(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ሆነበት የተባለውና ሁለት ጊዜ የተመረቀው የጎንደር የውሃ ፕሮጀክት መቋረጡ ተገለጸ። የህዝብ ቁጣ ይቀሰቀሳል በሚል ጉዳዩ በሚስጢር መያዙም ታውቋል። በሌላ በኩል ጎንደርን ጨምሮ በአማራ ክልል በበርካታ ከተሞች የውሃና መብራት አገልግሎት መቋረጡ ታውቋል። ከውሃና መብራት ሌላ ዘይትና ስኳር ከገበያ በመጥፋታቸው ህዝቡ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ ላይ ተመልክቷል። የጎንደርን የውሃ ጥም ለአንዴና ለመጨረሻ ...
Read More »ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ደብዳቤ ተጻፈ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) የአሜሪካው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማን በአሜሪካ በሚኖሩ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው የስለላ ተግባር እንዲቆም በማሳሰብ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ደብዳቤ መጻፋቸው ታወቀ። ኮንግረስማን ኮፍማን የህወሃት አገዛዝ በውጭ በሚኖሩ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገው የኢንተርኔት የስለላ ተግባር እየተጠናከረ በመምጣቱ አሜሪካ ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል። የኮሚፕውተር ቫይረስ በማሰራጨት የስለላ ተግባር ለመፈጸም በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ የሚያደርገውን የህወሃት አገዛዝ ተጠያቂ በማድረግ ...
Read More »ኦብነግ የህወሃት ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ በርካታ ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ። የኦጋዴን የዜና ወኪል የኦብነግን አባል ጠቅሶ እንደዘገበው ውጊያው የተካሄድው ታህሳስ 30/2010 ነው። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ውጊያ በመንግስት በኩል ማርጋገጫ ባይገኝም የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው ተመልክቷል። በጃሌሎ መንደር ተደረገ በተባለው በዚህ ውጊያ ከወታደሮቹ መገደልና መቁሰል በተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች፣ጥይቶችና የመገናኛ መሳሪያዎች መማረካቸው ተገልጿል። ...
Read More »በደሴ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) በደሴ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተሰማ። ፒያሳ በሚባለው አካባቢ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የደረሰውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ የእስር ርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑም ታውቋል። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የትግል ጥሪ ወረቀት ሲበተን አድሯል። በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በተበተነው በዚሁ የትግል ጥሪ ህዝቡ የህወሃትን አገዛዝ ለማስወገድ እንዲነሳ ተጠይቋል። ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ የደረሰውን የቦምብ ጥቃት በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ...
Read More »የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሀገር መክዳትና በሽብር ወንጀል ተከሰሱ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) የሰራዊቱን አባላት ለማስከዳትና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጎን እንዲሰለፉ ሲቀሰቅሱ ነበር የተባሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሀገር መክዳትና የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው። ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ይፈታሉ የሚል መግለጫ በተሰጠ ማግስት ክስ የተመሰረተባቸው እነዚህ ወታደሮች 5 መሆናቸውም ታውቋል። ሕገመንግስታዊውን ስርአት ለመጠበቅ የተሰጣቸውን አደራ በመተው የኦነግን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ሌሎች የሰራዊት አባላትንም ሲመለምሉ ነበር በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ...
Read More »አቶ አባይ ወልዱ ከትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትነት ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010) በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ግምገማ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የተባረሩት አቶ አባይ ወልዱ ከትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትነት ቦታቸውም በይፋ ተነሱ። ሁለት የዞን አስተዳዳሪዎችም ከስልጣናቸው የተባረሩ ሲሆን የደህንነት ዋና ሃላፊው የአቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ደግሞ የቢሮ ሃላፊ በመሆን ተሹመዋል። በቅርቡ የሕወሃት ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልልን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መመረጣቸውም ይፋ ሆኗል። አቶ ደብረጺዮን ትግራይ ክልል በመመደባቸው ...
Read More »በግብጽና ሱዳን መካከል የተጀመረው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2010) ሱዳን ደሴቷን ለቱርክ መስጠቷን ተከትሎ በግብጽና ሱዳን መካከል የተጀመረው ውዝግብ መቀጠሉ ተሰማ። ግብጽ ወታደሮቿን ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው የኤርትራ ድንበር ላይ ማስፈሯ የተገለጸ ሲሆን ሱዳንም ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ሙሉ በሙሉ ዘግታለች። ለግብጽና ሱዳን ውዝግብ መንስኤ የሆነው የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሪስፕ ጣይብ ኤርዶጋን ባለፈው ታህሳስ በሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ በሁለቱ መንግስታት መካከል የተደረገው ስምምነት ነው። ሱዳን ነጻነቷን ካገኘችበት እንደ ...
Read More »አንድ ጄኔራል ኢትዮጵያ ውስጥ ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2010) አንድ የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ጄኔራል ኢትዮጵያ ውስጥ መታሰራቸው ተሰማ። ጄኔራሉ ለደቡብ ሱዳኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ታባን ዴንግ ጋይ የቅርብ ሰው ናቸው ሲል ራዲዮ ታማዙጅ ገልጿል። በኢትዮጵያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት ብርጋዴር ጄኔራል ጋች ቶች ባለፈው ጥቅምት ድንበር አቋርጠው በጋምቤላ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ሲዘዋወሩ እንደነበር ዘገባው አመልክቷል። ጄኔራሉ በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት ምንም አይነት ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ታርፓም በተባለ ...
Read More »የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት የሆነው ኤፈርት በ745 ሚሊየን ብር ያስገነባው የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ጀመረ። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በሳምንት 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያስገኘው ይህ ፋብሪካ በቀን እስከ 5 ኪሎ ግራም ወርቅ ያመርታል። ኤፈርት ከዚህም በተጨማሪ በመላዋ ትግራይ የማዕድን ማልማት ስራዎችን ለማከናወን ከ8 የአሜሪካና የካናዳ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል። በዚህ ስምምነት መሰረትም በትንሹ በአመት ከአንድ ...
Read More »የእግር ኳስ ጨዋታ ግጭት አስከተለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 1/2010) በወልዲያ ከነማና በዋልዋሎ እግር ኳስ ቡድን መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ግጭት ማስከተሉ ታወቀ። ግጭቱ የተከሰተው ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሲሆን በፖሊስና በኳስ ደጋፊዎች መካከል ከተከሰተ መለስተኛ ግጭት ባለፈ የከፋ ጉዳት አለመድረሱም ታውቋል። የወልዲያ እግር ኳስ ቡድንና የትግራይ ክልሉ ዋልዋሎ የእግር ኳስ ቡድን የሚያደርጉት ጨዋታ ከሁለቱ ክልሎች ውጪ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ የተወሰነው በክልሎቹ የሚካሄደው ውድድር ...
Read More »