በመሃል አዲስ አበባ በሁሉም ክፍለከተሞች የሚኖሩ ነባር ነዋሪዎች ከይዞታቸው እንደሚነሱ አዲሱ ፍኖተ ካርታ አመለከተ

የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ ነባር የሚባሉ ማስፋፊያዎች ጨምሮ ፒያሳ፣4 ኪሎ፣6 ኪሎ፣ ካዛንቺስ፣ለገሀር፣ ቂርቆስ፣ በቅሎ ቤት፣ ቦሌ፣ልደታ፣ቄራ፣ ጎተራ፣ ሳሪስ እና የመሳሰሉ አካባቢዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን አንስቶ ወደሌላ አካባቢ የማስፈር ዕቅድ በአዲሱ ፍኖተ ካርታ (ወይም ማስተር ፕላን) መካተቱ ታውቋል። በአዲሱ ካርታ መሰረት ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረውን ወደጎን የመስፋት መርህ በማስቀረት ወደላይ ...

Read More »

በተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የቀረበው ክስ ፖለቲካዊ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ወች አስታወቀ

የካቲት ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶስት ወራት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባላት ጋር ለመወያየት ወደ ቤልጅየም በመሄድ በኅብረቱ ፓርላማ በመገኘት ንግግር አድርገው ሲመለሱ የታሰሩት የ60 ዓመቱ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የቀረቡባቸው ክሶች ሕጋዊነት የሌላቸው ፖለቲካዊ ክሶች ናቸው ሲል የሂውማን ራይትስ ወች የምስራቅ አፍሪካ ዋና አጥኚ ፊሊክስ ...

Read More »

በዶ/ር መረራ ላይ የተሰረተው ክስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው ነው ሲል ሂውማን ራይስት ዎች ስጋቱን ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ሰሞኑን የተመሰረተው ክስ ከህግ ይልቅ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ ስጋቱን ገለጸ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሩን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ዕስረኞች እንዲለቀቁ ጥሪውን ለኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበ ሲሆን መንግስት ከህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽን ከመስጠት ይልቅ እየወሰደ ያለው እስራት እና ወከባ መፍትሄን እንደማያስገኝ በተመራማሪው ፊሊክስ ...

Read More »

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ400 በላይ ዜጎች መገደላቸው ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) የኦሮሚያ ክልልን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ዕልባት አለማግኘቱንና በሁለቱ ወገኖች ከ400 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ ገለጸ። ካለፉት ስድስት ወራት ጀምሮ በፌዴራል መንግስት ድጋፍ ይደረግላቸዋል የተባሉ የሶማሌ ክልል ልዩ የፖሊስ አባላት 15 በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች መጠነ ሰፊ ጥቃት በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ...

Read More »

የአባይ ግድብ የሃይል ማመንጫ አቅሙ እንዲያድግ ተደርጓል መባሉ በግብፅ በኩል ስጋት አሳድሯል ተባለ

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ የሃይል ማመንጫ አቅሙ በ450 ሜጋ ዋት እንዲያድግ ተደርጓል መባሉ በግብፅ በኩል ስጋት ማሳደሩን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ማከሰኞ ዘገቡ። ሰሞኑን የኮሚኒኬሽን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚካዔል በግድቡ ላይ በተደረገ ማሻሻያ 6ሺ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ያቀርባል ተብሎ የነበረው ግድቡ ወደ 6450 ሜጋዋት ከፍ ማለቱን መግለጻቸው ይታወሳል። ይሁንና የግብፅ የውሃ ምህንድስና ...

Read More »

ለህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተመደበው ሶስት ቢሊዮን ብር አንድ ቢሊዮኑ ለ180 ሺ ዘመናዊ ዲጂታል ታብሌቶች መግዣ ሊውል ነው 

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በቀጣዩ አመት በኢትዮጵያ ሊካሄድ ለታቀደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተመደበው ሶስት ቢሊዮን ብር መካከል አንድ ቢሊዮን ብር ለ180ሺ ዘመናዊ ዲጂታል ታብሌቶች (የእጅ ኮምፒውተሮች) መግዣ ተመደበ። ለቆጠራው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው በአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ የሚሸፍን መሆኑን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊዎች መግለጻቸውን አዲስ ፎርቹን የተሰኘ የቢዝነስ ጋዜጣ ዘግቧል። ኤጀንሲው የዘመናዊ ኮምፒውተሮቹን በአንድ ቢሊዮን ብር ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ...

Read More »

ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለ2016 አም የሚሸልመው አፍሪካዊ መሪ ማጣቱን ገለጸ

ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2009) በአፍሪካ የመልካም አስተዳደር ዴሞክራሲ እንዲጎለብት አስተዋጽዖን ላደረጉ መሪዎች የአምስት ሚሊዮን ዶላር አመታዊ ሽልማት የሚሰጠው ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለሁለተኛ ተከታታይ አመት ለ2016 አም የሚሸልመው መሪ ማጣቱን ማክሰኞ ገለጸ። በፋውንዴሽኑ የሽልማቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሳሊም አህመድ ሳሊም ለ2016 አም ለሽልማቱ የሚበቁ የቀድሞ የአህጉሪቱ መሪዎችን ለመምረጥ በተደረገ ስራ አንድም መሪ መስፈርቱን ሊያሟላ እንዳልቻለ ለመገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። በዴሞክራሲያዊ ...

Read More »

በቴክኒክ ችግር በህንድ ለማረፍ የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) ቅዳሜ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በህንድ ለማረፍ ተገዶ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ ቀን መዘግየት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ማቅናቱን የህንድ የአቪየሽን ባለስልጣናት ገለጹ። 255 መንገደኞችን እና የበረራ ባለሙያዎችን ይዞ ከሙምባይ ወደ ካትማንዱ ከተማ በማቅናት ላይ እንዳለ ፓይለቱ (የአውሮፕላኑ አብራሪ) የቴከኒክ ችግር እንዳጋጠመውና ለማረፍ መገደዱን ለትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት ማድረጉን ኢንዲያ ቱዴይ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ET8806 የሚል ...

Read More »

የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የተላለፈውን ግርፋትና እስር ተከትሎ ለሃገሪቱ የሚሰጠው ድጋፍ እንዲቋረጥ ጠየቁ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) የሱዳን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያስተላለፈውን የግርፋት እና የእስር ቅጣት ተከትሎ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት ለሃገሪቱ ስደተኞችን ለመደገፍ የሚሰጣት ድጋፍ እንዲቋረጥ ጠየቁ። በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞች በሱዳን መንግስት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንደሚፈጸምባቸውና ድርጊቱ ሱዳን ከአውሮፓ ህብረት ጋር በቅርቡ የደረሰችውን ስምምነት የሚጻረር እንደሆነ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት መግለጻቸውን ዘጋርዲያን ጋዜጣ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የኮሌራ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (የካቲት 20 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በበርካታ ዞኖች የኮሌራ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ይፋ አደረገ። ቢርቆድ፣ ቀብሪደሃር፣ ደገሃቡር፣ ሽኮሽና፣ እና ጉናጉዱ ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች እየተዛመተ ባለው በዚሁ ተላላፊ በሽታ እስካሁን ድረስ በትንሹ 103 ሰዎች መያዛቸውን የሶማሌ ክልል የጤና ባለሙያዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ለሁለተኛ ጊዜ በክልሉ ተከስቶ የሚገኘው ...

Read More »