ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ጉብኝትን በማድረግ ላይ የነበሩት የሶማሊያው ፕሬዚደንት ሞሃመድ አብደላሂ ረቡዕ በሞቃዲሾ ከተማ በአንድ ሚኒስትር ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ጉብኝታቸውን አቋረጡ። ረቡዕ የሶስት ቀን ጉብኝትን ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተው የነበሩት ፕሬዚደንቱ ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እቅድ እንደነበራቸው ታውቋል። በአንድ ቀን ቆይታቸው ረቡዕ ምሽት በጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ከሌሎች ...
Read More »የአፋር ክልል የወረዳ ባለስልጣናት ለስብሰባ ወደ መቀሌ መሄዳቸው ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) በአፋር ክልል የ33ቱም ወረዳ አመራሮች ለስልጠና መቀሌ ሲገቡ፣ የክልልና የወረዳ አመራሮች ደግሞ አዲስ አበባ መሄዳቸው ታወቀ። የወረዳ አመራሮች በአሳይታና በሰመራ መሰልጠን እየቻሉ ወደ መቀሌ መጓዛቸው በክልሉ ቅሬታ መፍጠሩን ምንጮች ገልጸዋል። ከአፋር 33ቱ ወረዳዎች ወደ መቀሌ የተጓዙ 600 ያህል አመራሮች ሲሆን፣ በቆይታቸው ወቅት የውሎ አበልም ሆነ፣ ሙሉ ለሙሉ የሆቴል ወጪያቸው የሚሸፈነው በአፋር ክልል መንግስት እንደሆነም ታውቋል። ...
Read More »የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የመንግስት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት ውድቅ አደረጉት
ኢሳት (ሚያዚያ 26 ፥ 2009) በህወሃት አገዛዝ የተቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ያወጣውን የምርመራ ሪፖርት በቅርቡ አዲስ አበባን የጎበኙት የተባባሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ውድቅ አደረጉት። ኮሚሽነሩ ዛይድ ራድ አልሁሴን በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ብቻ ከ26 ሺ በላይ ሰዎች መታሰራቸውን እንዲሁም የተፈጸመው ግድያ በሃገሪቱ የህግ የበላይነት እንደሌለ ያሳያል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ...
Read More »በቆላድባ አርሶአደሮች የግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው
ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከዚህ ቀደም በሰሜን ወሎ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ሲካሄድ እንደነበረው አሁን ደግሞ በሰሜን ጎንደር አርሶአደሮች በግዴታ በእያካባቢያቸው ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው። በቆላ ድባ ከተማ ከ150 በላይ አርሶአደሮች ተመልምለው ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን፣ የከተማው ነዋሪ ቅሬታውን ሲገልጽ ተገደው እንደገቡ ተናግረዋል። አንዳንድ ሰልጣኞች ስልጠናውን ካልተካፈሉ የጦር መሳሪያቸውን እንደሚቀሙ ማስፈራሪያ የደረሳቸው ...
Read More »ሱዳን ከኢህአዴግ ጋር በመተባበር በታጋዮች ላይ ዘመቻ ከፈተች
ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች የሚፈጸሙ ጥቃቶች መበራከት ያሰጋው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ ከሱዳን ጋር ‘ የሰው እና የእጽ ዝውውርን መግታት” የሚል ሽፋን በሰጠው ዘመቻ፣ ራስ ምታት ሆነዋል ያላቸውን ታጋዮች የማደን ዘመቻ ጀምሯል። ኢሳት ቀደም ብሎ እንደዘገበው በሁለቱ ድንበሮች አካባቢ በሚገኙ ጫካዎች ይኖራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ታጋዮችን ለማጥቃት የሄዱ ...
Read More »በዶ/ር መረራ ጉዲና የክስ መቃወሚያ ላይ ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጠ
ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የአውሮፓ ሕብረት ባቀረበላቸው ግብዣ ላይ ተገኝተው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና ክስ ላይ አቃቤ ሕግ መቃወሚያ አቅርቧል። ሚያዝያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ምድብ ችሎት ላይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ...
Read More »በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነቱ ማሻቀቡን የኢትዮጵያ ስታስቲክ ኤጀንሲ አስታወቀ
ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ከወር ወር እየባሰበት መምጣቱን የኢትዮጵያ ስታስቲክ ኤጀንሲ ወርሃዊ ጥናት አመላክቷል። ድርጅቱ ባወጣው ዝርዝር ጥናት መሰረት ባለፈው መጋቢት ወር ላይ የምግብ ሸቀጦች ከነበሩበት 9 ነጥብ 6 ከመቶ ወደ 12 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች በበኩላቸው በመጋቢት ወር ከነበሩበት 4 ነጥብ 6 ከመቶ ...
Read More »አሜሪካ 2 መቶ ሚሊየን ዶላር እርዳታ ከኢትዮጵያና ዩጋንዳ እንደምትቀንስ ተዘገበ
ሚያዝያ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ አሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዘገባ ከሆነ ለምስራቅ አፍሪካ በየአመቱ ይመደብ ከነበረው አጠቃላይ እርዳታ የ30.8% ቅናሽ መደረጉንና ይህም በሚቀጥለው በጀት አመት 2017/18 ዓ.ም ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቋል። በዚሁ መሰረትም ከፍተኛ ቅናሽ ከተደረገባቸው አገሮች መካከል የኢትዮጵያው 131.2 ሚሊዮን ዶላር ከፍተኛው ሲሆን ፣ ዩጋንዳ 67.8 ሚሊዮን ዶላር፣ ሩዋንዳና ታንዛንያ እያንዳንዳቸው ...
Read More »በአፋር በተነሳ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ ።ሁለት የመከላከያ አባላትም ህይወታቸው አልፏል።
ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሚያዚያ 22 እስከ 23 ፣ 2009 ዓም የቀሰም ቀበና የስኳር ፕሮጀክትን የእርሻ መሬት ለማስፋት በጎሳዎች መካከል ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ ግጭት 23 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። የአብሌክ አድአሊ እና ሲድሃ ቡራ ጎሳዎች በጋራ ተነስተው የመሬት ወረራውን ለመቃወም እንዳይችሉ በመካከላቸው የመከፋፈል ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ሁለቱ ጎሳዎች እርስ ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ለ130 ሺህ ሕጻናት አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ
ሚያዝያ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ በኢትዮጵያ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ታዳጊ ህጻናት ተጎጂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ በኩል የ3 ሚሊዮን ዩሮ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያደርግ አስታወቀ። የተገኘውም እርዳታ ክፉኛ ለተጎዱ ህጻናት ህይወት ለማዳን እንደሚውልም ድርጅቱ አስታውቋል። ከፍተኛ ድርቅን ተከትሎ ርሃብ በተከሰተባቸው የአፋር፣ ሶማሊያ፣ ኦሮምያ ...
Read More »