በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ነሃሴ  ፲ ( አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውንና እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስዊዘርላንድ ዤኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ድርጅት ፊትለፊት በመገኘት አገዛዙ ስልጣኑን እንዲለቅ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ግድያውን ያቁም፣ የሚፈሰው የወገኖቻችን ደም የሁላችንም ደም ነው፣ በህወሃት ሕገመንግስት አንገዛም! የሚሉ በርካታ መፈክሮች በስፍራው ተስተጋብተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አድረገዋል።

በተመሰሳይም በተጨማሪም ኦጎስት19 ቀን 2016 በስዊድን ዋና ከተማ ስቶከልም እና በሆላንድ ደንሃግ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን የሚያሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚዘጋጅ አዘጋጆቹ ለኢሳት በላኩት መረጃ ገልጸዋል።