(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) ያለህዝብ ፍቃድ በፖለቲካ ውሳኔ በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ተጠየቀ። ትላንት በ8 ቀበሌዎች በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ 7ቱ ቀበሌዎች በነባሩ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ስር መቆየትን መምረጣቸው ተገልጿል። ይህን ተከትሎም ቀደም ሲል በህወሃት መንግስት በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ የትላንቱን ህዝበ ውሳኔ ውጤት በፌደሬሽን ምክርቤት በኩል እንደሚገለጽ አስታውቋል። ...
Read More »የኬንያ ፍርድ ቤት 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ሲል ውሳኔ አሳለፈ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010) የኬንያ ፍርድ ቤት ወደ ሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸው 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊትም የአንድ ወር እስራትና እያንዳንዳቸው 20 ሺ ሽልንግ እንዲቀጡም ወስኗል። አብዛኞቹ እድሜያቸው በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሆነ የተገለጸው ኢትዮጵያውያን ወደ ኬንያ በህገወጥ መንገድ የገቡት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሸጋገር ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ያቀረበባቸውን ክስ አምነዋል። ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ በሚል በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ለመሸፋፈን እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010)በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤያለሁ በሚል በሀገሪቱ ሕዝብ ላይ በአንድ ፈላጭ ቆራጭ የፓርቲ መዋቅር የሚያደርሰውን በደል ለመሸፋፈን እየሞከረ መሆኑን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው ጸሃፊ ግራህም ፒብልስ ገለጸ። ጸሀፊው ጉዳዩን አስመልክቶ ባቀረበው ሃተታ እንደገለጸው ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ምእራባውያን ኢትዮጵያን የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች በሚል የሚያቀርቡት ሪፖርት የአገዛዙን ግፍና በደል ለመሸፈን ምክንያት ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባለው ...
Read More »አዴሃን በጠገዴ ግጨው አካባቢ ለትግራይ ክልል የተሰጠው ቦታ የማያባራ የሕዝብ ግጭት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠነቀቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን/ በጠገዴ ግጨው አካባቢ ለትግራይ ክልል በብአዴን ተላልፎ የተሰጠው ቦታ የማያባራ የሕዝብ ግጭት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠነቀቀ። የትግራይና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በቅርቡ ያደረጉት ስምምነት የሕዝብን ይሁንታ ያላካተተ በመሆኑ አካባቢውን ወደ ግጭትና ትርምስ ሊወስደው ይችላል ብሏል። መላው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የአማራ ሕዝብ ወልቃይትን ለማስመለስ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን/ጥሪ አቅርቧል። በቅርቡ በግጨው ጉዳይ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ሊደረግ የታቀደውን ህዝበ ውሳኔ በመቃወም በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) በሰሜን ጎንደር በ12 ቀበሌዎች ሊደረግ የታቀደውን ህዝበ ውሳኔ በመቃወም በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ። ዕሁድ ሊደረግ በታቀደው በዚሁ ህዝበ ውሳኔ ሁለቱም ወገኖች ባለመሳተፍ እቅዱን እንዲያከሽፉም ጥሪ ተደርጓል። በመተማና ሽንፋ አካባቢዎች ግጭት ተፈጥሯል። ለዕሁዱ ህዝበ ውሳኔ በህወሀት የተሰማሩ የምርጫ አስፈጻሚዎችም ከየጣቢያ በህዝብ እየተባረሩ መሆኑ ታውቋል። ከ12ቱ ቀበሌዎች በ4ቱ ምርጫው መራዘሙ የተገለጸ ሲሆን በየአካባቢው ያለው ውጥረት በህዝበ ...
Read More »በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቃዮች ቁጥር ጨመረ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 5/2010) በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ መሆኑ ተገለጸ። ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ወደ ድሬዳዋና አዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች መግባታቸው ተገልጿል። በጂጂጋ የ28 ሰዎች የቀብር ስነስርዓት ዛሬ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፡ ትላንት ምሽት በከተማዋ የተደራጀ ዘረፋ ሲካሄድ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በጂጂጋ ከተማ የሸቀጦችና የምግብ ዋጋ መጨመሩን ...
Read More »የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የቴክኖሎጂ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ተጋለጠ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያው አገዛዝ ዜጎቹን እንዲሰልል የቴክኖሎጂ እገዛና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ኢንተርሴፕት የተባለ ተቋም አጋለጠ። ብሔራዊ የደህንነት ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የስለላ መረብ እንዲዘረጋ ትልቅ እገዛ ማድረጉን መረጃዎቹን ያሰባሰበው ይሄው ተቋም ገልጿል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየአመቱ የሀገራትን ሰብአዊ መብት አያያዝ በማስመልከት በሚያወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ዜጎቿን መሰለሏንና ማፈኗን ቢያወግዝም የዚሁ ድርጊት ተባባሪ መሆኑ ግን ትክክል አለመሆኑን ተቋሙ ተችቷል። ...
Read More »የአማራና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች ጠገዴ ላይ ያሳለፉትን ውሳኔ ልሳነ ግፉአንና የጠለምት አማራ ማንነት ኮሚቴ በጋራ እንደሚቃወሙት አስታወቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)የአማራና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንቶች ጠገዴ ወረዳ ላይ ያሳለፉትን ውሳኔ ልሳነ ግፉአንና የጠለምት አማራ ማንነት ኮሚቴ በጋራ እንደሚቃወሙት አስታወቁ። ሕወሃትና ተላላኪው ብአዴን በአዲሱ አመት ዋዜማ ለመላው የጎንደር ህዝብ የሰጡት ስጦታ ቢኖር ሰላምና አንድነቱን ሳይሆን አካሉ የሆነውን የጠገዴ ማህበረሰብን ለሁለት እንደ ቅርጫ መቀራመትን ነው በማለት እርምጃውን በጽኑ አውግዘዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የወልቃይትን መሬት ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ሕዝቡ እስራት፣ድብደባና ...
Read More »በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል የተፈጠረው የወሰን ችግር የከፋ የሰብአዊ መብት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ሰብአዊ መብት ጉባኤ አሳሰበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010) በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል የተፈጠረውና እየቀጠለ ያለው የወሰን ችግር መዳረሻውን ለመተንበይ የሚያስቸግር የከፋ የሰብአዊ መብት ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ሰብአዊ መብት ጉባኤ አሳሰበ። በአሁኑ ወቅት በአራት ክልሎችና አካባቢዎች ከወሰን ጋር በተያያዘ ችግር መከሰቱና ውጥረት መንገሱን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የሰብአዊ መብት ጉባኤ በክልሎች መካከል ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮች በአስቸኳይ እልባት ይሰጣቸው በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በአራት ክልሎችና አካባቢዎች ...
Read More »ኦህዴድና ሶህዴፓ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው
(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2010)ኦህዴድና ሶህዴፓ እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ሰሞኑን ከተከሰተውና ተባብሶ ከቀጠለው እልቂት ጋር ተያይዞ የሁለቱ ክልላዊ መንግስታት ቃል አቀባይ ቢሮዎች አንዱ ሌላኛውን ተጠያቂ የሚያደርግበት መግለጫ አውጥተዋል። በአቶ አብዲ መሀመድ ኦማር የሚመራው የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን በኦሮሚያና ሶማሌ ወሰን አካባቢ የተነሳው ግጭት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚደገፍና በክልሉ የታጠቁ ሃይሎች፣በክልሉ ፖሊስ፣ሚሊሺያና የኦነግ ቄሮ ...
Read More »