በጎንደር የስራ ማቆም አድማው ለሶስተኛ ቀናት ቀጥሎአል

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመሳሳይ ተቃውሞች በሌሎች ከተሞችም ይደረጋሉ በጎንደር በአደባባይ ሲደረግ የነበረው ተቃውሞ ወደ ስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ከተቀየረ በሁዋላ ፣ ሁሉንም የከተማዋ ነዋሪዎች በአንድነት ያሳተፈ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የንግድ ድርጅቶች አልተከፈቱም፣ ታክሲዎች አውቶቡሶች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ስራ አቁመዋል። ...

Read More »

በጋምቤላ 20 የኦሮሞ ተወላጆች የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ታሰሩ

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ 20 የኦሮሞ ተወላጅ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች አምልኮ ከሚያደርጉት ቤተክርስቲያን ተይዘው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በእጃቸው ላይ ከመጽሃፍ ቅዱስ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር ያልያዙት አማኞች፣ ኦሮሞ ስለሆኑ ብቻ መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የቤተክርስቲያን ምንጮች ገልጸዋል። ሰዎቹ ለአንድ ሳምንት ያክል በጋምቤላ እስር ቤት ሲቆዩ ፍርድ ...

Read More »

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውንና እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስዊዘርላንድ ዤኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ድርጅት ፊትለፊት በመገኘት አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ግድያውን ያቁም፣ የሚፈሰው የወገኖቻችን ደም የሁላችንም ደም ነው፣ በህወሃት ሕገመንግስት አንገዛም! የሚሉ በርካታ መፈክሮች በስፍራው ተስተጋብተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አድረገዋል። በተመሰሳይም በተጨማሪም ኦጎስት19 ቀን 2016 በስዊድን ዋና ...

Read More »

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከቤት ያለመውጣት አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥለው ዋሉ

ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008) ላለፉት ሁለት ሳምንታት ህዝባዊ ተቃውሞን ሲያካሄዱ የቆዩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እሁድ የጀመሩትን ከቤት ያለመውጣት አድማ ሰኞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ሰኞ ለኢሳት አስታወቁ። የከተማዋ ነዋሪዎች የጀመሩትን ይህንኑ ከቤት ያለመውጣት አዲስ አድማ ተከትሎ በከተማዋ የሚገኙ የመንግስትና የግል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ስራ ማቆማቸው ታውቋል። የከተማዋ አስተዳደር ባለስልጣናት ነዋሪዎች የተለመደ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ በድምፅ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን አሰናበተ

ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008) ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደውን የትራንስፖርት የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በሰራተኞቹ ላይ ግምገማን ሲያካሄድ የቆየው የከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰራተኞችን አሰናበተ። የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፈጽመዋል የተባሉ እነዚሁ ሰራተኞች በቅርቡ ክስ እንደሚመሰርትባቸው የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ ሰኞ መግለጹን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በከተማዋ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ታክሲዎችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተቋማት አስተዳደሩ ...

Read More »

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚደረገውን ግድያና እስር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ካናዳ፣ አውሮፕላ እንዲሁም አፍሪካ የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በመቃወም በሳምንቱ መገባደጃ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ። በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማና አካባቢው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ህዝቡ ያቀረበውን ሰላማዊ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽን እንዲያገኝ ጠይቀዋል። ሰላማዊ ጥያቄን እያቀረቡ ካሉ ዜጎች ጎን መቆማቸውን ሲገልጹ ያረፈዱት ...

Read More »

በውጭ ሃገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ህወሃት ኢህአዴግ ከስልጣን ተወግዶ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ

ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008) በውጭ ሃገራት የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የህወሃት ኢህአዴግ መንግስት ከስልጣን ተወግዶ በምትኩ ከፖለቲካ ድርጅቶች ሲቪክ ማህበራትና ብቃት ካላቸው ግለሰቦች የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም መግለጫ አወጡ። “ለ25 አመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና ለ40 አመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባልስልጣኞች ያሉበት ህወሃት/ኢህአዴግ በተለይ በዚህ አመት በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናውግዛለን፣ የህዝቡንም ...

Read More »

በምስራቅ ሃረርጌ  ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለሁለተኛ ሳምንት ቀጥሎ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳረጉ

ኢሳት (ነሃሴ 6 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ከሳምንት በፊት ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለሁለተኛ ሳምንት መቀጠሉንና በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸው ተገለጸ። ህጻናቶች ሳይቀሩ ለእስር መዳረጋቸውን የሚናገሩት የዞኑ ነዋሪዎች በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሚስወዱት ዕርምጃ እንዲቆም በመጠየቅ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ለሁለተኛ ሳምንት ቀጥሎ የሚገኘው ...

Read More »

የህወሃት/ኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በባህርዳር አዳዲስ አስር ቤቶችን እየተከፈቱ ነው ተባለ

ኢሳት (ነሃሴ 6 ፥ 2008) የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በባህር ዳር ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች የጅምላ እስር በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታውቀዋል። በከተማዋ አዳዲስ እስር ቤቶች መከፈታቸውን የተናገሩት እማኞች ተቃውሞውን ተከትሎ በተለይ ወጣት የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለእስር መዳረጋቸውን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። ይሁንና የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን የዕስር ዘመቻ ተከትሎ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱ ...

Read More »

በባህርዳር ከተማ የተገደሉት ሰዎች ከ55 እንደሚበልጡና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ዜጎች ታስረው እንደሚገኙ ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 6 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በባርዳር ከተማ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተፈጸመ ግድያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር በከተማዋ ብቻ 55 መድረሱንና ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ነዋሪዎች እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረብ መጀመራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። በሳምንቱ መገባደጃ በባህርዳር እና ጎንደር ከተሞች እንዲሁም በዙሪያዋ ባሉ የገጠር መንደሮች ግድያ ሲፈጸም መቆየቱን ያወሱት እማኞች በሆስፒታል ብቻ 55 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ መቻሉን ገልጸዋል። በርካታ የግድያው ሰለባ ...

Read More »