ጃኮብ ዙማ ስልጣን አለቅም አሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የፈጸምኩት ምንም ጥፋት ስለሌለ ከስልጣን የምወርድበት ምክንያት የለም ሲሉ ለፓርቲያቸውም ምላሽ መስጠታቸው ታወቀ። የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ጃኮብ ዙማ በሙስናና በልዩ ልዩ ተደራራቢ የወንጀል ክሶች ተጠያቂ በመሆናቸው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ስልጣን እንደማይለቁ አረጋግጠዋል። ፓርቲያቸው እያቀረበላቸው ያለው ጥያቄም ቢሆን ትክክል ያለሆነና ...

Read More »

ቶኒ ብሌር በዱከም ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት ተሰረዘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በዱከም ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት መሰረዙ ታወቀ። ለቶኒ ብሌር ጉብኝት መሰረዝ ምክንያቱ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት መሆኑ ታውቋል። ህዝባዊ እምቢተኝነቱና የስራ ማቆም አድማው ለሶስተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ተለያዩ አካባቢዎችም መዛመቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎም የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቶኒ ብሌር በዱከም የነበራቸው ጉብኝት ተሰርዟል። ቶኒ ቢሊየር ወደ ዱከም ...

Read More »

የተጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለ3ኛ ቀን ቀጠለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ለ3ኛ ቀን መቀጠሉ ታውቋል። በወሊሶ፣ ነቀምት፣ አዳማ፣ አወዳይ፣ አዲስ አበባ ዙሪያና ሌሎች በርካታ አከባቢዎች በሶስተኛው ቀን ተቃውሞ ተሳታፊ ሆነዋል። በወሊሶ ዛሬ በተካሄደው ትዕይንተ ህዝብ በስልጣን ላይ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ሕወሃት መንግስት ላይ ተቃውሞ ተሰምቷል። ዛሬም በወሊሶ ሱቆችና መደብሮች እንደተዘጉ ነው። በነቀምት ወለጋ በሶስተኛ ቀን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት ...

Read More »

በወልቂጤ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ። የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴም መቋረጡ ታውቋል። በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝባዊ ንቅናቄ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል። በሸካ ዞን ማሻም የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል። በጋምቤላ ከተማ የአድማ ጥሪ ወረቀት ተበትኗል። በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ታቅዶ የነበረው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ መጀመሩ ታውቋል። የወልቂጤ ነዋሪ የተጠራቀመውን ብሶትና ምሬቱን ያባባሰውን የሆስፒታል ግንባታ መቅረት ...

Read More »

በርካታ እስረኞች ከእስር ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ እንዲሁም አሕመዲን ጀበል፣አቶ ኦኬሎ አኳይን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ዛሬ ከወህኒ ተለቀቁ። ከሳምንት በፊት እንደሚፈቱ ከተገለጸ በኋላ የይቅርታ ደብዳቤ እንዲፈርሙ በመጠየቃቸውና አሻፈረኝ በማለት ንጽህናቸውን በማረጋገጣቸው የተስተጓጎለው የፍቺ ሒደት ዛሬ እውን መሆኑ ታውቋል። እጅግ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ድረስ በመሄድ አቀባበል አድርጎላቸዋል። በተያያዘ ዜና በትላንትናው ዕለት የተፈቱት አቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ...

Read More »

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከእስር ተለቀቁ

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከእስር ተለቀቁ (ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) ታዋቂውን ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋን እንዲሁም የቀድሞውን አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዱላአለም አራጌን ጨምሮ፣ በአገዛዙ ከፍተኛ በደልና ሰቆቃ የተፈጸመባት እማዋይሽ ዓለሙ፣የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር የሆኑት እነ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ፣ አርበኞች ግንቦት7 ትን ሊቀላቀል ሲል መንገድ ላይ እንደተያዘ የተነገረለት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት ...

Read More »

በኦሮምያ ተቃውሞው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ። በደቡብ በወልቂጤ ለ2 ቀናት የሚቆየው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀም

በኦሮምያ ተቃውሞው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ በደቡብ በወልቂጤ ለ2 ቀናት የሚቆየው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀምሯል (ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ውሎአል። በአዳማ ከእስር የተለቀቁትን የኦፌኮ ምክትል ሊ/መንበር አቶ በቀለ ገርባም ለመቀበል በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ገልጿል። አገዛዙን የሚያወግዙ መፈክሮችም ተሰምተዋል። ወጣቶቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ደም ...

Read More »

ኢሳትና የአሜሪካ ድምጽን በፍርድ ቤት ለመክሰስ በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ማህበር ውሳኔ አሳለፈ

ኢሳትና የአሜሪካ ድምጽን በፍርድ ቤት ለመክሰስ በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ማህበር ውሳኔ አሳለፈ (ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) የትግራይ ተወላጆች ማኅበር በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ እኤአ ጃንዋሪ 27 ቀን 2018 ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢሳትና ቪኦኤ አማርኛ ዝግጅት ክፍል በቀጥታና በተዘዋዋሪ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የሚያደርጉ በመሆናቸው ሕጋዊና ዲፕሎማሲዊ ዘመቻ እንዲደረግባቸው ሲል ውሳኔ አሳልፏል። የማኅበሩ አባላት በመላው ኢትዮጵያ በሚኖሩ የትግራይ ...

Read More »

በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል

(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል በአንዳንድ አካባቢዎች ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚጓዙ መንገደኞች በትራንስፖርት እጥረት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። የንግድ እቃዎችን የጫኑ መኪኖች በየቦታው ቆመዋል። በአዲስ አበባ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመው ማንኛውንም እንቅስቃሴ ...

Read More »

አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ

(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ ባለፉት 2 ቀናት በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የኦፌኮ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባ ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ ከእስር ተፈተዋል። ሰሞኑን ችሎት በመድፈር የአንድ አመት እስር የተፈረደባቸው እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ መፈታታቸው ውሳኔውን ላስተላለፉት ዳኞች ...

Read More »