ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዜና –ጥቅምት 13/2010)የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስልጣናቸውን እንዲለቁ ዓለም ዓቀፍ ግፊት እየተደረገ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ የዚምባቡዌውን ፕሬዝዳን ሮበርት ሙጋቤን የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርገው መሾማቸውን ተከትሎ በመላው ዓለም ቁጣ ተቀስቅሷል። ዶ/ር ቴድሮስ ወዲያውኑ ሹመቱን በመሰረዝ የመጣባቸውን ተቃውሞ ሊያበርዱ ቢሞክሩም ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው ዓለም ዓቀፍ ግፊት ግን መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። ዓመት ...

Read More »

በናይጄሪያ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 13 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010) ናይጄሪያ ውስጥ ሶስት ሴቶች በሰውነታቸው ላይ በተጠመደ ቦንብ ባደረሱት ፍንዳታ 13 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆሰሉ። የሀገሪቱ ጦር ቦኮ ሃራም የተባለው አክራሪ ቡድን ሊደመሰስ ጥቂት ጊዜ ብቻ ቀርቶታል እያለ በሚናገርበት ወቅት የተፈጸመ ከባድ ጥቃት መሆኑም ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በሶማሊያ ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ አቅራቢያ በደረሰ የመንገድ ዳር ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል። በናይጄሪያ እሁድ እለት ...

Read More »

በውጭ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በእርቅና ሰላም ላይ ያተኮረ ጉባዔ ጠራ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010) በኢትዮጵያ እርቅና ሰላም ላይ ያተኮረ ጉባዔ መጥራቱን በውጭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ። በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶሱ ከህዳር 7 ጀምሮ የሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ዋነኛ የምክክር አጀንዳው እርቅና ሰላም እንደሚሆን ገልጿል። ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ኢትዮጵያውያን የዘር የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርጉ ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሰለፉ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪ አቅርቧል። የቅዱስ ሲኖዶሱ ...

Read More »

አምባገነኑን የሕወሃት አገዛዝ ለማስወገድ ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 13/2010)በኢትዮጵያ በውድቀት አፋፍ ላይ ያለውን አምባገነን የሕወሃት አገዛዝ ለማስወገድ ሁሉም የለውጥ ሃይሎች በጋራ እንዲቆሙ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው በአሜሪካ ቨርጂኒያ ያካሄደውን የጥምር ድርጅቶቹን ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በኢትዮጵያ ሕዝቡ የሚፈልገውን ለውጥና ሕጋዊ ስርአት እውን ለማድረግ ሁሉም የለውጥ አካላት ሊተባበሩ ይገባል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ ምክር ቤት መግለጫ ሀገሪቱ ወደ አስከፊ ቀውስ ከመግባቷ በፊት ...

Read More »

ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ አሳስቦናል አሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ እንዳሳሰባቸውና አለመቻቻልና ከፋፋይ ፖለቲካ እየተባባሰ መምጣቱ ለሀገሪቱ አደጋ ነው አሉ። ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ የወቅቱን ፕሬዝዳንት ስም ሳይጠቅሱ አሁን ያለው አስተዳደር እየፈጠረ ያለው የከፋፋይና የማስፈራራት ፖለቲካ በሀገሪቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል። ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ በተለያየ ወቅት በተለያየ መድረክ ላይ ስለወቅቱ የሀገራቸው ጉዳይ ንግግር አድርገዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ...

Read More »

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በጎንደር ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ህብረተሰቡ እንዳይካፈል ተጠየቀ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) በፋሲል ከነማ የክለብ አርማ ስም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጃኖ የሚል ቢራ ለማስተዋወቅ ነገ በጎንደር ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ህብረተሰቡ እንዳይካፈል የአካባቢው ወጣቶች አስጠነቀቁ። ባላገሩ በሚል ይዞ የመጣው ቢራ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለኪሳራ የተዳረገው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አሁን ደግሞ ጃኖ በሚል አዲስ ቢራ ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱ ከንቱ ሙከራ ነው ሲሉ ወጣቶቹ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ኮንሰርቱ የኦሮሞ ወገኖቻችን እየተገደሉ ባሉበት መዘጋጀቱና ከጃኖ ቢራ ...

Read More »

አቡነ ማትያስ ስራዬን ለመስራት ተቸግሬያለሁ አሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ስራዬን ለመስራት ተቸግሬያለሁ በማለት ስልጣን ለመልቀቅ መናገራቸውን የቤተክህነት ምንጮችን ዋቢ ያደረጉ መረጃዎች አመለከቱ። ሐራ ተዋህዶ የተባለው በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው ድረገጽ እንደዘገበው ፓትሪያርኩ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ በቃል ያሳወቁ ሲሆን በቀጣይም በጽሁፍ ያሳውቃሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፉት 4 ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቤተክርስቲያኒቱ 36ኛ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በዋሽንግተን ...

Read More »

በኢትዮጵያ ለአገዛዙ ቁልፍ በሆኑ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ልዩ ጥበቃ እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ለአገዛዙ ቁልፍ በሆኑ የመንግስት ተቋማት ውስጥ ልዩ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ልዩ ጥበቃው ከአገዛዙ ባፈነገጡ ባለስልጣናት መፈንቅለ መንግስት ሊካሄድ ይችላል በሚል ስጋት ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድ ጭንቀትና ውጥረትን ፈጥሯል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት የሕዝቡ ተቃውሞ የፈጠረው ቀውስ በአገዛዙ ባለስልጣናት በኩልም የእርስ በርስ ሽኩቻና አለመተማመኑ አይሏል። ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ያሉትን የተቃውሞ ሰልፎች ማን እንዳቀናበራቸው ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት10/2010)በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ያሉትን የተቃውሞ ሰልፎች ማን እንዳቀናበራቸውና አላማቸው ምን እንደሆነ ምርመራ ላይ መሆኑን የክልሉ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ በበኩሉ በኦሮሚያ ባለው ግጭት ሀገር አለን ማለት የማንችልበት ደረጃ ላይ እየደረስን በመሆኑ ያሳስበናል ብሏል። በኦሮሚያ ክልል ተጠናክሮ የቀጠለውን ሕዝባዊ አመጽና የተቃውሞ ሰልፎች ተከትሎ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የሕወሃት ንብረት ለሆነው ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በኢሉባቦርና በጂማ ሊሙ ገነት ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) በኦሮሚያ ክልል በወለጋ፣ በኢሉባቦርና በጂማ ሊሙ ገነት ተቃውሞ መካሄዱ ተገለጸ። በሊሙ ገነት ህዝቡ ሰፋፊ የቡና ማሳዎችን በመቆጣጠር እየተከፋፈለው መሆኑንም ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ተቃውሞው ኩታ ገጠም በሆኑ የአማራ ክልል መንደሮችም መግባቱ እየተነገረ ነው። በኢሉባቦር በተካሄደው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በሰሜን ሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀል ከተማ በነበረው ተቃውሞ በመንግስት ታጣቂዎች በተወሰደ እርምጃ 2 ሰዎች መገደላቸውንና 8 ሰዎች መቁሰላቸውን ...

Read More »