(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በ8 ጉዳዮች በሽብር ወንጀል በእንግሊዝ መንግስት የተከሰሱት ታዋቂው ምሁርና ፖለቲከኛ ዶክተር ታደሰ ብሩ በተከሰሱባቸው ሁሉም ጉዳዮች ነጻ ተባሉ። ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በሕዝብ በተመረጠ ዳኝነት/ጁሪ/ ዶክተር ታደሰ ብሩን በሙሉ ድምጽ ነጻ ናቸው ብሏል። ዶክተር ታደሰ ብሩ ሂደቱን ሲከታተሉና ሲጨነቁ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል። ዶክተር ታደሰ ብሩ የተከሰሱት የሽብር ወንጀሎች ለምርምርና ለነጻነት ትግል የተጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍትን ...
Read More »የሶማሌ ክልል ተወላጆች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ከ5ሺህ በላይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ያለውሃና ምግብ በመቆየታቸው ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ። ሰሞኑን ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የስልክም ሆነ የትራንስፖርት ግንኙነት ተቋርጧል። አስቸኳይ ድጋፍ ካልደረሰላቸው ዕልቂት ሊከሰት እንደሚችል በማስጠንቀቅ የሶማሌ ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ መግለጫ አውጥቷል። በአራት ቀበሌዎች ተጠልለው የሚገኙ የሶማሌ ተወላጆችን ለመደገፍ የኦሮሞ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል። በአካባቢው ሌላ ...
Read More »ሳውዳረቢያ የተተኮሰባትን ባሊስቲክ ሚሳኤል አመከነች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ሳውዳረቢያ ከሃውቲ አማጽያን የተተኮሰባትን ባሊስቲክ ሚሳኤል ሪያድ አቅራቢያ ማምከኗን አስታወቀች። የሃውቲው አል ማሲራህ ቴሌቪዥን እንዳለው በአማጽያኑ የተተኮሰው ሚሳኤል በአል-ያማማ ቤተመንግስት በስብሰባ ላይ የነበሩ የሳውዲ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ነበር። ሳውዳረቢያና አሜሪካ ኢራን የሃውቲ አማጽያንን ሚሳኤል ታስታጥቃለች ሲሉ ይከሳሉ። ኢራን ግን ክሱን ታስተባብላለች። ባለፈው ወርም ተመሳሳይ ሚሳኤል የሪያድን አይሮፕላን ማረፊያ ሊመታ ጥቂት ሲቀረው ነበር ተጠልፎ የወደቀው። የሃውቲ አማጽያን ላለፉት ...
Read More »በሃይማኖት አባቶች ስም እንቅስቃሴ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ እንዲገባ በሃይማኖት አባቶች ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የኢሳት ምንጮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለ ክልሉ ፈቃድ እንዲገባ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ እንዲያደርጉ ታዘዋል። የሃይማኖት አባቶች በቀጣዮቹ ቀናት በዚህ ዙሪያ የጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። በፌደራልና በአርብቶ አደሮች ሚኒስቴር በኩል ለቀረበው ጥያቄ የሕወሃትና ...
Read More »አቶ አባዱላ ገመዳ ቅሬታቸውን አሰሙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ያመለከቱት አቶ አባዱላ ገመዳ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ተሰማ። አቶ አባዱላ በእኔም ሆነ በድርጅቴ ኦሕዴድ ላይ የተፈጠረው ችግር በኢሕአዴግም ሆነ በመንግስት መዋቅሮች ውስጥ የሕወሃት የበላይነት በመኖሩ ነው ብለው እቅጩን ተናግረዋል። በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ቅሬታቸውን በይፋ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ ከተወሰኑ የኦሕዴድ አባላት ድጋፍ ቢያገኙም የተወሰኑት ...
Read More »በመከላከያ ሰራዊት 7 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በኦሮሚያ ክልል ከያቤሎ እስከ ሞያሌ መስመር በመከላከያ ሰራዊት 7 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። በአከባቢው ባሉ ወረዳዎች ግጭት ተፈጥሯል። መንገዶች መዘጋታቸው ታውቋል። በመቱ፣ በነቀምት፣ በደምቢዶሎ፣ በዋደራ፣ በሻኪሶና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ዛሬ ተቃውሞች ተካሂደዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግጭት ተለይቶት የማያውቀው የሞያሌ መስመር በየዕለቱ ሰዎች መገደላቸው እየተለመደ መቷል። በተለይም የመከላከያ ሰራዊትና የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በሚወስዱት ርምጃ የሚገደሉ ሰዎች ...
Read More »በሚሊሺያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በአማራ ክልል በጎጃምና ጎንደር መስመር ዋና ዋና መንገዶች ላይ በሚሊሺያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻና ጥበቃ መጀመሩ ተገለጸ። የህዝብ ንቅናቄ በተፈጠሩባቸው ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት በብዛት መግባቱ ተገልጿል። በዩኒቨርስቲዎች አሁንም ትምህርት አልተጀመረም። በአፋር፣ ጋምቤላና አሶሳ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎች የንብረት ማውጫ ፍቃድ መከልከሉም ታውቋል። በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ውጥረት መንገሱን የሚያሳዩ መረጃዎች ለኢሳት ደርሰውታል። በጎጃምና በጎንደር መስመሮች ከፍተኛ ፍተሻና ጥበቃ ...
Read More »ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በኦሮሚያ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የፋሲል ከነማን ተጫዋቾች “ፋሲል ኬኛ” በማለት በሞተረኛ ፖሊሶች አጅበው ፍቅራቸውን በመለገስ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል። የአዳማ ከነማ ህዝብ ለፋሲል ከነማ ያደረገው አቀባበል በኦሮሚያና አማራ ሕዝብ መካከል ያለው ትስስር ጠንካራ መሆኑን አመላክቷል። የሕወሃትን አገዛዝ በመቃወም በአንድ ወቅት የጎንደርና የባህርዳር ህዝብ የኦሮሞ ደም ...
Read More »ሲሪል ራምፖሳ አሸነፉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ/ኤ ኤን ሲ/ ፓርቲን የመሪነት ቦታ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሲሪል ራምፖሳ አሸነፉ። የመሪነቱን ቦታ ማን ይወስዳል የሚለውን ውጤት ለማወቅ ደቡብ አፍሪካውያን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። አዲሱ ተመራጭ ሲሪል ራምፖሳ በስልጣን ላይ ያሉትን የሀገሪቱን ፕሬዝዳንትና የፓርቲውን መሪ ጃኮብ ዙማን ይተካሉ። የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ የኤ ኤን ሲ ፓርቲ መሪን ለመምረጥ በተካሄደው ምርጫ በምክትል ፕሬዝዳንቱ ሲሪል ራምፖሳና በቀድሞው የአፍሪካ ...
Read More »የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መኖሪያ ቤቶች ተሸጡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መኖሪያ ቤቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሽጠው ለመንግስት ገቢ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ። በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ ሞክራችኋል በሚል በተመሰረተባቸው ክስ የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ንብረታቸውም እንዲወረስ በፍርድ ቤት ተወስኗል። ጠቅላይ አቃቢ ህግ አደረኩት ...
Read More »