ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ዝውውር ላይ አፈና መፈጸሟን የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አስታወቀ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ  አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ተከትሎ  በሕገወጥ መንገድ ድረገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎትን በተለያዩ ዘዴዎች በመጠቀም መዝጋቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። ሕዝባዊ ተቃውሞው ከተነሳበት እ.ኤ.አ. ኖቨምበር 2015 ጀምሮ ማኅበራዊ ድረገጾችን፣ የግል የዜና አውታር ድረገጾችን በመዝጋት ሕገወጥ የሆነ የመብት ጥሰቶች መፈጸሙን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። አስቸኳይ የጊዜ አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ...

Read More »

ባለቤትነቱ የሸህ መሀመድ አል አሙዲ የሆነው የሀዋሳው ሚሊኒየም ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ከተዘጋ ሳምንት አለፈው።

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፋብሪካው ሰራተኞች እንደተናገሩት መንግስት ፋብሪካውን በመዝጋቱ ሳቢያ ከ450 በላይ የሆኑ ስራትኞች በስጋት ተውጠው ይገኛሉ። መንግስት የሸህ አልአሙዲ ንብረት የሆነውን ይህን ፋብሪካ የዘጋው የጥራት ደረጃውን አልጠበቀም በሚል ነው። የፋብሪካውን መዘጋት ተከትሎ ፔፕሲ ኢንተርናሽናል ወደ ስፍራው በመምጣት ባደረገው ምርመራ ፋብሪካው ደረጃውን የጠበቀ እንደሆነ ማረጋገጫ ቢሰጥም መንግስት እንዳይከፈት አዟል ተብሎ ከሳምንት በላይ ታሽጎ ይገኛል። ቀደም ...

Read More »

የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ቦታ አናውቅም አሉ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ህብረት መንግስት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ቦታ እንዲያሳውቅ መጠየቁን የዘገበው አሶሺየትድ ፕሬስ፣ የኢትዮጰያ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር  የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ግዛቸው መንግስቴ  ጋዜጠኛ ተመስገን ያለበትን ቦታ እንደማያውቁ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥቅምት 2014 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ህብረቱ  ዛሬ እንዳለው  ከሁለት ኣመት እስር ...

Read More »

የትምህርት ጥራቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መሄዱ ተነገረ፡፡

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በሚካሄደው የመማር ማስተማር ሂደት የትምህርት ጥራቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መምጣቱን ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ በክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በሚካሄዱ የመምህራን ቅጥር ከአስረኛ ወደ አስራ አንደኛ ክፍል መሸጋገር ያልቻሉ ተማሪዎችን ያካተተ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያዎች፣ የሚቀጠሩት ረዳት መምህራን ምንም ዓይነት ስልጠና ሳይሰጣቸው ወደ ሙያው ገብተው እንዲሰሩ በመደረጋቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ...

Read More »

በደቡብ አፍሪካ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን የገደሉ ሶስት ዘራፊዎች ተያዙ

ታኅሣሥ  ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካዋ ሞዶርኩል መንደር በሱቅ ውስጥ በስራቸው ላይ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን ገድለው በመዝረፍ ያመለጡት ሶስት ወንጀለኞች ሰኞ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቦሎሴንቴ ፍሪ ስቴትስ ፖሊስ አስታውቋል።ሟቾቹ ኢትዮጵያዊያን የ27 እና 31 ዓመት ወጣቶች ሲሆኑ ዘራፊዎቹ ንብረቶቻቸውን ዘርፈው ከአካባቢው መሰወራቸውንም ፖሊስ ገልጿል። ተጠርጣሪ ወንጀሎኞቹ በሕዝብ ትብብር መያዛቸውን እና እድሜያቸውም የ27፣32 እና 33 ዓመት ...

Read More »

አሜሪካ ለሳውዲ አረቢያ የምታደርገውን የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ለመቀነስ ወሰነች

ኢሳት (ታህሳስ 5 ፥ 2009) ሳውዲ አረቢያ በየመን እየወሰደች ያለው ወታደራዊ ዕርምጃ ያስነሳውን ቅሬታ ተከትሎ አሜሪካ ለአገሪቱ የምታደርገውን የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ለመቀነስ ወሰነች። ካለፈው አመት ጀምሮ ሳውዲ አረቢያ ካለፈው አመት ጀምሮ ሳውዲ አረቢያ በየመን አማጺያን ላይ እየፈጸመች ያለው የአየር ጥቃት ለበርካታ ንጹሃን ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የመናዊያን ሲገልፁ ቆይተዋል። በተለይ በጥቅምት ወር በአንድ የቀብር ስነስርዓት ...

Read More »

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 አመታት ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው ሃገራት ተርታ እንደማትገባ ተመድ ይፋ አደረገ

ኢሳት (ታህሳስ 5 ፥ 2009) ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 አመታት ወደ መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው ሃገራት ተርታ እንደማትገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ። የመንግስት ባለስልጣናት ሃገሪቱ በቀጣዮቹ አስር አመራት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ትገባለች ሲሉ በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንና በጉዳዩ ዙሪያ ሰሞኑን ሪፖርቱን ያወጣው የድርጅቱ የንግድና የልማት ጉባዔ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ 16 ሃገራት እቅዱን እንደሚያሳኩ ቢገልጽም፣ ኢትዮጵያን ሳያካትት ቀርቷል። ከአፍሪካ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ገቢ 400 ሚሊዮን ዶላር (ወደ አንድ ቢሊዮን ብር) አካባቢ ልታጣ እንደምትችል ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 5 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆች አመት ከቱሪዝም ገቢ 400 ሚሊዮን ዶላር (ወደ አንድ ቢሊዮን ብር) አካባቢ ልታጣ እንደምትችል ተገለጸ። በሃገሪቱ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አለመረጋጋት በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን እያሳደረ እንደሚገኝ አፍሪካ ኒውስ መጽሄት የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ረቡዕ ባቀረበው ዘገባ አስፍሯል። በፈረጆች 2015 አም ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ወደ ሶስት ቢሊዮን ዶላር አካባቢን አግኝታ ...

Read More »

በአሜሪካ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የተመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 5 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ዙሪያ ለመምከር በአሜሪካ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ የተመራ የልዑካን ቡድን ረቡዕ አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃገሪቱ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መውጣትን ተከትሎ ዕርምጃው በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ስጋትን አሳድሯል ሲል በተደጋጋሚ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በአዲስ አበባ የሶስት ቀን ቆይታ የሚኖረው ይኸው የልዑካን ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በጸጥታ ሃይሎች የተወሰዱ የሃይል ዕርምጃዎች ሽፋን እንዳያገኙ ድረገጾችን መዝጋቱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 5 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ መንግስት በጸጥታ ሃይሎች የተወሰዱ የሃይል ዕርምጃዎች ሽፋን እንዳያገኙ በትንሹ የ16 የመገናኛ ብዙሃንን ተቋም ድረገጾች እንዲዘጉ ማድረጉንም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ረቡዕ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። የማህበራዊ ድረ-ገጾችን ጨምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ለመዝጋትና ለመቆጣጠር በተካሄደው በዚሁ የአፈና ዕርምጃ የተቃዋሚ ፓርቲ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ሰለባ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ...

Read More »