ህወኃት በሁመራ ከተማ የአማራ እና የትግራይ ተወላጅ ሽማግሌዎችን በመመልመልና “እርቅ እናውርድ!” በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝባዊ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑን የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።

ግንቦት ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት ይህን ለማድረግ የተዘጋጀው ከልቡ እርቅና ፍቅርን ፈልጎ ሳይሆን በእርቅ ስም ፖለቲካ ቁማር ለመጨዋት በመኾኑ ሕዝቡ ሁኔታውን በጥንቃቄ እንዲከታተልና ህወኃት በቀደደለት ቦይ እንዳይሄድ የነዋሪዎቹ ውቀኪሎች ተናግረዋል።
እንዲሁም ጠገዴን ከሁለት በመክፈል ጠገዴ ና ፀገዴ ብሎ የለዬውና በድንበር ጉዳይ ህዙቡን ሲያጋጭ የቆዬው ህወኃት በአሁኑ ሰዓት የሁለቱን አካባቢ እርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች ባህርዳር መሰብሰቡ ታውቋል።
ያነሳነው የመብት ጥያቄ በእርቅ እና በሽንገላ የሚቀለበስ እንዳልሆነ እንዲታወቅ በአፅንኦት ማስታወስ እንሻለን የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ ወልቃይት ጠገዴ ምንጊዜም አማራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።