋቸውን እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የአራቱ ሟቾችን ስም በመጥቀስ ስለድርጊቱ እማኝነታቸውን የሰጡት የበዴሳ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ከፍተኛ የጸጥታ ...

Read More »