(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010) በኦሮሞና ሶማሌ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተፈናቅለው ወደ ሀረር መግባታቸው ታውቋል። ሁለቱ ክልሎች እየተወዛገቡ ነው። ከሁለቱም ወገኖች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ወደ አጠቃልይ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አስተላልፈዋል። ይህ ግጭት በአገዛዙና በህዝብ መካከል ብቻ መሆኑን በሶማሌ እና ኦሮሚያ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢሳት ...
Read More »በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ተቃውሞ እየተካሄደ ነው
(ኢሳት ዜና–መስከረም 3/2010)በምስራቅ ኢትዮጵያ በሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። አጠቃላይ የተቃውሞ ሰልፍም እንዲደረግ በኦሮሞ ወጣቶች ጥሪ መተላለፉ ተሰምቷል። ዛሬ በሀረርና በድሬዳዋ ተቃውሞ ተጀምሯል። የስራ ማቆም አድማም ተመቷል። በድሬደዋ ወታደሮች በብዛት መግባታቸው እየተነገረ ነው።በአወዳይ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል መንግስት ግጭቱ ቆሟል ሲል መግለጫ ሰጥቷል። ግጭቱ ቀጥሏል። የቀውስ ቀጠናው አድማሱን ...
Read More »የጦር ጄኔራሎችን ጨምሮ ለ7 ወታደራዊ ባለሙያዎችና ለቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጀግንነት ሽልማት ተበረከተ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 3/2010)በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጥር በተገኙበት የጀግኖች ምሽት ፕሮግራም ተካሄደ። በስነስርአቱም ሶስት የጦር ጄኔራሎችን ጨምሮ ለ7 ወታደራዊ ባለሙያዎችና ለቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ሃይል የጀግንነት ሽልማት ተበርክቷል። በጀግኖች ምሽት ክብረ በአል ላይ ተገኝተው ለተመረጡት ጀግኖችና ተወካዮቻቸው ሽልማቱን የሰጡት የኮሪያው ዘማች ሻምበል ማሞ ሀብተወልድ ናቸው። በኢትዮጵያና ሶማሊያ ጦርነት በአየር ለአየር ውጊያ የሶማሊያ ጀቶችን መተው የጣሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሸናፊ ...
Read More »የኢሳት 7ኛ አመት በሴንትሊዊስ ሚዙሪ ተከበረ
(ኢሳት ዜና –መስከረም 3/2010) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ/ኢሳት/7ኛ አመት በሴንትሊዊስ ሚዙሪ በድምቀት ተከበረ። በአሉ ሲከበርም ኢሳት በ7 አመት ጉዞው የተጎናጸፋቸው በርካታ ድሎች ተነስተዋል ያጋጠሙት ችግሮችም ተዳሰዋል። ኢሳት የተመሰረተበትን 7ኛ አመት በማስመልከት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና አህጉራት እየተካሄደ ያለው ዝግጅት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 9/2017 በሚዙሪ ግዛት ሴንትሊዊስ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። ከኢትዮጵያ አዲስ አመት ጋር ተያይዞ በተዘጋጀው በዚህ አመታዊ ፕሮግራም ላይ ...
Read More »ከሕወሃት ጋር ቅርበት ያላቸው አንዳንድ የቅማንት ተወላጅ ነጋዴዎችና የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የሕወሃት የጦር አዛዦች በሚስጥር መምከራቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 3/2010) በአማራ ክልል ከሕወሃት ጋር ቅርበት ያላቸው አንዳንድ የቅማንት ተወላጅ ነጋዴዎችና የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የሕወሃት የጦር አዛዦች በጭልጋ አቅራቢያ ሰርባ በተባለ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በሚስጥር መምከራቸው ተሰማ። በሕወሃት ወታደራዊ አዛዦች የተመራው ስብሰባ የተካሄደው በሰሜን ጎንደር ሕዝበ ውሳኔ ይካሄድባቸዋል በተባሉ ቀበሌዎች የአማራ ተወላጆችን ነን የሚሉ መብዛታቸው አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ ነው። በሌላ በኩል የሕወሃት ካድሬዎች ሕዝበ ውሳኔ በሚካሄድባቸው 12 ...
Read More »በፍሎሪዳ ኢርማ አውሎ ንፋስ 25 በመቶ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) በአሜሪካ የፍሎሪዳ ግዛትን የመታው ኢርማ አውሎ ንፋስ 25 በመቶ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ተሰማ። የሀገሪቱ የፌደራል የአስቸኳይ ጊዜ መስሪያ ቤት 65 በመቶ የሚሆኑት መኖሪያ ቤቶችም ከባድ በሚባል ሁኔታ መጎዳታቸውን አስታውቋል። 60 በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎች እስካሁን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ ሆነው በጨለማ እንደተዋጡ ናቸው ይላል ቢቢሲ በዘገባው። በፍሎሪዳ ከአውሎ ንፋሱ ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውም ታውቋል። ...
Read More »አንድ የእስራኤል ኩባንያ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረተ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) አንድ በኢትዮጵያ በማእድን አሰሳ ላይ የነበረ አንድ የእስራኤል ኩባንያ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መሰረተ። ዘሔግ ኔዘርላንድ በተመሰረተው በዚህ ክስ አይ ሲ ኤል የተባለው የእስራኤል ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት የ198 ሚሊየን ዶላር ካሳ መጠየቁም ተመልክቷል። የእስራኤሉ ኩባንያ አይ ሲ ኤል በኢትዮጵያ መንግስት ላይ በኔዘርላንድ ዘሔግ ክሱን የመሰረተው ስምምነቱ የተካሄደው በኔዘርላንድ በመሆኑ እንደሆነም አስታውቋል። በኢትዮጵያና በኔዘርላንድ መካከል የተፈረመውን የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ...
Read More »በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሀዝ አድጎ በሐገሪቱ የኢኮኖሚ መናጋት እየፈጠረ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሀዝ አድጎ በሐገሪቱ የኢኮኖሚ መናጋት እየፈጠረ መሆኑን የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ገለጹ። የማእከላዊ ስታስቲክስ ማእከል በበኩሉ በተለይ ከፍተኛ የእህል ዋጋ ግሽበት በመኖሩ የኢኮኖሚ ቀውስ መከሰቱን ገልጿል። በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የዋጋ ግሽበቱን ከ8 በመቶ በታች አደርገዋለሁ እያለ ሲዝት ቢቆይም በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ መጠን ጨምሮ 10 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ታውቋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የተመዘገበው ...
Read More »የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የግጨው ስምምነትን ተከትሎ ባለው ተቃውሞ ዙሪያ ሊመክር ነው
(ኢሳት ዜና–መስከረም 2/2010) የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከነገ በስቲያ ሲጀምር የግጨው ስምምነትን ተከትሎ ባለው ተቃውሞ ዙሪያ እንደሚመክር የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በሰሜን ጎንደር የቅማንት የሕዝበ ውሳኔ ከመካሄዱ በፊት በአካባቢው ውጥረት መከሰቱም የማእከላዊ ኮሚቴው መነጋገሪያ አጀንዳ ይሆናል ተብሏል። ማእከላዊ ኮሚቴው በቀጣይ ጊዜ ከስልጣን በሚወገዱ አባላት ዙሪያም ይመክራል። የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በሶስት ቡድን የተከፈለ በቅርበትና በአካባቢ ...
Read More »የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የኦሮሞ ተወላጆች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ
(ኢሳት ዜና –መስከረም 2/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የኦሮሞ ተወላጆች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ታወቀ። ይህን ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ሀረር ከተማ መሸሻቸው ተገልጿል። በምስራቅ ኢትዮጵያ በሶማሌና ኦሮሚያ ወሰኖች ላይ የተጀመረው ግጭትም መባባሱ ተሰምቷል። በምስራቅ ሀረርጌ በርካታ ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። በደደርና አወዳይ በትንሹ 3 ሰዎች ተገድለዋል። በኦሮሞና ሶማሌ ክልል ወሰኖች ዙሪያ የተጀመረው ውጊያ በቀጠለበት ከሶማሌ ክልል የኦሮሚያ ተወላጆች እንዲወጡ መደረጋቸው በኦሮሚያ ...
Read More »