(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009) የሰሜን ካሪቢያ ደሴቶችን እየመታ ባለው ኢርማ አውሎ ንፋስ እስካሁን 10 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በአደግኝነቱ በ5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢርማ አውሎ ንፋስ የደሴቲቱን አብዛኛውን ክፍል ከጥቅም ውጪ ማድረጉን መረጃዎች አመልክተዋል። አውሎንፋሱ እሁድ ወደ ደቡባዊ ፍሎሪዳ ይሻገራል መባሉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል። ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ተነስቶ የሰሜን ካሪቢያን ደሴቶችን እየመታ ያለው ኢርማ አውሎ ንፋስ እስካሁን የ10 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።–በርካቶችን መኖሪያ ...
Read More »በቅማንት ላይ በሚሰጠው ሕዝበ ውሳኔ ተጽእኖ ለማድረግ የስርአቱ ካድሬዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች እየደበደቡና እያንገላቷቸው መሆኑ ተነገረ
(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009)የአማራና ቅማንትን ማህበረሰብ ለመለያየት በሚሰጠው ሕዝበ ውሳኔ ተጽእኖ ለማድረግ በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ካድሬዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች እየደበደቡና እያንገላቷቸው መሆኑ ተነገረ። በሕዝቡ ውስጥ አማራና ቅማንት አይለያዩም በሚሉ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች ላይ የግድያ ዛቻ እየተፈጸመባቸው መሆኑን የጎንደር ሕብረት ገልጿል። የሕብረቱ ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ንጋቱ እንደገለጹት መስከረም 7/2009 የሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ውጤቱ ምንም ሆነ ምን የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ መቼም ...
Read More »የሶማሊያ መንግስት ኦብነግን በአሸባሪነት መፈረጁን ግንባሩ ህገወጥ ፍረጃ ሲል አጣጣለው
(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009) የሶማሊያ መንግስት ኦብነግን በአሸባሪነት መፈረጁን የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ህገወጥ ፍረጃ ሲል አጣጣለው። የሶማሊያ ፓርላማን ስልጣን በመጋፋት በፕሬዝዳንት ፋርማጆ የሚመራው የሚኒስትሮች ምክርቤት ውሳኔውን ማሳለፉ የሀገሪቱን ህገመንግስት የጣሰ ነው ሲልም ኦብነግ አስታውቋል። በቅርቡ ለህወሀት መንግስት ተላልፈው በተሰጡት የኦብነግ አመራር አባል አብዲካሪን ሼህ ሙሴ ምክንያት በሶማሊያ ከፍተኛ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን ትላንት የፕሬዝዳንት ፋርማጆ መንግስት ኦብነግን በአሸባሪነት መፈረጁ የተቀሰቀሰውን የህዝብ ...
Read More »ኢትዮጵያ ያልተረጋጉ ሐገራት ምድብ ውስጥ ደረጃዋ ማሽቆልቆሉን አንድ ጥናት አመለከተ
(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 2/2009) ኢትዮጵያ ያልተረጋጉ ሐገራት ምድብ ውስጥ ደረጃዋ ማሽቆልቆሉን በአሜሪካ የተካሄደ ጥናት አመለከተ። የምስራቅና የማእከላዊ አፍሪካ ሐገራት በአለም ላይ ካሉና ጥናቱ ካካተታቸው 178 ሐገራት ያልተረጋጉና ሰላም የደፈረሰባቸው ከተባሉ ሀገራት በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ተቀምጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ከአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ካውንስል ጋር በጣምራ ሆነው በአፍሪካ የሰላም ችግር ላይ ለመምከር ትላንት ረቡእ አዲስ አበባ ገብተዋል። ምስራቅ አፍሪካና ...
Read More »የራህ ናይል ሆቴል በባለቤትነት ከባለስልጣናት ጋር የተያያዘ ነው በሚል የተላለፈው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ
(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 1/2009) በባህርዳር ከተማ የራህ ናይል ሆቴል በባለቤትነት ከባለስልጣናት ጋር የተያያዘ ነው በሚል የተላለፈው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች በሰነድ አስደግፈው በላኩልን መረጃ አመለከቱ። በባህር ዳር ቀበሌ 05 ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው ራህናይል ሆቴል የተገነባው ለ20 አመታት በምህንድስናና የማማከር አገልግሎት እንዲሁም በዲዛይን ስራና በግንባታ ዘርፍ ሙያ በተሰማሩና አቶ አበበ ይመኑ በተባሉ አርክቴክት አማካኝነት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። በ4 መቶ ...
Read More »የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከስልጣን እንዲለቁ ከተለያዩ ወገኖች እየተጠየቁ ነው
(ኢሳት ዜና –ጳጉሜ 1/2009)የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ሞሃመድ (ፋርማጆ) ከስልጣን እንዲለቁ ከተለያዩ ወገኖች እየተጠየቁ ነው። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አብድልከሪም ሼህ ሙሴን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ለሚመራው መንግስት አሳልፈው የሰጡት ፕሬዝዳንቱ ከሀገር ውስጥና ከባህርማዶ በሶማሊያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በሶማሊያ የሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃንም ዘመቻ ከፍተዋል። የሶማሊያ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላትና ታላላቅ ሰዎች ፕሬዝዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ ባለው ስታዲየም በደረሰ አደጋ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከ30 በላይ ቆሰሉ
(ኢሳት ዜና –ጳጉሜ 1/2009)በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ ባለውና በቻይና ኩባንያ በመሰራት ላይ በሚገኘው ስታዲየም በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሰዎች መሞታቸውና ከ30 በላይ መቁሰላቸው ከተደበቀ ከአንድ ወር በኋላ ተጋለጠ። የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙናንን ማለትም እንደ አሶሼትድ ፕረስ፣ ኢቢሲ ኒውስና የመሳሰሉትን ትኩረት የሳበው ይህ አደጋ የተጋለጠው ከአደጋው የተረፉት ሰዎች ለአዲስ ሽታንዳርድ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ ገርጂ ኢምፔሪያል ሆቴል ...
Read More »በምዕራብ ሀረርጌ መኢሶ ከተማ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ በተጣለው ቦምብ ሶስት ተማሪዎች ተጎዱ
(ኢሳት ዜና–ጳጉሜ 1/2009) በምዕራብ ሀረርጌ መኢሶ ከተማ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ በተጣለው ቦምብ ሶስት ተማሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ። ከቦምብ ጥቃቱ በኋላ በሶማሌ ልዩ ሃይል ታጣቂዎችና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል ውጊያ የተደረገ ሲሆን 6 ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል። በውጊያው ከቆሰሉት መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች ጭሮ ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል። ትላንት በመኢሶ በሁለቱ ብሄረሰቦች መካከል የተደረገው የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ...
Read More »በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 118 የሸንኮራ አገዳ ማመላለሻ ተጎታች ጋሪዎችን ለመግዛት የወጣውን ጨረታ በሚስጥር ለሬይስ ኢንጂነሪንግ ለመስጠት መታቀዱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 30/2009) በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 118 የሸንኮራ አገዳ ማመላለሻ ተጎታች ጋሪዎችን ለመግዛት የወጣውን ጨረታ በጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ለሚመራው ሬይስ ኢንጂነሪንግ በሚስጥር ለመስጠት ቅድመ ስምምነት መደረጉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በሼህ መሐመድ አላሙዲን ከፍተኛ አክሲዮን ድርሻ በባለቤትነት የሚተዳደረው ሬይስ ኢንጂነሪንግ ማሽነሪዎችን ለማስመጣት ከጨረታው በፊት ከአንድ የብራዚል ኩባንያ ጋር መፈራረሙን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አጋልጠዋል። የ150 ሚሊየን ብር ግምት ባለው ጨረታ እየተሳተፉ ...
Read More »ኢርማ የተባለው አደገኛ አውሎ ንፋስ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሆነችው ፍሎሪዳ በመገስገስ ላይ ነው
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 30/2009) ኢርማ የተባለው አደገኛ አውሎ ንፋስ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሆነችው ፍሎሪዳ በመገስገስ ላይ መሆኑ ታወቀ። የፍሎሪዳ ግዛት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ያወጀ ሲሆን የአሜሪካ የፌደራል መንግስትም ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ኢርማ የተባለው አደገኛ አውሎ ንፋስ ሐርቬይ የተባለው ዝናብ የቀላቀለው አውሎ ንፋስ ሒውስተንን በከፍተኛ ደረጃ ከመታ ከቀናት በኋላ ይከሰታል መባሉ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል። በቴክሳስ ግዛት ሒውስተን ከደረሰው አደጋ የከፋ ሁኔታ ...
Read More »