ታኅሣሥ ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማላዊን አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገ ወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ቁጥራቸው 100 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከዓለምአቀፉ የደተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የማላዊ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቤስተን ችላቢሊ አስታወቁ። ሚንስትሩ ቀደም ብሎ 300 ኢትዮጵያዊና ስደተኞች ከማላዊ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸዋል። በማሉፓ እስር ቤት ውስጥ150 ስደተኞች መኖራቸውን ...
Read More »በቡሌ ሆራ እስር ቤቶች ሞልተው ተጨማሪ እስር ቤቶች እየተከፈቱ ነው
ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ከተማ ከተለያዩ ቀበሌዎች እየተያዙ የሚታሰሩ አርሶአደሮች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ በቅርቡ ከተከፈቱት ሁለት እስር ቤቶች በተጨማሪ ሌሎች እስር ቤቶች መከፈታቸውንና እነሱም መሙላታቸውን ተናግረዋል። ልጆቻቸውን የሚያጠቡ እናቶች፣ ወጣቶች፣ አዋቂዎችና በእድሜ የገፉ አዛውንት ሳይቀር መታሰራቸውን የሚገልጹት እነዚሁ ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ሰአት አቅሙ ያላቸው ሰዎች አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን፣ አቅሙ የሌላቸው ግን ...
Read More »የብር የምንዛሬ ዋጋ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ነው
ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ከተከሰተው ህዝባዊ አመጽ በሁዋላ የዶላር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል። በህጋዊ ገበያ በ23 ብር ገደማ የሚመነዘረው ዶላር በጥቁር ገበያ ከ28 ብር በላይ እየተመነዘረ ነው። በርካታ ባለሃብቶች ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ብር ወደ ዶላር በመመንዘር ሃብታቸውን ወደ ውጭ ማሸሻቸው፣ ወደ አገሪቱ የሚገባው ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ፣ ዲያስፖራው ወደ አገሩ የሚልከው ገንዘብ በመቀነሱ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ...
Read More »ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጀውን የስራ ዕድል ባለስልጣናት ያደራጇቸው ቤተሰቦች እና ስራቸውን የለቀቁ መሃንዲሶች እየተጠቀሙበት ነው ተባለ፡፡
ታኅሣሥ ፮ (ስድስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በተለያዩ የክልል ቢሮዎችና የዞን መምሪያዎች በግንባታ ስራ ላይ ተቀጥረው የሚገኙ መሃንዲሶች ስራቸውን በመልቀቅ ላይ ያሉት በቅርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የስራ ዕድል አማራጮችን ለማስፋፋትና ለማበረታታት በሚል የተዘጋጀውን መመሪያ ቁጥር 27/2009 ተንተርሶ ነው፡፡ መመሪያው ከተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ የሌላቸውን ወጣቶች ወደ ስራ ለማስገባትና የስራ ዕድል አማራጮችን ለመፍጠር የሚል ቢሆንም፤ ወጣቶችን ...
Read More »የብሪታኒያ ፓርላማ አባላት በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ላይ ስለሚወሰደው ዕርምጃ ክርክር ሊያካሄዱ ነው
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ዙሪያ መውሰድ በሚገባው ዕርምጃ ላይ ለመምከር የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት በቀጣዩ ሳምንት የክርክር መድረክ ሊያካሄዱ መሆኑ ተገለጸ። ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ አቶ አንዳርጋቸው በብሪታኒያ መንግስት ተወካዮች ዘንድ እንዲጎበኝ መደረጉ በፓርላማ አባላትና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ስጋትን ማሳደሩን የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው። የጉዳዩ አሳሳቢነትን ተከትሎ የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት የሃገሪቱ መንግስት ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት የስለላ ተግባርን ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕ ፓኬት ኢንስፔክሽን (Deep Packet Inspection) የተሰኘና የኢንተርኔት የስለላ ተግባርን ለማከናወን የሚረዳ ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ተገለጸ። ቴክኖሎጂው በህጋዊ መንገድ የደህንነት ተያያዥ ስራዎችን ለማከናወን በተለያዩ አለም አቀፍ ኩባንያዎች በመቅረብ ላይ ቢሆንም፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት አገልግሎቱን እየገዙ ለኢንተርኔት የስለላና ቁጥጥር ስር በማዋል መሆናቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል። ቴክኖሎጂውን ለስለላ ተግባር እየተጠቀመ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ደንብ ማስከበር ስልጠና ተሰጥቷቸው በማህበር የተደራጁ ወጣቶች እንዲበተኑ ተደረገ
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ልዩ የትራንስፖርት የደንብ ማስከበር ስልጠና ተሰጥቷቸው በ21 ማህበራት የተደራጁ ከ300 በላይ ወጣቶች ያለአግባብ እንዲበተኑ መደረጉን የማህበሩ አባላት ለኢሳት አስታወቁ። ከተደራጁና በተለያዩ የመዲናይቱ የትራስፖርት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከተሰማሩ ስድስት አመት እንደሆናቸው የሚናገሩት አባላቱ ከታህሳስ 1, 2009 ዓም ጀምሮ ማህበራቸው እንዲበተን ውሳኔ እንደደረሰባቸው ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። የደንብ ማስከበር ስራውን ...
Read More »የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስፋፊያ የ159 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው አመት ሊያካሄዳቸው ላቀደው የማስፈፊያ ስራዎች የአፍሪካ ልማት ባንክ የ159 ሚሊዮን ዶላር ብድርን አጸደቀ። በአፍሪካ እየታየ ያለው የመንገደኞች ቁጥር መቀነስና በሃገሪቱ ተከስቶ ያለው አለመረጋጋት በአየር መንገዱ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ብሉምበር የዜና ወኪል ከቀናት በፊት መዘገቡ ይታወሳል። እነዚህ ክስተቶች በተያዘው አመት በአየር መንገዱ ገቢ ላይ መቀዛቀዝን ሊፈጥር እንደሚችል የዜና ወኪሉ የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳል ባኪር ለሰሯቸው ስህተቶች የሃገሪቱ ዜጎች ይቅርታ ጠየቁ
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳል ባኪር በስልጣን ዘመናቸው ለሰሯቸው ስህተቶች የሃገሪቱ ዜጎች ይቅርታን እንዲያደርጉላቸው ጠየቁ። የይቅርታ ጥያቄያቸውን በፓርላማ ተገኝተው ያቀረቡት ፕሬዚደንቱ በደቡብ ሱዳን ሰላማዊ ድርድር እንዲካሄድ ጥሪን በማቅረብ ለሁሉም የተቃዋሚ ሃይሎች የደህንነት ዋስትና እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል። በሃገሪቱ ይካሄዳል የተባለውን ሁሉ አሳታፊ ድርድር በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ የተቃዋሚ ሃይሎች በአንድ በማሰባሰብ ለደቡብ ሱዳን ሰላም የሚያስፈልግ እንደሆነ ሳልባኪር ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎችን ለማጥቃት አዲስ እንቅስቃሴ ተጀመረ
ታኅሣሥ ፭ (አምስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በዞኑ የተለያዩ ግንባሮች በተደረጉ ውጊያዎች ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰበት የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ዛሬ ረዕቡ ማለዳ ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ወልቃይት አሰማርቷል። አዲሱ እንቅስቃሴ የጸረ ሽምቅ አዛዥ ኮማንደር ዋኘው አዘዘ መታሰራቸውን ተከትሎ የታቀደ ሲሆን፣ ቀደም ብለው የተደረጉት ተመሳሳይ ዘመቻዎች ሳይሳኩ ቀርተው ነበር። ለውጤት መጥፋቱ ተጠያቄ የተደረጉት ኮማንደር ዋኘው ሲሆኑ፣ የአሁኑን ...
Read More »