ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት ብቻ 12.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ አለባት

ግንቦት ፯ ( አባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ከቻይና ባንኮች ብቻ እኤአ ከ2000-2014 ከፍተኛ ብድር ከወሰዱ አምስት የአፍሪካ አገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ የቻይና አፍሪካ ጥናት ማእከል አስታወቋል። ጥናቱ በተጠቀሱት ዓመታት ብቻ አንጎላ 21 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ብድር ስትወስድ፣ ኢትዮጵያ በ12 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛ ብድር ወሳጅ አገር ተብላለች። ሱዳን ...

Read More »

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና አቶ ዳንዔል ሺበሺ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡ

ኢሳት (ግንቦት 4 ፥ 2009) ላለፉት አምስት ወራት ያለምንም የክስ ሂደት በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና የቀድሞ የአንድነት አመራር አቶ ዳንዔል ሺበሺ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡ። በቦሌ ክ/ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሁለቱ አቤቱታ አቅራቢዎች በጥቅምት ወር በሃገሪቱ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። በማህበራዊ ድረገጾች የተለያዩ ጽሁፎችን ሲያቀርቡ የነበሩት ጋዜጠኛ ...

Read More »

ቢቢሲ በስድስት ቋንቋዎች ለሚጀምረው የራዲዮ ስርጭት በኬኒያ አዲስ ቢሮ እንደሚከፍት አርብ አስታወቀ

ኢሳት ( ግንቦት 4 ፥ 2009) የብሪታኒያው የማሰራጫ ጣቢያ ቢቢሲ ሶስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ጨምሮ በስድስት ቋንቋዎች ለሚጀምረው የራዲዮ ስርጭት በኬኒያ አዲስ ቢሮ እንደሚከፍት አርብ አስታወቀ። በኬንያ መዲና ናይሮቤ ለሚከፈተው ለዚሁ ቢሮ 10 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቧል። ስቱዲዮው ለ250 ሰዎች የስራ እድልን እንደሚፈጥር የቢቢሲ ተወካዮች ገልጸዋል። የብሪታኒያ መንግስት የማሰራጫ ጣቢያው ለሚጀምረው አዲስ ስርጭት በየአመቱ 85 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ እንደሚመደብ ባለፈው አመት ...

Read More »

በቱርኩ ጉለን ንቅናቄ ተቋቁመዋል የተባሉ ስድስት ትምህርት ቤቶች ማሪፍ ፋውንዴሽን ለተሰኘ የቱርክ መንግስታዊ ተቋም ተላልፈው ተሰጡ

ኢሳት ( ግንቦት 4 ፥ 2009) በኢትዮጵያ በቱርኩ ጉለን ንቅናቄ ተቋቁመዋል የተባሉ ስድስት ትምህርት ቤቶች ማሪፍ ፋውንዴሽን ለተሰኘ የሃገሪቱ መንግስታዊ ተቋም ተላልፈው ተሰጡ። ትምህርት ቤቶቹን የመረከብ ሂደት ከወራት በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ትምህርት ቤቶቹን አስተላልፎ ለመስጠት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ የተካሄደ መሆኑ የፋውንዴሽኑ ተወካይ አደም ኮክ ለቱርኩ ዜና አገልግሎት (አናዱሉ) ገልጸዋል። ባለፈው አመት በቱርክ የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ የቱርክ ባለስልጣናት የጉለን ...

Read More »

የአርበኛ ጎቤ መለኬ የእህት ልጅ ታፍኖ ተወሰደ

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአርበኛ ጎቤ የእህት ልጅ የሆነው ወጣት ዳዊት አንጋው ትናንትና ነው በወያኔ ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ታጣቂዎቹ ወጣት ዳዊትን አፍነው የወሰዱበትም ምክንያት ያልተናገሩ ሲሆን፤ በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ማረጋገጣቸውን ምንጮቹ ጠቅሰዋል። አርበኛ ጎቤ መልኬ ያለፈውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ እጅግ በርካታ ሀብትና ንብረቱን ትቶ የሀገሩን ነጻነት ለማስከበር ከወያኔ ...

Read More »

በዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ላይ እየተካሄደ ያለው የተቃውሞ ዘመቻ ዓለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እያገኘ ነው።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሎስ አንጀለስ ሴንቲኔል፣አፍሪካን ኒውስና በርካታ የውጪ ሚዲያዎች ፣ ኢትዮጵያን በመወከል የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ለመሆን የሚወዳደሩት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተቀናጀና ተከታታይ የተቃውሞ ዘመቻ እየተካሄደባቸው እንደሆነ አስነብበዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖምን በማስተዋወቁ ረገድ ከአንዳንድ አካላት ድርጅቱን ለመምራት ብቃት እንዳላቸው ቢገለጽም፣ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቁ አይደሉም የሚል ተቃውሞ እንደገጠማቸው ተገልጿል። ...

Read More »

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የተከሠሱት እነ ሉሉ መሰለ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ::

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲከላከሉ እንዲከላከሉ የተበየነባቸውን የሰማያዊ ፓርቲ አባልና የ2007 ዓ.ም ሀገራዊምርጫ የአርባ ምንጭ አካባቢ የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ አቶ ሉሉ መሰለን ጨምሮ 7 ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡ አቶ ሉሉ መሰለ የቀረበባቸው ክስ፣በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን በአርበኞች ግንቦት ሰባት አባልነት በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካል ...

Read More »

በአማራ ክልል ሙስና ፈጽመዋል የተባሉ 211 ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸው ተገለጸ።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እውነቴ አለነ ፤ ግለሰቦቹ የተቀጡት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ጠንካራ የክትትልናየቁጥጥር ስራ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው በማለት ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል። ከተከሳሾቹ መካከል 182ቱ ወንድና 29ኙ ሴቶች ሲሆኑ፤በተመሰረተባቸው በስልጣን ያለ አግባብ በመጠቀም፣ በግዢና ጨረታ ሙስና፣ በተጭበረበረ ሰነድበመገልገል፣ በግብር መሰወርና በመሰል የወንጀል ...

Read More »

ህወኃት በሁመራ ከተማ የአማራ እና የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌዎችን በመመልመልና “እርቅ እናውርድ!” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት ይህን ለማድረግ የተዘጋጀው ከልቡ እርቅና ፍቅርን ፈልጎ ሳይሆን በእርቅ ስም ፖለቲካ ቁማር ለመጨዋት በመኾኑ ሕዝቡ ሁኔታውን በጥንቃቄ እንዲከታተልና ህወኃት በቀደደለት ቦይ እንዳይሄድ የነዋሪዎቹ ውቀኪሎች ተናግረዋል። እንዲሁም ጠገዴን ከሁለት በመክፈል ጠገዴ ና ፀገዴ ብሎ የለዬውና በድንበር ጉዳይ ህዙቡን ሲያጋጭ የቆዬው ህወኃት በአሁኑ ሰዓት የሁለቱን አካባቢ እርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች ባህርዳር ...

Read More »

የብሪታኒያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲለቀቁ ግፊት እየተደረገበት ነው

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2009) የብሪታኒያ መንግስት ባለስልጣናት በሃገሪቱ በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በሚመከረው አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ዙሪያ እንዲመክሩ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሃሙስ ጥሪ አቀረበ። በለንደን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በዚሁ ጉባዔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሳታፊ ሲሆኑ ከብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ ጋር ውይይትን ...

Read More »