ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝቡን ጥያቄ የመለሰ ባለመሆኑ ህዝባዊ ተቃውሞ ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የብሪታኒያው ዘጋርዲያን ጋዜጣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ዋቢ በማድረግ ዘገበ። አዋጁ ተቃውሞን ለመቆጣጠር ተግባራዊ ቢያደርግም ህዝቡ ሲያነሳ የነበረው የተለያየ ጥያቄ እስካሁን ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን በኢጄሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ ለደህንነታቸው ስማቸውን እንዳይገለጽ በመጠየቅ ለጋዜጣው ተናግረዋል። በምዕራብ ሸዋ የሚኖሩ የተለያዩ ...
Read More »710 ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ባለድርሻዎቹ ሆነው መገኘታቸው ታወቀ
ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009) የብሄራዊ ባንክ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸውን የአክሲዮን ድርሻ እንዲመልሱ ባስተላለፈው መመሪያ እስከአሁን ድረስ 710 የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ባለድርሻዎቹ መገኘታቸው ተገለጸ። ባንኩ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በሃገሪቱ የሚገኙ የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለብሄራዊ ባንክ የተጠየቁትን ዝርዝር በመስጠት ላይ ሲሆን፣ በእስከአሁኑ እርምጃ 700 የውጭ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ባለድርሻዎቹ ተለይተው መታወቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ለባንኩ የቀረበን ሪፖርት ...
Read More »የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በሶማሊላንድ ወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም ስምምነት መድረሷ ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 6 ፥ 2009) የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የራሷን ነጻ ሃገር አድርጋ ባወጀችው የሶማሊላንድ ወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም ስምምነት መድረሷ ተገለጸ። የተባበሩት ኤሜሬት የወሰደችው ይኸው እርምጃ በጎረቤት ሃገራት ዘንድ ጥያቄ ማስነሳቱን ቢቢሲ የፖለቲካ ተንታኞችን ዋቢ በማድረግ በጉዳዩ ዙሪያ ባቀረበው ዘገባ አመልክቷል። የሶማሊላንድ ፕሬዚደንት አህመድ ሞሃመድ ሱላኒዬ የሶማሊላንድ ሃገሪቱ የወሰደችው ዕርምጃ ስራን ለመፍጠር ጠቀሜታ እንዳለው ለፓርላማ አባላት መግለጻቸው ታውቋል። 144 የሚሆኑ የፓርላማ ...
Read More »የሶማሊ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በኦሮምያ ፖሊሶች ላይ ጥቃት ፈጸሙ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ከፍተኛ የህወሃት ድጋፍ ባላቸው በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመራው ልዩ ሃይል በኦሮሞያ ክልል ከባቢሌ በ18 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኙት በአውሸሪፍና ደረሬ ቀበሌዎች በመግባት ከኦሮምያ ፖሊስ ጋር የተዋጋ ሲሆን ፣ በውጊያውም አንድ የኦሮምያ ፖሊስ ሲገደል ፣ ሁለት ፖሊሶች ተማርከው ተወስደዋል። ይሁን እንጅ በሁሉቱ ሃይሎች መካከል ...
Read More »ብአዴን የሚያስተዳድራቸው ሰባቱ ድርጅቶች ኪሳራ ውስጥ ገብተዋል ተባለ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል ብአዴን ያቋቋማቸው ከ16 በላይ የልማት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ 7ቱ በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ናቸው። ድርጅቶቹ በመነሻ ካፒታል በአምስት ነጥብ ሰባት ቢልየን ብር ከህዝብ በጀት ተበድረው ቢቋቋሙም፣ የብአዴን ባለስልጣናት እንደልባቸው የሚዘርፏቸው ተቋማት መሆናቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። ለዝርዝሩ ፋሲል የኔዓለም በኮንስትራክሽን ፣ በማማከር ፣ በማሽነሪ ኪራይ ፣ በፋብሪካ ምርቶች ፣ በውሃ ጉድጓድ ...
Read More »አቃቢ ህግ ነጻ መረጃ አላገኘሁም በሚል የፈታቸው ባለስልጣናት በድጋሜ ታሰሩ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2007 ዓም በሃመር ወረዳ ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰድ ወይም እንዳይወሰድ በማድረግ ለወጣቶቹ በቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ድጋፍ ሰጥታችኋል ተብለው ታስረው የነበሩ የወረዳው ባለስልጣናት መረጃ የለም በሚል አቃቢ ህግ ክስ እንደማይመሰርት ማስታወቁን ተከትሎ ባለስልጣኖቹ ቢፈቱም፣ በድጋሜ እንዲታሰሩ ተደርጓል። ፋይሉን የመረመሩ ዐቃቢያነ ህጎች ደግሞ ከሥራና ደመወዝ ...
Read More »በመላ ሃገሪቱ በሚታየው የነዳጅ እጥረት ተጓዦች ከታሪፍ በላይ በመክፈል መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበርካታ የሃገሪቱ ከተሞች የሚታየው የነዳጅ እጥረት ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት ተጓዦች ከመደበኛ ታሪፍ በላይ እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን ለኢሳት ገለጹ፡፡ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ከወራት በፊት የተከሰተው የነዳጅ እጥረት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በተለይ በአማራ ክልሏ በበርካታ ከተሞች የቤንዚን አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንታት መቆጠሩን አሽከርካሪዎች ተናግረዋል። በባህር ዳር፣ጎንደር ፣ወልዲያና ደሴ በመሳሰሉት ትልልቅ ከተሞች የነዳጅ አገልግሎት ...
Read More »በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ኤንባሲ ውስጥ በመግባት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
የካቲት ፫ ( ሦስት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሱዳን ውስጥ ለሚፈጸምባቸው ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ኤንባሲው ለስደተኞች ምንም ዓይነት እገዛ አለማድረጉን በመቃወም ኤንባሲው ግቢ ውስጥ በመግባት በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ኢትዮጵያውያኑ ኤንባሲው አካባቢ ያሉ የደህንነት አባላት በቪዲዮ ምስል እንዳይቀርጹ ካሜራዎችን በመቀማት ለመከልከል ሙከራ አድርገዋል። ኢትዮጵያን ስደተኞች በሱዳን በኡንዱርማን እና በተለያዩ ...
Read More »በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ከፍተኛ ውጥረትና ወከባ መኖሩ ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 3 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰላምና መረጋጋት አምጥቷል ቢልም አሁንም ድረስ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍሎች ውጥረትና ወከባ መኖሩን ነዋሪዎች ለውጭ መገናኛ ብዙሃን ገለጹ። ሙዚቃ መስማት ወንጀል ሆነ ማሳሰሩንም አስታውቀዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎች በምሽትና ተሰባስቦ የመወያየትና የመጫወት እንቅስቃሴያቸው አሁንም ድረስ እገዳ ተጥሎበት እንደሚገኝ ለጀርመኑ ዶቼ ዌሌ የእንግሊዝኛ ክፍል ...
Read More »የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር የሚለቀቁበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ተጠየቀ
ኢሳት (የካቲት 3 ፥ 2009) የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት የአገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር የሚለቀቁበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ዳግም ጥያቄ ማቅረባቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 62ኛ አመት የልደት በዓልን አስመልክቶ በብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር መኖሪያ ቤት አካባቢ ዝግጅትን ያካሄዱ የፓርላማ አባላትና የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች የሃገሪቱ ባለስልጣናት ለዜጋቸው መብት መከበር ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸው ኢስሊንግተን ጋዜት የተሰኘ ...
Read More »