በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 9/2010) በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል። ትላንት ምሽት የተጀመረው የገብረጉራቻው አመጽ በርካታ የመንግስት ተሽከርካሪዎችን በእሳት በማቃጠል ተካሂዷል። ዛሬ በአምቦና በወለጋ ሆሮጉድሩ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት የህወሃት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ ጠይቋል። ሕዝባዊ ተቃውሞው በተለያዩ አካባቢዎች በመደረግ ላይ ነው። ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለው። በርካታ ቤቶች በእሳት ወድመዋል። ህዝቡ ይህን እርምጃ ሲወስድ በተጠናና በስልጣን ላይ ካለው ስርዓት ጋር ግንኙነት ካላቸው ጋር ...

Read More »

የኬንያ ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በጥይትና በአስለቃሽ ጋዝ እየበተነ ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 9/2010)የኬንያ የፖሊስ ሃይል በሀገሪቱ በድጋሚ ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በጥይትና በአስለቃሽ ጋዝ እየበተነ መሆኑ ታወቀ። የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሕዝቡ ለተቃውሞ እንዳይወጣ ጥሎት የነበረውን እገዳ ውድቅ ቢያደርግም የሀገሪቱ ፖሊስ ግን ሰልፈኞቹን ከመበተን ወደ ኋላ እንዳላለ ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በድጋሚ የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፍትሃዊ ሆኖ ስለመካሄዱ በእርግጠኝነት መናገር ...

Read More »

በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ያለእቅድና ጥናት የተተከለው የሸንኮራ አገዳ ኪሳራ አደረሰ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 9/2010)በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ያለእቅድና ጥናት የተተከለው የሸንኮራ አገዳ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ የ7 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማስከተሉን የፕሮጀክቱ ሃላፊዎች አመኑ። ኢሳት በሸንኮራ አገዳው መበላሸት ምክንያት ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱን የውስጥ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት የምርምርና የልማት ማዕከል ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ኪዳኔ ተስፋሚካኤል እንደገለጹት አገዳውን ከማሳው ለማስወገድና ሁለተኛውን የሸንኮራ ምርት እንዲቀጥል ...

Read More »

ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ግብጽ እንቅፋት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰች ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 9/2010)በኢትዮጵያ ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ግብጽ እንቅፋት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል የግንባታው ብሔራዊ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት ገለጸ። ግብጽ በበኩሏ በገለልተኛ አለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚቴ ይቀርባሉ የተባሉ ሁለት ጥናቶች በመዘግየታቸው ጉዳዩ ክፉኛ አሳስቦኛል ስትል በመስኖ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች። በአዳይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ መክረዋል።ግድቡንም ጎብኝተዋል። የአባይ ጉዳይ ለኢትዮጵያውያን የልማት ተስፋ ለግብጽ ደግሞ ...

Read More »

የኬንያ አንድ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን ከሀገር ኮበለሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በኬንያ አንድ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን በደረሰባቸው የግድያ ዛቻ ምክንያት ወደ አሜሪካ መኮብለላቸው ተሰማ። የከፍተኛ ባለስልጣኗ ከሀገር መኮብለል በድጋሚ በሀገሪቱ ሊካሄድ በዝግጅት ላይ ያለውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተአማኒነትን ጥርጣሬ ውስጥ መክተቱ ታውቋል። በሌላ ዜና በላይቤሪያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ በቂ ድምጽ ማግኘት አልቻሉም በሚል ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ተወስኗል። በኬንያ የሚካሄደው የድጋሚ ምርጫ በሚቀጥለው ሳምንት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ...

Read More »

የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ ተራዘመ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በኢትዮጵያ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ መራዘሙ ተነገረ። የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተወሰነው በሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ነው ተብሏል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተፈለገው ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄዱ ሌላ ቀውስ ይፈጥራል በሚል ነው። ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦለት በህዳር 2010 ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄድ ...

Read More »

የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ። አዋጁ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ፖልሲን ይቃርናል ተብሏል። በወረቀት ላይ የሰፈረው ፖሊሲ በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሚኖር የምልመላና የእድገት ስራ በግለሰቡ ብቃት ላይና በዚሁ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያዛል። አሁን ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የሚደረገው የስራ ...

Read More »

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉት ዜጎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010)በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉት ዜጎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ። ከተፈናቀሉት ውስጥ ከ100 የሚበልጡ እናቶች ድንኳን ውስጥ ልጆቻቸውን መገላገላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ይፋ አድርገዋል። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በችግሩ ሳቢያ የአንዱ ክልል ተማሪ ወደ ሌላው ክልል ዩኒቨርስቲ ሄዶ ለመማር እንደማይፈልግም ተመልክቷል። የመንግስት ቃልአቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ማክሰኞ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ...

Read More »

በሶማሊያ የቦንብ ጥቃት ሰለባዎችን ለመታደግ አለም አቀፉ ማህበረሰብ መንቀሳቀስ ጀመረ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 7/2010)በሶማሊያ ሞቃዲሾ የደረሰውን ዘግናኝ የሽብር ፍጅት ተከትሎ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰለባዎቹን ለመታደግ መንቀሳቀስ ጀመረ። ወደ 300 ሰዎች ያለቁበትንና ከ300 በላይ የቆሰሉበትን ይህንን የቅዳሜውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካና የኳታር አውሮፕላኖች መድሃኒት ጭነው ሞቃዲሾ አርፈዋል። ቱርክ ከቆሰሉት ውስጥ 40 የሚሆኑትን ለህክምና ወደ ሃገሯ ስትወስድ ጎረቤት ጅቡቲን ጨምሮ ሀገራት ሰብአዊ እርዳታ በማድረግ ላይ መሆናቸውም ተመልክቷል። ሕዝብ በሚበዛበት ሆቴልና የመንግስት ሕንጻዎች ባሉበት ...

Read More »

የኢሳትን 7ኛ አመት ዝግጅቶች በአለም የተለያዩ አካባቢዎች ተካሄዱ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 7/2010)የኢሳትን 7ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የአለም አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን በማከናወን በሀገራቸው የሚካሄደውን የለውጥ ትግል እያገዙ ነው። በሰሞኑ ብቻ በዳላስ ቴክሳስና በላስቬጋስ እንዲሁም በአውስትራሊያ አድላይድና ፐርዝ በመቀጠልም በአውሮፓ ኖርዌይ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ተካሂደዋል። በዝግጅቱ በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮችና ኢሳት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ውይይትና ምክክር ተደርጓል። በዳላስ ቴክሳስ በየአመቱ የሚካሄደው የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት እጅግ ደማቅና በርካታ ...

Read More »