ከግብር ተመን ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ በአዲስ አበባ መጀመሩ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 13/2009) በግብር ተመን ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መጀመሩ ታወቀ።

በሳሪስ፣በአጣና ተራ፣መሳለሚያና ሌሎች የአዲስ አበባ አካባቢዎች ሱቆችና መደብሮች ተዘግተዋል።

ተቃውሞው በኦሮሚያ በርካታ ከተሞች ቀጥሎ የዋል ሲሆን ከአምቦ የሚወጡና የሚገቡ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች መሳሪያ በጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንደሚታጀቡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል ።

በደቡብ ኢትዮጵያም በሲዳማና በጋሞጎፋ ዞኖች በግብር ጭማሪው ላይ የተነሳው አድማ ቀጥሏል።

በጎንደር ደግሞ ዛሬ ለነጋዴዎች የተጨመረባቸው ግብር በወረቀት እየታደላቸው በመሆኑ ከሰሞኑ ተቃውሞ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።