በአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ

መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አባባ በርካታ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች አስታወቁ። የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ለከተማዋ የውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ጉድጓዶች በመድረቃቸው ምክንያት የውሃ እጥረቱ መከሰቱን በቅርቡ መግለፁ ይታወሳል። ባለስልጣኑ የውሃ እጥረቱ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል ሲል ከቀናት በፊት መግለጫን ቢሰጥም ነዋሪዎችና የተቋማት ባለቤቶች ችግሩ ዕልባት አለማግኘቱን ይገልጻሉ። ለአመታት የቆየው የመዲናይቱ የውሃ እንዲሁም የመብራት እጥረት በዕለት ከእለት ኑሯቸው ...

Read More »

በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

መጋቢት 13: 2009) በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ሳምንት ጊዜ የቀጠለው የነዳጅ እጥረት በነዋሪዎች ላይ ማህበራዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጹ። በተለይ የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቅመው የተለያዩ ጉዳዮች የሚያከናውኑ ነዋሪዎች የነዳጅ እጥረቱ ለሁለተኛ ሳምንት በመቀጠሉ ምክንያት ለዘርፉ ብዙ ችግር መዳረጋቸውን አስታወቀዋል። በመዲናይቱ የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለሃብቶች በበኩላቸው ነዳጅ ለማግኘት በነዳጅ ማደያ አካባቢዎች ለማደር መገደዳቸውን ጭምር ለመገናኛ ብዙሃን አስረድተዋል። ለመንግስት ስራና ለግል ጉዳዩች ለመንቀሳቀስ የህዝብ ...

Read More »

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ ጭምር እንዲያስመዘግቡ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ

መጋቢት 13: 2009) የውጭ ምንዛሪ ዝውውርን ለመቆጣጠር ሲባል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች የያዙትን ገንዘብና ጌጣጌጥ ጭምር እንዲያስመዘግቡ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ሆነ። ከዚህ በፊት ከተለያዩ ሃገራት የአየር ትራንስፖርት ተጠቅመው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች 24 ሰዓት እስካልሞላቸው ድረስ የያዙትን ገንዘብም ሆነ ጌጣጌጥ ማስመዝገብ እንደማይጠበቅባቸው ታውቋል። ይሁንና በአዲሱ መመሪያ መሰረት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ በእጁ የሚገኙ ገንዘቦችን እንዲሁም ጌጣጌጦችን እንዲያስመዘግብ መደረጉን የኢትዮጵያ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የተበከለ ውሃን የተጠቀሙ ነዋሪዎች ለሞትና ህመም ተዳረጉ

መጋቢት 13: 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ስር በምትገኘው የሃርገሌ ከተማ አካባቢ ከሚገኝ ግድብ የተበከለ ውሃን ከተጠቀሙ ነዋሪዎች መካከል በትንሹ ስድስቱ ሞተው በርካታ ለህመም መዳረጋቸውን አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ። በክልሉ በመባባስ ላይ ያለው የድርቅ አደጋ ጋር በተያያዘ ሰዎች በመሞት ላይ መሆናቸውን የገለጸው የካቶሊክ ዕርዳታ ድርጅት፣ ህይወታቸውን ለመታደግ ሲሉ ከግድቡ የተገኘን ውሃ የሚጠቀሙ ሰዎች ለሞትና ለበሽታ መዳረጋቸውን በጉዳዩ ዙሪያ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ አካባቢዎች የጀመረው የሽምቅ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

መጋቢት 13: 2009) አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰሞኑን በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የጀመረው የሽምቅ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ። ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የንቅናቄው ሰራዊት አባላት በማክሰኝት፣ በደጎማ፣ በደንቀዝን ፣ በበለሳ፣ በአዲስ ወረዳ፣ በደምቢያ እንዲሁም በጯሂት በህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ስርዓት ተቋማት ላይ የተቀናጀ የሽምቅ ጥቃት ማድረሳቸውን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በሰሜንና ደቡብ ጎንደር በተካሄዱ የንቅናቄው የሽምቅ ጥቃት መንግስት ቀይ ...

Read More »

ትግላችን ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ማዳን ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህኒን) የሚካሄደው የነጻነት ትግል ሃገራዊና ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የማዳን መሆኑን የድርጅቱ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ። የቤህኒን የፖለቲካ ሃላፊ አልሃጂ አፈንዲ ጠሓ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በህወሃት/ኢሀዴግ  የሚመራውን አገዛዝ ለማስወገድ የሚካሄደው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል። ድርጁቱ በሃገር ውስጥ የሚካሄደው የትጥቅ ትግል በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ያነጣጠረ እንጂ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የማድረስ አላማ እንደሌለውም ገልጸዋል። በቅርቡ ...

Read More »

አለም-አቀፍ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ተጠቅሞ የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን እንዲያስቆም ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) የአለም አቀፍ ማህብረሰብ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ በማቆም በሃገሪቱ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲያበቃ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን በቤልጂየም ብራሰልስ ከተማ ያደረገውና ውክልና ያልተሰጣቸው ህዝቦች ድርጅት (Unrepresented Nations and People’s Organization) የሚል መጠሪያ ያለው ድርጅት በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ ያላቸውን የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች፣ አፈናዎችና፣ ድብደባዎች በተመለከተ የባለ 27 ገፅ ሪፖርት አቅርቧል። ...

Read More »

በቆሼ በደረሰ አደጋ የሟቾች ቁጥር በመቶዎች ሊበልጥ እንደሚችል የጸጥታ አካላት ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቆሻሻ መደርመስ (መናድ) በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር መንግስት ከሚገልጸው በመቶዎች ሊበልጥ እንደሚችል ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የጸጥታ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዘገበ። ቁፋሮ እየተካሄደበት ባለው ስፍራ ለጸጥታ ስራ ተሰማርቶ የሚገኝና ማንነቱ እንዳይገለጽ የጠየቀ የጸጥታ ባልደርባ አሁንም ድረስ በርካታ ሰዎች ከቁፋሮ አለመውጣታቸውን ለጋዜጣው አስረድቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ሳምንት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ አለም አቀፍ ድጋፍ ባለመገኘቱ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ላለው የድርቅ አደጋ የሚያስፈልገው አለም አቀፍ ድጋፍ እየተገኘ ባለመሆኑ ድርቁ እያደረሰ ያለው አደጋ እየተባባሰና ስጋት እየሆነ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። ይኸው የድርቅ አደጋ በተለይ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል በርካታ ሰዎች በከፋ የምግብ እጥረት የአካልና የጤና ችግር እንዲደርስባቸው ያደረገ ሲሆን፣ ዕድሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ ህጻናት ወደ ማገገሚያ ማዕከል እየገቡ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ በሚያወጣው ...

Read More »

በአንድ ኢትዮጵያዊ የእስራዔል ወታደር ላይ ድብደባን የፈጸመ ፖሊስ በወንጀል ሊከሰስ እንደሚችል ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009) የእስራዔል የፍትህ ሚኒስቴር ከሁለት አመት በፊት በአንድ ኢትዮጵያዊ የእስራዔል ወታደር ላይ ድብደባን የፈጸሙ ፖሊስ በወንጀል ሊከሰስ እንደሚችል አስታወቀ። ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የቀድሞ አቃቤ ህግ ተጀምሮ ፍርድ ሳያገኝ በእንጥልጥል የቆየው ድርጊት እንዲዘጋ ባለፈው ጥር ወር ውሳኔን ቢያስተላልፍም ጉዳዩ ይግባኝ ቀርቦበት በአዲስ መልክ መታየት መጀመሩን የእስራዔል መገናኛ ተቋማት የእስራዔልን የፍትህ ሚኒስቴር ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። የፖሊስ ባልደርባው የቀረበለትን ...

Read More »