ሰላም ባስ ጋራዥ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው በፖሊስ እየተጠበቀ ነው

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 14/2009)የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ጋራዥ ላይ ጥቃት የተፈጸመው ሐሙስ ምሽት ላይ ነበር። ስፍራውም ሳሪስ አካባቢ በቀለበት መንገድ መስመር ላይ እንደሆነም ተመልክቷል። በፖሊስ በተከበበው የሰላም ባስ ጋራዥ ውስጥ መርማሪ ባለሙያዎች መሳሪያዎችን ይዘው የፍንዳታውን ሁኔታ ሲያጠኑ እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስለጉዳቱ መጠን ለማወቅ አለመቻላቸውን ገልጸዋል። የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ከኢትዮጵያ የመንግስት ባንኮች አላግባብ ...

Read More »

ከቤተ መንግስት እስከ አፍሪካ ህብረት የሚኖሩ ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከቦታቸው ሊፈናቅሉ ነው

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 14/2009)የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ባሳለፍንው ሳምንት የአዲስ አበባ ማእከላትና ኮሪደሮች ልማት ኮርፖሬሽን እንደሚቋቋምና ኮርፖሬሽኑ ስራ እንደሚጀምር ገልጸው ነበር። በዚሁም መሰረት ከአፍሪካ ህብረት እስከ ቤተ መንግስት ከሚገኙ ቦታዎች 300 ሔክታር መሬት በማስለቀቅና በማዘጋጀት ስራውን እንደሚጀምርም ገልጸዋል። ይህንን ተከትሎም የአካባቢው ነባር ነዋሪዎች ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማና በስሩ ወዳሉ ወረዳዎች ለቤት ...

Read More »

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለ2010 ካጸደቀው የ40 ቢሊየን ብር በጀት 30 ቢሊየኑን ከግብርና ከገቢ ሊሰበስብ ነው

(ኢሳት ዜናሐምሌ 14/2009)የአዲስ አበባ አስተዳደር በተጠናቀቀው የበጀት አመት ብቻ ከአንድ ከአንድ ቢሊየን አራት መቶ ሚሊየን ብር በላይ አባክኗል። ይህም በዋና ኦዲተር ቢሮው ተረጋግጦ ብክነቱ በታየባቸው መስሪያ ቤቶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዛቱ ይታወቃል። የአዲስ አበባ አስተዳደር ለቀጣዩ 2010 ባጸደቀው በጀት 40 ቢሊየን ብር ለካፒታልና መደበኛ በጀት ቢመድብም አብዛኛው እቅድ ግን ባልተጨበጠ ገንዘብና ገና ለገና ከግብርና ከገቢ የሚሰበሰብ ነው። በአስተዳደሩ በጀት ላይ ...

Read More »

የነጋዴዎች አድማ መላ አገሪቱን እየሸፈነ ነው

ሐምሌ ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ ደምቢዶሎ፣ ነቀምት፣ ወለታ፣ ጊንጪ፣ ሱሉልታ፣ ሻሸመኔ፣ ዶዶላ ተጠናክሮ ሲካሄድ ከሰነበተ በሁዋላ፣ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ በመሸጋገር በሳሪስ፣ ከኮልፌ አጠና ተራ፣ ታይዋን ሰፈር፣ ዘነበወርቅ፣ አዲስ ጎማ አቦ ወርቁ ፣ ንፋስ ስልክና ሌሎችም ቦታዎች የንግድ ድርጅቶች እየተዘጉ ተቃውሞው በመካሄድ ላይ ነው ነው። ዛሬ ...

Read More »

ተመላሽ ወታደሮች እኛን ያየ ይቀጣ እያሉ ነው

ሐምሌ ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ፣ ከአልሸባብ ጋር በተደረጉ ውጊያዎች ሁሉ የተሳተፉና በተለያዩ ምክንያቶች መከላከያን የለቀቁ የቀድሞ ምልስ ወታደሮች አቤቱታቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል። በደሴ የሚገኙ የተመላሽ ሰራዊት አባላት፣ አገዛዙን ደማችን አፍስሰን አጥንታችን ከስክሰን ብናገለግለውም፣ ባለስልጣኖቻችን እንደ ቆሻሻ እያዩ፣ የትም ጥለውናል ብለዋል። መከላከያን መቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶች እነሱን አይተው ትምህርት እንዲወስዱም ይመክራሉ። “ እኛ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 450 ሺ የሚጠጋ ህዝብ ወደ መጠለያ ካምፕ ገባ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 13/2009)ዋሽንግተን ፖስት በጽሁፉ እንዳስነበበው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች በሶማሌ ክልል የዝናብ እጥረት ተከስቷል። ይህ ደግሞ በሚሊየን የሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ ጥገኞች እንዲሆኑና የቀድሞ የአኗኗር ዘይቤአቸውን እንዲቀየር አድርጎታል ይላል ዘገባው። የጽሁፉ ዘጋቢ በመጠለያው ከሚገኙት የሱማሌ ተወላጆች ውስጥ ያናገራቸው ወይዘሮ ዘይነብ ጣሂር የድርቁ አስከፊነት በሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ይናገራሉ። የዘጠኝ ልጆች እናት የሆኑት ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ እንዲወጡ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ 4 ቀን ቀረው     

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 13/2009) የሳውዲ አረቢያ መንግስት በሃገሩ ይኖራሉ ያላቸውን 5 ሚሊየን ህገ ወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር መጋቢት 29/2017 ነበር የሶስት ወራት የጊዜ ገደብ ያስቀመጠው። እንደአውሮፓውያኑ ሰኔ 25/2017 ደግሞ የጊዜ ገደቡ ለተጨማሪ አንድ ወር መራዘሙን ይፋ ማድረጉ ይታውሳል። በሳውዲአረቢያ መንግስታዊ ተቋማት መረጃ መሰረት በሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩት በአጠቃላይ ቁጥራቸው 5 ሚሊየን የሚጠጋ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያውያኑ ብዛት 400ሺ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ያለው የህዝብ በደልና የፍትህ እጦት በሽምግልና የሚፈታ አይደልም ተባለ        

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 13/2009)በመቀሌ ከተማ ከሐምሌ 14 እስከ 16/2009 ይካሄዳል የተባለው የአማራና የትግራይ ሽማግሌዎች ስብሰባ አላማው በግልጽ አልተቀመጠም። ይህም ሆኖ ግን ከአማራና ከትግራይ ክልል የተውጣጡ 1 ሺ 200 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች  የክልሎቹ ፕሬዝዳንቶች አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና አቶ አባይ ወልዱ በተገኙበት ይካሄዳል ነው የተባለው። ከአማራ ክልል 4 መቶ የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው የተባሉ የብአዴን ካድሬዎችን ጨምሮ መቀሌ ከተማ ገብተዋል። ታዛቢዎች እንደሚሉት የወልቃይት ...

Read More »

ከግብር ተመን ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ በአዲስ አበባ መጀመሩ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 13/2009) በግብር ተመን ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መጀመሩ ታወቀ። በሳሪስ፣በአጣና ተራ፣መሳለሚያና ሌሎች የአዲስ አበባ አካባቢዎች ሱቆችና መደብሮች ተዘግተዋል። ተቃውሞው በኦሮሚያ በርካታ ከተሞች ቀጥሎ የዋል ሲሆን ከአምቦ የሚወጡና የሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች መሳሪያ በጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንደሚታጀቡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል ። በደቡብ ኢትዮጵያም በሲዳማና በጋሞጎፋ ዞኖች በግብር ጭማሪው ላይ የተነሳው አድማ ቀጥሏል። በጎንደር ደግሞ ዛሬ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ከዕለታዊ የገቢ ግብር ትመና ጋር በተያያዘ የተጀመረው አድማ ተቀላቀሉ

ሐምሌ ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአምቦ፣ ነቀምቴ፣ ወሊሶ፣ ግንጪ፣ ሻሸመኔ፣ባሌ፣ መንዲ ፣ ነጆ፣ ሆለታና ሌሎችም በርካታ ከተሞች ላለፉት 3 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የነጋዴዎች ተቃውሞ፣ ዛሬ ሃሙስ ወደ አዲስ አበባ በመሸጋገር፣ በተለያዩ የመዲናዋ ክፍሎች የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶቻቸውን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። ሳሪስ ፣ አስኮ፣ ኮልፌ አጠና ተራ፣ ዘነበ ወርቅ፣ ታይዋን ሰፈርና በመሳሰሉ ...

Read More »