በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሸርቆሌ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ20 በላይ የጸጥታ አባላት መገደላቸው ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 24 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሱዳን በምትዋሰንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሸርቆሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቤኒሻንጉል ነጻነት ንቅናቄና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ከ20 በላይ የጸጥታ አባላት መገደላቸውን የንቅናቄው አመራሮች ለኢሳት ገለጹ። ከቀናት በፊት በተካሄደው በዚሁ ግጭት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የአጸፋ ዕርምጃ በትንሹ ስድስት ነዋሪዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው በአግባቡ የማይታወቅ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውንም የንቅናቄው አመራሮች አስረድተዋል። የኢትዮጵያን ድንበር ...

Read More »

በውጭ ብድር የተጀመሩ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ የብድር የመክፈያ ጊዜያቸው መድረሱ ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) ኢትዮጵያን ስኳር ላኪ ሃገር ያደርጋሉ ተብለው ከውጭ በተገኘ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ግንባታቸው ከሰባት አመት በፊት የተጀመሩ ፋብሪካዎች ግንባታቸው ተስተጓጉሎ እያለ ብድር የመክፈያ ጊዜያቸው መድረሱ ተገለጸ። በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ውስጥ የሚገኘው መንግስት በበኩሉ በመገንባት ላይ ያሉትን ጨምሮ በስራ ላይ ያሉ የስኳር ፋብሪካዎች ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በሽርክና ለመስራው መወሰኑን ይፋ አድርጓል። መንግስት ከተለያዩ አበዳሪ ...

Read More »

አሜሪካ 35 የሩሲያ ዲፕሎማቶች እስከፊታችን እሁድ ድረስ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) አሜሪካ 35 የሩሲያ ዲፕሎማቶች እስከፊታችን እሁድ ድረስ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። በአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ልዩ ትዕዛዝ የተላለፈውን ይኸው ውሳኔ ሩሲያ ባለፈው ወር በአሜሪካ ተካሄዶ ከነበረው ምርጫ ጋር በተገኛኘ እንደሆነ ታውቋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ሩሲያ በምርጫው ሂደት ላይ የኢንተርኔት ሻጥር ለመፈጸም ስትንቀሳቀስ እንደነበር በማስረጃ መገኘቱ ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። የአሜሪካ ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች ሲከታተሉት ነበር የተባለውን ...

Read More »

ምዕራባውያን አዲስ አመትን ለመቀበል የጸጥታ ቁጥጥር ማጠናከራቸው ተገለጸ

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) የፊታችን ዕሁድ የሚከበረውን 2017 የፈረንጆች አዲስ አመት ለመቀበል አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያን ሃገራት የጸጥታ ቁጥጥር ማጠናከራቸው ተገለጸ። በዚህ በአሜሪካ ቅዳሜ ምሽት በኒው ዮርክ ከተማ የሚከበረውን የዋዜማ ስነስርዓት በማስመልከት የከተማዋ ፖሊስ 7 ሺ የፖሊስ አባላትን በማሰማራት የጸጥታ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩን የአሜሪካን ፖሊስ አርብ አስታውቋል። በቅርቡ በጀርመን በርሊን ከተማ የተፈጸመው የሽብር ድርጊት ለጸጥታ ቁጥጥሩ ምክንያት የሆነ ሲሆን፣ የበአሉ ...

Read More »

የአትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የቀብር ስነስርዓት በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ታወቀ

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) የታዋቂው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የቀብር ስነስርዓት የፊታችን ዕሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ቅድስ ስላሴ-ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ታወቀ። የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር አስከሬን አዲስ አበባ ሲደርስ የመቀበልና የቀብር ስነስርዓቱን የሚያስተባብር በአትሌቶች የሚመራ ኮሚቴ መቋቋሙ ታውቋል። ምሩፅ ካረፈበት ጊዜ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ እየተሰጠ ያለው ምላሽ እንዳስደሰታቸውም ልጆቹ ሄኖክ፣ ካህሳይና፣ ሚካኤል ምሩጽ ገልጸዋል። ማክሰኞ ታህሳስ 18: 2009 በካናዳ ...

Read More »

130 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አርብ አስታወቀ

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ 130 ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አርብ አስታወቀ። ለእስር ከተዳረጉት ሰዎች በተጨማሪ በስምንት ትላልቅ አክሲዮኖች በአራት ህንጻዎች በ49 ተሽከርካሪዎች፣ በ22 በመኖሪያ ቤቶችና በሁለት ፋብሪካዎች ላይ እገዳ መደረጉንም ኮሚሽኑን ዋቢ በማድረግ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰበር ዜና ዘግበዋል። ይህንና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለእስር የተዳረጉ የመንግስት ባለስልጣናትና ንብረት የታገደባቸውን ግለሰቦችና ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ከእስር እንዲፈቱ የሚያስተባብር አለም ቀፍ ግብረ ሃይል ተቋቋመ

ኢሳት (ታህሳስ 21 ፥ 2009) ነዋሪነታቸው በተለያዩ የአለማችን ሃገራት የሆነ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር መረራ ጉዲና ከእስር እንዲፈቱ የሚያስተባብር አለም ቀፍ ግብረ ሃይል አቋቋሙ። ግብረ ሃይሉ እያካሄደ ያለው ይኸው አለም አቀፍ ዘመቻ አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ኢትዮጵያ ለእስር የዳረገቻቸው የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞችን እንዲሁም ሌሎች አካላትን እንድትለቅ ግፊት እንደሚያደርጉ የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል። የዘመቻው መጀመር አስመልክቶ መግለጫን ያወጣው ግብረ ሃይሉ ...

Read More »

የአማራ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ከስልጣን ተነሱ

ታኅሣሥ ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በክልሉ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ደሴ አሰሜ ከሃላፊነት ተነስተው እንዲንሳፈፉ ተደርጓል። ለአገዛዙ ታማኝ ናቸው የሚባሉት አቶ ደሴ፣ እንደሌሎች ከሃላፊነት እንደተነሱት ሰዎች ወደ እስር ቤት ባይወሰዱም፣ በአሁኑ ሰአት ከስልጣን ተነስተው ያለስራ ተቀምጠዋል። በክልሉ ውስጥ በተለይም የሙስሊም አትዮጵያውያን እንቅስቃሴ ...

Read More »

በኬንያ ናይሮቢ ስደት ላይ የነበረ ኢትዮጵያዊ  ታፍኖ መወሰዱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ

ታኅሣሥ ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምንጮቻችን የላኩት መረጃ  እንደሚያመለክተው በቅርብ ጊዜ ከኢትዮጵያ የመጣውና ላለፉት ሶስት ወራት በናይሮቢ በስደተኝነት የቆየው ስደተኛ  የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ ሲሆን ፤ ምናልባትም ከፍ ያለ ማእረግ ሳይኖረው እንዳልቀረ ጠቁመዋል። ይህ የመንግስት ሰው የነበረውና በቅርቡ ከሀገር ቤት ከድቶ የመጣው ስደተኛ ትናንት በናይሮቢ ዲዶራይ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር  ሳለ የኢትዮጵያ ደህንነቶች በፓትሮል  በመምጣት አፍነው እንደወሰዱት ምንጮቹ ...

Read More »

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች ዕድሜ ልክ ከውድድር እንዲታገዱ ያስተላለፈው ውሳኔ ተቃውሞ አስነሳ

ኢሳት (ታህሳስ 20 ፥ 2009) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስፖርት ውድድር ወቅት አበረታች መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች ዕድሜ ልክ ከውድድር እንዲታገዱ ያስተላለፈው ውሳኔ በአትሌቶች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ። የፌዴሬሽኑ አዲሱ ፕሬዚደንት አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ አበረታች ነው የተባለ መድሃኒት ተጠቅመው የተገኙ አትሌቶች ከእንግዲህ በኋላ የእድሜ ልክ እገዳ ይጣልባቸዋል ሲል ከሮይተርስ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ገልጸዋል። ከወራት በፊት ስድስት የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር ወቅት አበረታች መድሃኒት ...

Read More »