(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ተሰማ። በባህርዳር መውጪያና መግቢያ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቋል። በእንጅባራ ውጥረት መኖሩ እየተነገረ ነው። በአምቦ መስመር ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመደረግ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አንዳንድ ከተሞች ተመሳሳይ አድማ ተጀምሯል። በኢሉባቡር ጎሬና በወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ሻምቡ ተቃውሞ በመካሄድ ...
Read More »የፈረንጆቹ ገና ተከበረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የፈረንጆቹ የገና በአል በበርካታ የአለም ክፍሎች በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፓፕ ፍራንሲስ በበአሉ ዋዜማ ባስተላለፉት መልዕክት አለም ስደተኞችን እንድታስተናግድ የክርስትና እምነት ግድ ይላል ብለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ቤተልሄም እየተካሄደ ያለው ግጭት በአሉን ጥላ ያጠላበት መሆኑንም መረጃዎች አመልክተዋል። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ትላንት በዋዜማው በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በአውሮፓ ለአክራሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለው ድጋፍ ...
Read More »ቀለብ ስዮም ተፈታች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አመራር ቀለብ ስዮም ከእስር ተፈታች። ሀምሌ 2 ቀን 2007 ወደ እስር ቤት ተወርውራ የነበረችው ቀለብ ስዩም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈባትን ውሳኔ በመቃወም ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበችው ይግባኝ መሠረት 4 ዓመት በእስር እንድትቆይ ተላልፎ የነበረው የእስር ቅጣት ተቀንሶ ወደ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ወርዶ ነበር። በዚሁ መሰረት ቀለብ ስዩም የእስር ጊዜዋን ጨርሳ ዛሬ ...
Read More »አቶ በቀለ ገርባ በጽኑ ታመሙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በጽኑ መታመማቸው ተነገረ። የእስር ቤት ባለስልጣናትም አቶ በቀለ ገርባ ሕክምና ወደሚያገኙበት ሆስፒታል እንዳይሄዱ ማገዳቸውንም ለማወቅ ተችሏል። አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቢኖራቸውም መራመድ ባለመቻላቸው የፍርድ ሂደቱ ተስተጓጉሏል ተብሏል። ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ ክሳቸው ከሽብር ወንጀል ሕገመንግስትን በሃይል ለማፍረስ በመምከር ወደሚል ቢቀየርላቸውም እስካሁን የዋስ ...
Read More »በሀገሪቱ አዲስ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በሀገሪቱ አዲስ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው ባካሄደው የድርጅቱ 2ኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን ገምግሟል። ዶክተር መረራና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሁሉም የኦፌኮ አመራሮች ከእስራት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል። የኦህዴድ መሪዎች ለሕዝብ ላሳዩት ወገናዊነትም አድናቆቱን ገልጿል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመጡ አባላቱ ጋር ያካሄደውን የድርጅቱን 2ኛ ጉባኤ በማስመልከት ባለፈው ...
Read More »መንግስት ችግሮችን በድርድርና በውይይት እንዲፈታ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በኢትዮጵያ የተከሰቱ ችግሮችን መንግስት በድርድርና በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች። አገሪቱን ከውድቀት፣ ሕዝቡንም ከሞትና ከስደት ለመታደግ መንግስት ከባድ ሞራላዊና መንግስታዊ ሃላፊነት እንዳለበትም አሳስባለች። የሃይማኖት አባቶችም አጥፊውን ወገን ያለፍርሃት እንዲገስጹም ጥሪዋን አቅርባለች። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰባት የገለጸችው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በ34ኛው የጳጳሳት መደበኛ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ከመከረች በኋላ መግለጫ ማውጣቷ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በብጹዕ ካርዲናል ...
Read More »በሀገሪቱ ያለው ችግር የብሔር ፖለቲካ ያመጣው መዘዝ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳሰባቸው ታዋቂ ዜጎች በሀገሪቱ ያለው ችግር የብሔር ፖለቲካ ያመጣው መዘዝ መሆኑን ገለጹ። በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ዜጎች በአሁኑ ጊዜ የሰው ሕይወትና ንብረት እየወደመ እንዲመጣ ምክንያት የሆነው ልዩነትን የሚያበረታታው ሕገመንግስት ነው ብለዋል። ከፊሎቹ ይህን ሀሳብ ቢቃወሙም ብዙዎቹ ግን የብሔር ፖለቲካው ያመጣውን መዘዝ ለማስወገድ ሕዝቡ ለአንድነቱ መቆም አለበት ብለዋል። ሕዝባዊና ሀገራዊ እርቅ እንዲደረግ ጥሪ ...
Read More »አንድ የአፍጋኒስታን ተወላጅ 19 ያህል ሰዎችን አቆሰለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ አንድ የአፍጋኒስታን ተወላጅ ሆን ብሎ በመኪና ባደረሰው አደጋ 19 ያህል ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ከደጋው ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ባይኖሩም በአደጋው ከቆሰሉት ሰዎች ግን አራቱ ሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። በሜልቦርን ማዕከላዊ የንግድ ክፍለ ከተማ ለገና ገበያ ወዲያ ወዲህ ሲሉ የነበሩ ሰዎችን በሚያሽከረክረው ሱዙኪ ኤስ ዩ ቪ ተሽከርካሪ የገጨው የ32 ...
Read More »የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞ የከፋ ደረጃ ይደርሳል በሚል የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እንዲገባ እያደረገ መሆኑ ተነገረ። መጪው ጊዜ ያስፈራው የህወሃት መንግስት ቀደም ሲልም ግዙፍ የእህል ጎተራ በማስገንባት እህል ሲያከማች መቆየቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ተጨማሪ እህል ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከአርሶ አደሩ በርካሽ ዋጋ እየገዛ ወደ ትግራይ እያጓጎዘ መሆኑ ታውቋል። የትግራይ ክልል ብዙ እህል ...
Read More »የብአዴን አመራር አባላት የአማራ ሕዝብ ሆድ ብሶታል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የአዲስ አበባ ወረዳዎች የብአዴን አመራር አባላት የአማራ ሕዝብ ሆድ ብሶታል በሕወሃት አገዛዝም ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ነው ሲሉ አማረሩ። የብአዴን ካድሬዎች ያካሄዱት የጥልቅ ተሃድሶ የግምገማ ቃለጉባኤ ኢሳት እጅ ገብቷል። ካድሬዎቹ የሕወሃት የበላይነት ስለመኖሩም ማረጋገጫ በማቅረብ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎች ባካሄዱት ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ በየወረዳዎቻቸው የሚገኙ የሕወሃት አመራሮች ቁልፍ ቦታዎችን እንደተቆጣጠሩ ይፋ አድርገዋል። የሕወሃት የበላይነት በየተቋማቱ ...
Read More »